የአራት ዓመት ማነጻጸሪያ የቀረበበትን የሪፖርቱ አንያንዳንዱ
ክፍል ያስገርማል። የማነጻጸሪያው ማሳረጊያ አስደንጋጭ ነው። መረጃው በአሃዝ፣ በኩኔታ፣ በባህሪው ስደትን ይገልጻል።
ትንታኔው በካርታ፣ በስደቱ መነሻና መድረሻ መካከል፣ እንዲሁም በስደት መዳረሻ ላይ የሚያጋጥመውን አፈና፣ ቶርቸር፣
አስገድዶ መደፈር፣ ስቃይ፣ የባህር ሲሳይ የሆኑ ወገኖችን ይጠቅሳል።
በተለይ በምስራቅ አፍሪቃ በኤርትራ፣ በኢትዮጵያ በኬንያ፣
በጅቡቲ፣ በሶማሊያና፣ፑንት ላንድ፣ ሶማሊ ላንድ፣ ስደትና የስደትን አስከፊነት በሪፖርቱ ተዘርዝሯል። አገራችን
ኢትዮጵያ በስደት የተለዩዋት ዜጎቿ ቁጥር አገር አልባ ከሆነችው ሶማሊያ የሚልቅበትን ሁኔታ ያመላክታል።
የዓለም የስደተኞች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽርን /UNHCR/
በመጥቀስ የኖቬምበር 2012 ሪፖርቱን ያቀረበው Regional Mixed Migration Secretariat
/RMMS/ የተባለው ከኢሚግሬሽን ድርጅት ጋር የሚሠራውና በአውሮጳ ኮሚሽን እና በሌሎች ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ድርጅት
ከ2009 – 2012 ከኢትዮጵያ ወደ የመን የተሰደዱትን ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከሶማሊያ ጋር በማነጻጸር ያቀርባል።
በዚህ ማነጻጸሪያ መሰረት 223ሺህ 770 ወገኖች ወደ የመን በነፍስ ግቢ በነፍስ ውጪ የባህር ጉዞ ወደ የመን
አቅንተዋል። በተመሳሳይ ከሶማሊያ 100ሺህ 845 ሰዎች የመን በተመሳሳይ ገብተዋል። እንግዲህ እዚህ ላይ ነው
አሳሳቢውና አስደንጋጩ ጉዳይ የሚነሳው።
በኢኮኖሚ ከዓለም አገሮች ሁሉ እጅግ ተመንጥቃ ባለሁለት አሃዝ
እያደገች መሆኗ የሚነገርላት ኢትዮጵያ ወደ የመን ብቻ ከገቡት ስደተኞች በችግርና ያለ አስተዳዳሪ መንግሥት ሁለት
አስርተ ዓመታት ካሳለፈችው ከሶማሌ በመቶ ሺህ ስምንት መቶ ይበልጣሉ።
Abuse: Most of the Ethiopians arriving
in Yemen are enroute to Saudi Arabia. They normally travel along the
eastern side with smugglers (benign or violent) up to Haradh area in
order to cross into KSA. The incidences of kidnapping, torture, rape and
extortion of new arrivals is very high. Ethiopian Christians face
persecution for openly or privately exercising their faith.
የኦሮሞ ተወላጆችን በማስቀደም የዘረዘረው ሪፖርት በሁለተኛነት
ኦጋዴን፣ በሶስተኛ ደረጃ አማራን፣ በአራተኛ ደረጃ የትግራይ ተወላጆችን በቅድም ተከተል የሚዘረዝረው ሌላው
የRegional mixed migration secretariat /RMMS/ ሪፖርት ኢትጵያዊያን በስደት ስለመሞታቸው
ያወሳል። በካርታ የተመለከተው የስደተኞች የእንክርት ጉዞ በየብስና በውሃ በማመላከት ያስቀመጠው ሪፖርቱ፣ ኤርትራን
ጨምሮ አስደንጋጭ የስደት መረጃ ይፋ አድርጓል። አራቱንም ሪፖርት ከዚህ በታች አትመነዋል፡፡ ማጣቀሻውን በመጫን
ዝርዝሩን መመልከት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
No comments:
Post a Comment