No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 22 September 2012

የበረከት አዜብና የስብሃት ፍጥጫ ከ ኢየሩሳሌም አርአያ

ሕወሀትን ከጀርባ በማሽከርከር የሚታወቁት ስብሀት ነጋ ለቀጣዩ ፍልሚያ ሀይል እያደራጁ ነው። ለበረከት ያላቸው ጥላቻ-ንቀት ጭምር የተላበሰ ነው። አዜብን ለመበቀል ግዜው አሁን እንደሆነ አረጋግጠዋል።የስብሀትና አዜብ ቁርሾ የተጠነሰሰው ከአምስት አመት በፊት ነበር። በወቅቱ የተወሰኑ የህውሀት ማ/ኮሚቴ አመራሮችን የሰበሰቡት አዜብ«ስብሀት ከኤፈርት ሃላፊነቱ መነሳት አለበት » ይላሉ። ትእዛዙን የተቀበሉት እነቴዎድሮስ ሀጎስ መልእክቱን ለሽማግሌው ያደርስሉ። ስብሀትም በቁጣ«ጉአል ጎላ ክትቅመጠሉ ድያ?ሞይተ ድየ ብደወይ?» ማለትም «የጎላ ልጅ ልትቀመጥበት ነው? ሞቼ ነው በቁሜ?» ነበር ያሉት። «የሚስቱን ትእዛዝ ሳያወላዳ ተግባራዊ ያደርጋል» ሲሉ በገረሜታ የሚገልጹአቸው መለስ በወቅቱ በአዜብ የቀረበውን ስብሀት ነጋን የማስነሳት ሀሳብ ከመተግበር ወደሁዋላ አላሉም።
«ፉከራ»ብቻ ሆነው የቀሩት ሽማግሌው ከኤፈርት፣በሁዋላም ከፓርቲው አመራር እንዲወጡ በማድረግ አዜብ የበላይነታቸውን አሳዩ። ስብሀት ነጋ ከስልጣን ከተነሱ በሁዋላ የባልና ሚስቱን ስም እየጠቀሱ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልቦዘኑም። አዜብ ከሽማግሌው አልፈው «ታማኝ» የተባሉ ጄኔራሎችን ሳይቀር ከሀላፊነት እንዲወገዱ አድርገዋል። ከነዚህም ጄ/ል ወዲ አሸብር እና ጄ/ል ዮሀንስ(ጆኒ) ሲጠቀሱ፣ የዛሬ አምስት አመት ለጄ/ል ሳሞራ በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ ወዲ አሽብር ለአንድ አመት የቁም እስረኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል።
እግዱ ተነስቶላቸው የሚመለሱበት፣ በሁዋላም ጠቅልለው የሚወጡበት አካሄድ ለፓርቲው ቅርብ ለሆኑ አባላት ጭምር ግራ ያጋባ እንቆቅልሽ እንደነበር ይጠቁማሉ። አዜብ ብዙ ርቀት ለመጝዋዝ የጣሩት የስብሀትን አካሄድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ነገርግን ያሰቡት እቅድ ሙሉ ለሙሉ ሳይሳካ የአሁኑ ጠንካራ ፍልሚያ ላይ ደርሰዋል።ስብሀት ከፓርቲው ሲለቁ «የእኔ» የሚሉአቸውን ሰዎች ቁልፍ ቁልፍ ቦታ እንዲጨብጡ አድርገዋል። የህወሀት ማ/ኮሚቴ ውስጥ የስብሀት ሁለት እህቶች አሉ።የፌደራል ደህንነት ቢሮ የሚመራው በጸጋዬ በርሄ (ሀለቃ)ሲሆን፣ የጸጋዬ ባለቤት ቅዱሳን ነጋ፣ የስብሀት ነጋ ታናሽ እህት ናት። ስብሀት በአዜብና በረከት ላይ ለከፈቱት የውስጥ ዘመቻ ከጎን ካሰለፉት አንዱ አርከበ እቁባይ ይገኙበታል።አርከበ ከአዜብ በተደጋጋሚ የደረሰባቸው ጥቃት ለመጠጥ ሱሰኝነትና ብስጭት ዳርጎአችው ቆይቶአል። የእግዜር ሰላምታ መለዋወጥ ካቆሙ ክርመዋል። ስብሀት አርከበን ከጎን ሲያሰልፉ ሌላም አላማ አንግበው ነው። ይኽውም የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ይረከባል ተብሎ የሚጠበቀው አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ታናሽ እህት ንግስቲ ገ/ክርስቶስ የአርከበ ባለቤት ናት። ብርሀነ የነበረው ወዳጅነትና ታማኝነት ከመለስ ጋር አብሮ ምእራፉ ተዘግቶአል።
ሌላዋ የሴት ጄነራል ተሿሚ አስካለ ብርሀኔ ትባላለች። ህወሀትን የተቀላቀለችው ከበርካታ ታዳጊ እኩዮችዋ ጋር ሲሆን ጊዜው ደግሞ ግንቦት 1970 አ.ም ነበር። አብረዋት ጫካ ከገቡት ሴቶች ሁሉም ማለት ይቻላል በነመለስ ተገፍተው ሜዳ ተጥለዋል። ጀነራል አስካለ ይህን ሹመት ማግኘትዋ አስገራሚ የሚያደርገው ነጥብ አለ። የቀድሞ አየር ሀይል አዛዥ ጀ/ል አበበ (ጆቤ) ባለቤት ስትሆን ፣ጆቤን ጨምሮ የጦር አዛዦችና ከፍተወታደራዊ መኮንኖች እንዲባረሩ የተደረገው በመለስ ህገወጥ ውሳኔና ፊርማ እንደነበር ምንጮቹ ያስታውሳሉ።

No comments:

Post a Comment