No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 31 May 2013

ትህዴን በለቀቀው የጦር ኃይሉን የሚያሳይ ቪድዮ ዙሪያ አስተያየትዎ ምንድን ነው?

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የምስራቅ ክፍለ ጦር ግንባር ሰራዊቱን በዩቲዩብ በኩል ከለቀቀ በኋላ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
ትህዴን በዩቲዩብ በለቀቀው ቪድዮ “ሃይሌን አጠናክሬ ጠላትቼን ልቀጣ ተነስቻለሁ” ይላል። እንደ ትህዴን ገለጻ “የኢህኣዴግ ስርኣት የሚወድቀው በሰለማዊ ትግል ሳይሆን ራሱ በመረጠው በትጥቅ ትግል ስለሆነ፤ ኣንድነትን በመፍጠር እድሜ ጠላታችንን እናሳጥር” ሲል ጥሪውን በቪድዮው ስር አቅርቧል።
ይህን ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በተለይ አስመራን መቀመጫቸውን ያደረጉ ተቃዋሚዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰላማዊ ትግል አያዋጣም በሚል ጦር ሰራዊታቸውን የሚያሳዩ ቪድዮዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። የአርበኞች ግንባር ከዚህ ቀደም ቪድዮውን የለቀቀ ሲሆን አሁን ደግሞ ትህዴን ይህን ማድረጉ አንዳንዶች ትግሉ መቼ ይሆን ከአስመራ የሚወጣው ሲሉ ይጠይቃሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ተቃውሚዎቹ አንድ ሆነው ትግሉን ካላፋጠኑት አንዱ የአንዱ ጠላት እንዳይሆን ፍራቻ ያላቸው አስተያየት ሰጪዎች አሉ።
እርስዎም ቪድዮውን ይመልከቱና አስተያየትዎን ይስጡ። ምን ያስባሉ?
 

source: the habesha

No comments:

Post a Comment