No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Wednesday 19 September 2012

ለተጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ ተጠያቂው ማን ነው ? Amhara Genocide Documentary MUST WATCH


በአሁኑ የአማራ ክልል መስተዳድር ስር የሚተዳደረው የክልሉ አስተዳደር በየጊዜው የከፋ አገዛዛዊ ስርአት እና ጭፍጨፋ ከመድረሱም በላይ ለከፍተኛ እልቂት  ተዳርጎአል ለዚህም ተጠያቂው የአማራ ክልል መስተዳድር ነው ይህም ሆኖ ሳለ  ክልል መስተዳድሩን በስሩ አድርጎ የሚያስተዳድረው እና እጁን ይዞ የሚያንቀሳቅሰው የወያኔ መንግስትም የዚሁ ድርጊት ተቋዳሽ ከመሆኑም በላይ ዋናው የድርጊቱ መርሃ ግብር ፈጣሪ እና ቀማሪ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል ።ሆኖም በአማራ ክልል ለደረሰው ጭፍጨፋ ተጠያቂው ማን ነው ብለን ስንጠይቅ መልሱ የትግራይ ህዝብ ነው ካላችሁ ተሳስታችኋል የትግራይ ህዝብ ከደሙ ንጹህ ነው ።በስልጣን ላይ ያለው ገዢው አስተዳደር ብቻ ነው ።ለትግራይ ህዝብ መሰደድ የአማራው ህዝብ ተጠያቂ
አይሆንም ለአማራው ህዝብ ኦሮሞ ወይም አፋር አይሆንም ዋነኛዎቹ መሪዎቹ ሆነው ሳለ እኛስ ለምን የህብረት አንድነታችን ተቋጨ ? ይህንን ለማለት ያነሳሳን በዚህ ቪዲዮ የምትመለከቱትን ዶክመንታሪ የጭካኔውን እና ግፈኝነት ለናንተ በመተው ፍርዱን እንድትሰጡ በማለት ነው
ሞረሽ የአማራ አንድነት ለዘ-ሐበሻ በላከው የ1 ሰዓት ዶኩመንታሪ ፊልም ላይ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በማሳየት ለሕዝብ እንድናደርስ ጠይቋል። በአማራው ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ይህ
ጥናታዊ ፊልም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለሌላው ወገኑ በማስተላለፍ ሕዝብ እንዲያውቀው በማድረግ ወገንተኛነቱን እንዲያሳይ ሞረሽ ይጠይቃል። ቪድዮውን ይመልከቱት። እውን ለትግራይ ሕዝብ መሰደድና ችግር ውስጥ መግባት የአማራ ሕዝብ ተጠያቂ መሆን አለበት? ቪድዮው ምላሽ አለው። (ይህን ቪድዮ ከ13 ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት እንዳይመለከቱት ይመከራል)
።መልካም እይታ
እንዲ ዳምኖ ዳምኖ የዘነበ እንደሆን
እንዴት ያሉ በሮች ይጠመዱ ይሆን
እንዲህ ጨሶ ጨሶ የነደደ እንደሆን
ያመዱ ማፍሰሻ ስፍራው ወዴት ይሆን>?

Amhara Genocide Documentary MUST WATCH

No comments:

Post a Comment