No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday, 7 May 2013

የኛ አሚሮች ዛሬም ፅኑ ናቸው ለአቋማቸው!!!

የህዝበ ተወካዬች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቃሊቲ ማረሚያ ቤቱን ለመጎብኘት በመጡበት ወቅት ከአሚሮቻችን ጋር ካደረጉት ውይይት ተቀንጭቦ የተወሰደ፡

የህዝበ ተወካዬች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በ21-8-05 ቃሊቲ ማረሚያ ቤቱን ለመጎብኘት በመጡበት ወቅት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት ድንቅ የኢስላም ልጆች የመረጣቹን ህዝብ ድምፅ ካላሰማቹ የናንተ ተወካይነት ምኑ ላይ ነው በማለት አጥብቀው ሲወቅሱ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በታችም የምታነቡት ከጅግኖቻችን አንዱ የሆነው ከፓርላማ አባል አቶ ጀምበሬ ጋር ያደረገውን ንግግር ነው፡፡

አቶ ጀምበሬ- እኛ የሙስሊሙ ጉዳይ መርገቡንና ጉዳዩም መፈታቱን፣ የመጅሊስ ምርጫ መደረጉን ባለፈው የሆኑ የፀጥታ አካላት ጋር ግጭት ተፈጥሮ የታሰሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ይህን ሰምተናል እነሱንም ለማየት ነው የመጣነው ብለው ተናገሩ፡፡
ይህን ሲናገሩ የሰማው ድንቅ የኢስላም ልጅ ነጠቅ አደረጋቸው እና የሚከተለውን አላቸው፡- - እናንተ የሚደርሳችሁ መረጃ የተዛባ(distorted) ነው ወይም መረጃ የሌላቸሁ ከሆናችሁ ይገርማል ፡፡ ባለፈው አርብ እለት እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በ44 ከተሞች ውስጥ የተቃውሞ ድምፅ
አሰምተዋል፡፡እናንተ ነገሩ ተፈቷልተረጋቷል ትላላችሁ፡፡ይህንን የሚሊየኖች ጩኸት አልሰማንም ካላችሁ ታዲያ እናንተ “””መንግስት አይደላችሁም ወይም መንግስት የለም ማለት ነው፡፡“”” ምክያቱም አንድም በዚህች ሀገር ላይ ምን እየተደረገ እንደሆነ መረጃ ሊኖራቸሁ ይገባል፡፡ ሁለተኛም መረጠን ያላችሁትን ህዝብ ጥያቄ ካዳመጣችሁ እደግመዋለሁ መንግስት አይደላችሁም ወይም መንግስት የለም ማለት ነው፡፡በሀገሪቱ ውስጥ ምን እየሆነ እንዳለ አላውቅም የሚል ከሆነ መንግስት የለም ማለት ነው፡፡
-ነገር ግን መረጃው እያላችሁ ሀቁን ደብቃችሁ መረጠን የምትሉትን ህዝብ ሳይሆን፤ህዝብ ምን ጠየቀ፤ጥያቄውስ ህጋዊና ሰላማዊ ነውን? ሳይሆን ፓርቲያችን ምን አለ! በማለት ለህዝብ ሳይሆን ለፓርቲ አገልጋይ ሆናችሁ ሀቅን ሸፍናችሁ ብትሄዱ ዛሬን ታልፉ ይሆናል ነገር ግን ህሊናችሁ እያወቀ ይህን ሀቅ ሸፍናችሁ ብታልፉ ነገ በታሪክ ትጠየቃላችሁ፡፡“””ህሊናችሁም ይበላቹሀል አንተም ህሊናህን ይበላሃል“” በማለት የህዝብ አለኝታነቱን አበክሮ በንግግር ገለፀላቸው፡፡ አቶ ጀምበሬም ቀጠል አደረጉና”

ጀምበሬ- አዎ አውቃለሁ ይበላኛል መንግስት ነጻነት ሰጣቸሁ……አህባሽ……የሚለው ጥያቄ………
ብለው ለመናገር ሲሞክሩ ወድያው ድንቁ የኢስላም ልጅ እቆማቸው እና የሚከተለውን ጨመረላቸው፡-

ጀግናችን፡-- NO አህባሽ ምናምኑን ተወው!!! ነጻነት የሰጠንም መንግስት ሳይሆን ህገ-መንግስቱ ነው፡፡ ጥያቄያችንም አህባሽ….ሳይሆን በመጀመሪያ ደረጃ የመንግስት የበላይ የሆነውን ህገ-መንግስት -መንግስት ራሱ እየጣሰው ህገ-መንግስቱ የሰጠንን ነፃነት እየነጠቀን በእምነታችን ጣልቃ ገብታል ይውጣልን የሚል የመብት ጥያቄ ነው የጠየቅነው፡፡ ስለዚህም ህዝብ ወከለን የምትሉ እናንተ የ40 ሚሊዮን ህዝብ ጥያቄ አንስታችሁ እንኳን ለመነጋገር አትፈልጉም፡፡ታዲያ ይሄ “ህዝብ“ “ህብረተሰብ“ የምትሉት አካል የትኛው ነው፡፡ ህዝብ እኛ ካልሆንን የት ስላለው ህዝብ ነው የምታወሩት፤አኛ ኢትዮጲያዉያን ነን ብለን እናስባለን እናንተ ስለኛ ማውራት ካቃታችሁ የሚሊየኖች ጥያቄ ማንሳት ካቃታችሁ፤እኛ ህዝብ ካልሆንን እናንተም ተወካይ ካልሆናቸሁ ወሬው ስለነማን ነው? ማንንስ ነው ወከልን የምትሉት? የእናንተ እዛ መቀመጥ ዋጋ ቢስ ነው ማለት ነው በማለት ድንቅ የሆነ ምላሹን በመስጠጥ ን የፓርላማ አባል የሆኑትን አቶ ጀምበሩ ዝም አሰኝቷቸዋል፡፡

ይህን የመሰሉ ጀግና እና በአቋማቸው ፅኑ የሆኑ አሚሮች ነው አላህ የሰጠን፡፡

አላሁ አክበር!!
source.Minillik Salsawi fb page.

No comments:

Post a Comment