No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 20 April 2013

! ……. የፍትሕ ሁኔታ በትግራይ …….!


ኣንድ Abraha Desta
ኣቶ ግርማይ ጀርመን ትናንት ማታ በዋስ ተለቀዋል። በኣክሱም ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለ ምክንያት (ወይ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት) ታስረው የሚሰቃዩ ንፁህ ዜጎች እንዳሉ ጠቁመዋል። እስረኞቹ የግል ሚድያዎች በኣክሱም ወህኒ ቤት ያለ መጨናነቅ እንዲዘግቡና እንዲያጣሩ ተማፅነዋል።
በትግራይ የፍትሕ ስርዓቱ የተዛባ ከመሆኑ የተነሳ ወንጀል ፈፅመው የታሰሩ (ለምሳሌ ‘ዓዲ ሃገራይ’ ተብሎ በሚጠራ ኣከባቢ ሁለት ልጆች በግፍ የገደሉ ሰዎች) ጥሩ እንክብካቤ ሲደረግላቸው ምክንያቱ በማይታወቅ (ወይ በፖለቲካ) የታሰሩ ግን ብዙ ችግር እንደሚደርስባቸው ተገልፀዋል።

ሁለት
በትግራይ ‘ፈረስ ማይ’ በሚባል ቦታ ዉሃ ከጠፋ ኣራት ወራት ቢያልፍም የሚመለከተው ኣካል መፍትሔ ሊሰጥ ባለመቻሉ ነዋሪዎቹ ለብዙ ዉሃ ወለድ በሽታዎች መዳረጋቸው ለማወቅ ተችለዋል። ኣስተዳዳሪዎች ለፖለቲካዊ ስብሰባዎች ብቻ እንጂ የህዝብ ማህበራዊ ችግሮች ግዜ እንደማይሰጡ ይነገራል።
ሦስት
በደጉዓ ተምቤን ልዩ ስሙ (ቁሸት) ‘ድንግለት’ (ሀገረ ሰላም ኣከባቢ መሆኑ ነው) በሚባል ኣከባቢ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ወደ ቤተክርስትያን (እንዳ ማርያም) እየሄዱ ፖለቲካ ስለሚሰብኩና ዕዳ ያለባቸው ኣባወራዎች ስለሚያስሩ የኣከባቢው ሰዎች ወደ ቤተክርስትያኑ ላለመሄድ በመኃላ ኣድማ እንደመቱና የቤተ ክርስትያኑ ቄሳውስት ሁኔታው በመረዳት ካድሬዎቹ ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ቢመክሩም ሰሚ ስላላገኙ ወረዳ ሄደው መክሰሳቸው ታውቀዋል።
ኣራት
በውቅሮ ኣከባቢ በሚገኝ ኣንድ ትምህርትቤት ተማሪዎች ለህወሓት ድጋፍ ሰልፍ እንዲወጡ ታዘው ፍቃደኛ ስላልሆኑ፣ በፓርቲው ደጋፊዎችና ገለልተኛ ኣቋም ያላቸው መምህራን ኣነስተኛ ግጭት ተፈጥሮ ትምህርትቤቱ ለኣንድ ቀን ተዘግቶ መዋሉ ታውቀዋል።
ኣምስት
(ከወራት በፊት ነው) ኲሓ ኣከባቢ ነው። ኣስተዳዳሪዎቹ የገበሬዎችን መሬት ወደ ከተማ እንዲገባ ተወስነዋል በማለት ለመውሰድ ሲሞክሩ የገበሬዎቹ ተወካዮች “መሬታችን ኣንሰጥም፣ ወደ ከተማ ኣልገባም፣ ከገባ ግን እንዲገባ የተወሰነበት ሕጋዊ የኣስተዳደሩ ወረቀት ወይ ፕላን ኣሳዩን።” በማለት ተቃውማቸው ያሰሙ ሲሆን ተወካዮቹ ያለ በቂ ምክንያት መታሰራቸው ታውቀዋል።
ስድስት
በእንደርታ ወረዳ የሚገኙ ኣርሶ ኣደሮች መሬታቸው በኢንቨስትመንት ስም ተነጥቀው ስርዓቱ ለሚደግፉ ባለሃብቶች እየተሰጠ ሲሆን ገበሬዎቹ ተደራጅተው ጉዳያቸው ለሚመለከተው ኣካል ቢያቀርቡም መፍትሔ እንዳላገኙ ጠቁመዋል። ማስፈራርያም እየደረሰባቸው ነው።
በመጨረሻ
በትግራይ ኣከባቢዎች ባደረግነው ፖለቲካዊ ተሞክሮ መሰረት (ስለ ኣብዛኛው ነዋሪ ቀለል ባለ ግምገማ መሰረት)
1) ለውጥ ፈላጊ: ኣላማጣ፣ ሑመራ፣ ተምቤን፣ ሽረ
2) ጥሩ የፖለቲካ ግንዛቤ ያለው (ለውጥ ለማምጣት ግን ቅስቀሳ የሚያስፈልገው): ውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ ኣክሱም፣ ማይጨው
3) በፍርሃት የሚኖር ህዝብ: እንደርታ፣ ሓውዜን፣ ዓድዋ
4) ሌሎች ኣከባቢዎች: ለመወሰን ኣስቸጋሪ ሁኖብኛል
ባጠቃላይ በትግራይ ሙስና ሕጋዊ ስራ ‘የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው’።
It is so!!!
source: Abraha Desta fb page.

No comments:

Post a Comment