No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 19 April 2013

! …… በለው ‘አውጫጭ’ ተጀመረ …….!

ባለፈው የትግራይ ህዝብ በምርጫ ወረቀቶች የተለያዩ ኣስተያየቶች (ኣብዛኞቹ ስድቦች) በመፃፍ ህወሓትን ማስጠንቀቁ ፅፌ ነበር። ያኔ ባስቀመጥኳቸው ቁጥሮች ታድያ ‘ማኖ የነካሁ’ መሰለኝ። 

የህወሓት መሪዎች በሰጠሁት ስታትስቲክስና የቀበለ መረጃ ተንተርሰው በማጣራት መረጃ የወጣባቸው የምርጫ ጣብያዎች እየለዩ ይገኛሉ። ይህን ያህል መረጃ የወጣበት መንገድና መረጃው የሰጡ ሰዎች ለማወቅ ‘ኣውጫጭ’ ጀምረዋል። በተጠቀሱት አከባቢዎች የነበሩ የምርጫ ታዛቢዎችና አስተባባሪዎች (ሁሉም የህወሓት አባላት ናቸው) ‘hard ዉስጥ’ ናቸው። (ወይኔ ድሮ ለኣውጫጭ ቅኔ ነበር መድሃኒቱ።) 

በተያያዘም ህወሓቶች እኔ ለምፅፋቸው መረጃዎች ምንጮቹ እነማን እንደሆኑ (የራሳቸው አባላት ወይ የዉስጥ ሰዎች እንደሚሆኑ ጥርጥር የላቸውም) ለማወቅ ‘ኣብርሃ ደስታ የሚባል ልጅ ከነማን ጋር እንደሚንቀሳቀስ ከድሮ በበለጥ ክትትል’ እንዲደረግበት ተወስነዋል። በዚህ መሰረት ድሮ እንዲከታተሉኝ ከተመደቡት ‘የደህንነት ሰዎች’ ኣሁን በሁለት እጥፍ ይጨምራሉ። እኔም ደስ አለኝ፤ አጃቢዎቼ (ዞምቢዎቹ) በዝተውልኛላ።

ይሄ ስልክ መጥለፍ ምናምን ተዉት እንዴ? ወይስ ብዙ …… መጠቀም እንደሚቻል ተገንዝበዋል? ለማንኛውም ሁለቱ የህወሓት/ ኢህኣዴግ ከፍተኛ ‘የደህንነት ሓላፊዎች’ ከፍተኛ ጠብ ላይ ናቸው። በሁለቱ መካከል የከረረ ጠብ ኣለ (ስም መጥቀስ ኣያስፈልግም)። እርስበርሳቸው የሚጣሉት ያህል እኔን ኣይጠሉኝም።



የደህንነት ሰዎች ሰለማዊ ግለ ሰዎችን ከመከታተል ይልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ነገሮች ቢያተኩሩ ጥሩ ነው። የገዢው ፓርቲ ህልውና ለማስቀጠል የዜጎች መብት ከመጣስ ይልቅ የህዝብን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማስጠበቅ ቢጥሩ መልካም ነው።

It is so!!!
source:Abraha Desta fb page.

No comments:

Post a Comment