No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Sunday 16 September 2012

ከ21 ዓመት በኋላ ህወሓት ተነፈሰ!! ህወሓትና ስዩም መስፍን በኢህአዴግ ምክር ቤት ድምጽ ተነፈጉ!


September 16, 2012 (ጎልጉል)
የመከላከያውንና የደህንነቱን የስልጣን ርካብ ከቀድሞው ይልቅ ቆንጥጦ ለመያዝ እየተረባረበ ያለው ህወሓት በግልጽ ከሚታየው የፖለቲካ አመራር ወንበሩ ተነሳ። ለ21 ዓመታት የድርጅት፣ የጠ/ሚኒስትርነትና ቁልፍ የስልጣን መደቦችን ተቆጣጥሮ የኖረው ህወሓት ሁለቱን ግዙፍ ወንበሮች ለማስጠበቅ በድርጅትና በጎንዮሽ ትስስር ያካሄደው ዘመቻ አልተሳካለትም።
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አቶ መለስን የሚተካ መሪ መሰየም አለመቻሉን አቶ በረከት ስምኦን ያሳበቁበት ህወሓት በቀጣዩ ምርጫም ወንበሩን እንደማያገኘው አቶ በረከት በግልጽ ተናግረዋል። ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ ሁለቱ አዲስ
ተሿሚዎች በስልጣናቸው እንደሚቀጥሉ በይፋ ተናግረዋል።

የኢህአዴግን የአመራር ወንበር ላለማጣት ያደረገው ሙከራ በየድርጅቶቹ በተካሄደ የተናጠል ስብሰባ ተሞክሮ ሊሳካ እንዳልቻለ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። በስም ተጠቅሰው ኢህአዴግን እንዲመሩ የቀረቡትን የህወሃት ሰዎች አንቀበልም ያሉት አባል ድርጅቶች በተቃራኒ በቀጣዩ የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ መተካካቱ በተዋጽዖ የተመጣጠነ እንዲሆን የሚያሳስብ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል።ከአቻ ድርጅቶቹ በተጨማሪ አሜሪካ ያስተላለፈችው መመሪያም ተጽዕኖ መፍጠሩ ተገምቷል።
ለዚህ ይመስላል አቶ በረከትና አቶ ሬድዋን ሁሴን በሂልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ላይ “አቶ ኃይለማርያም የራሳቸውን ካቢኔ የመመስረት ሙሉ መብት አላቸው” በማለት አቶ በረከት የቀድሞው ካቢኔ ሊፈርስ ወይም ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚችል አመላክተዋል።
የህወሓት/ኢህአዴግን አካሄድ በመገመትና በመተንተን የሚታወቁት ረዳት ፕሮፌሰር መድኔ ታደሰ ሴፕቴምበር 14 ለአሜሪካ ሬድዮ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል በሰጡት ማብራሪያ አሁን ተፈጠረው አጋጣሚ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ለውጥ ማስከተሉ አይቀሬ መሆኑን አስረድተዋል። አያይዘውም መለስ በሌሉበት ሁኔታ የቁጥጥር አስተዳደር ማራመድ እንማይቻልም አመልክተዋል። ከቁጥጥር ይልቅ ወደ መመካከርና አብዛኞችን ወደሚያሳትፍ አመራር እንደሚለወጥ ተናግረዋል።
ተተኪ ሊቀመንበር ለመሰየም ሲሳብና ሲጎተት የከረመው ኢህአዴግ ራሱ ካወጀው የአቶ መለስ ህልፈት ከሃያ ስድስት ቀናት በኋላ አስቀድሞ በስፋት የተተነበየውን ሹመት ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል አድርጎ ሰይሟል። አቶ ኃይለማርያም “ምደባው የመስዋዕትነት ነው” ሲሉ ለመንበራቸው ያላቸውን ቁርጠኛነት ለጓዶቻቸው አረጋግጠዋል። ህወሓትን ወክለው አቶ ስዩም መስፍን ለምርጫ ቢወዳደሩም ድምጽ በማጣታቸው ሳይመረጡ ቀርተዋል።
ብቸኛው የመረጃ ምንጭ ኢቲቪ መስከረም 4 ቀን 2005 ዓ ም በምሽቱ ሶስት ሰዓት የዜና እወጃው ቀንጭቦ ባቀረበው ምስል አቶ ኃይለማርያምና ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንን በኢህአዴግ ምክር ቤት የአመራር ወንበራቸው ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ታይተዋል።
source Maleda times

No comments:

Post a Comment