ከዳዊት ዋስይሁን
ገበሬውን ከመሬቱ አፈናቅለው ጭሰኛ አድርገውታል ድምጼ ተነጠቀ ብሉ አደባባይ የወጣውን ሰላማዊ ዜጋ መንግስቴን ሊንድ ነው በማለት ክሁለት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ቀጥተኛ ትእዛዝ እስፍጭፈዋል ከደቡብ የኢትዮጵያ ክልል ለረጅም ግዜ ተደላድሎና ቤተሰብ መስርቶ የነበረውን ሰባ ሺህ የአማራ ገበሬ አፋናቅለውታል፣ በጋምቤላ ክልል አኝዋኮችን አስጨፍጭፈዋል ጥቅጥቅ ደኖችን አስመንጥረው ለባእዳን መሬቱን ሰጥተወል፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በቤንሻንጉል እንዲኡህም በኦጋዴን ህዝብ አስፈጅተዋል፣ የወታደራዊ፣ የደህንነትና የኢኮኖሚውን ዘርፍ በራሳቸው ጥቂት ቡድኖች ቁጥጥር ስር እንዲሆን አድርገዋል። መለስ ዜናዊ ሁለት ፊት ሲኖራቸው አንደኛው እሳቸውን ለሚረዷቸው ምእራባውያንና ደጋፊዎቻቸው ሁል ግዜ የሚያሳዩት የተማሩ ፈገግታ ከፊታቸው የማይለይ አስተዋይ አስመሳይና ብልጣብልጥንት የተላበሱ ጮሌ ሲሆኑ ለአገራቸው ህዝብ ደግሞ አንድ ቀን አደባባይ ያላያቸው የማያነጋግሩት የሚጠሉት ደስ ሲላቸው የሚሰድቡት የሚያሳስሩት የሚያሰቃዩት ወዘተ ሲሆን ይህንን ባህሪያቸውን ቀረብ ያሉ አጋሮቻቸው የሚያውቁ ሲሆን የማያውቁት ግን ጮሌ ነታቸውን እንደትልቅ አዋቂነት እየቆጠሩ የሚያሞጋግሱዋቸው ብዙዎች አሉ። መለስ የአገራቸውን ተቃውሞ በመግታትና ብቻ ጸጥ በማድረግ አልተቆጠቡም እንደውም እጃቸውን ወደ አውሮፓና አሜሪካ በማስረዘም በሳቸው ለይ የሚደረግ ማናቸውንም አይነት ተቃውሞ ጸጥ ለማድረግ ላይ ታች ሲሉ ያልተሳካላቻው መሪ ነበሩ ከዚህም ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የተቃውሞ እንስቃሴዎችን ከንቱ ሊያስቀር የሚችል የቅጥር የዲብሎማሲ ስራ ማሰራት ይገኝበታል ይህም በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካ ተጽእኖ ማምጣት የሚችሉ ፖለቲከኞችን መቆጣጠርና ደጋፊ ባይሆኑ እንኳን ተቃዋሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ለይ የተኮረው ስራቸው ደግሞ በአንዳንድ ቦታዎች በብዙ መቶ ሺህ ዶላር እየከፈሉ ይህንን ሊሰሩ የሚችሉ የውጭ ዜጎችን መቅጠርንም ያጠቃልላል። ሌላው በኢንባሲዎቻቸው አማካኝነት የስለላን ስራ ማከናወን ሲሆን ለዚህም እንደማስረጃ የሚጠቀሰው ከኢንባሲዎች አካባቢ ሾልኮ የወጣ መረጃ ሲኖን ይህም በየትኛውም አካባቢ የሚከናወን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በፊልም ተቀርጾ፤ በፎቶ የተደገፈ ሰልፋ ላይ የተሳተፉ ስም ዝርዝር፡ ሰልፋን ያስተባበሩ ግለሰቦች ስም የት ቦታ እንደተደረገ፤ ቀኑና ሰአቱ አንዲሁም የስልፋ አላማ የሚያጠቃልል መረጃ ለውጭ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኮፒ እንዲደረግ ለኤምባሲዎቻቸው የሚያከናውኑት ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ሌላው ኢምባሲ በሌለበት ቦታ የሚደረግ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሚጠቀሙበት አሰራር ሁለት አይነት ሲሆን አንደኛው ነጻ የሆኑ ግለሰቦችን በመጠቀም በዛ አካባቢ ያለ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ከተቻለ ደጋፊ እንዲሆን ካልተቻለ ከማንኛውም እንቅስቃሴ እንዲርቅ የሚንቀሳቀስ ከሆነ የሚያረገውን እንቅስቃሴ መከታተልና ሪፖርት ማድረግ ማስፈራራት ማሸማቀቅና ከእንቅስቃሴው እንዲገታ ማድረግ ሁለተኛው የአገዛዙ ደጋፊዎችና አቀንቃኞች በየአካባቢ የሚደረግ እንቅስቃሴን የመከተተልና ሪፖርት የማድረግ፤ የማስፈራራት የማሸማቀቅ አላፊነት አለባቸው። ለምሳሌ ሰፕቴምበር 2፣ 2012 ባደረግነው በአለፋት 21 አመታት የተጨፈጨፉ፤ የተገደሉ የታሰሩ ሰማእታትን የማሰብ ሰልፍ አምባገነኑ መለስ በሚቀበርበት ቀን እዚሁ ኦስሎ የርንባርንቶገት አድርገን ነበር ይህ ሰልፍ ከመደረጉ በፊ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ማህበረሰቡን የማስፈራራት ዘመቻ ቁጥሩ በመይታይ በስልክ በመደወል ዘመቻ አድርገው ነበር አልፎ አልፎም በግምባር ሰዎች ጋር በመሄድ ለማስፈራራት ያደረጉት ሙከራም እንዳለ የቃል ሪፖርት ደርሶናል። ይህ አልበቃ ብሎአቸው በሰልፋ ቀን ከሚጠበቀው በላይ ሰው በመገኘቱ የተበሳጩ የገዢው መደብ ደጋፊዎች እና ሲምፓታይዘሮች ተደራጅተው በመምጣት ከየአቅጣጫው ጠርዝ ይዘው ፎቶ ሲያነሱና የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሲከታተሉ እንደነበር በፎቶም በምስክርም ይዘንዋል እንደውም ይህ አልበቃ ብሏቸው አንደኛው ግለሰብ ከካሜራማንና ከጥበቃ ስራ ላይ ያሉ አባሎቻችንን ካልደበደብኩ ብሎ ሲጋበዝም ነበር ከዚህም አልፎ እንኝህን ግለሰቦች እና ሰልፉን ያስተባበሩትብ እንደሚገሉ ደጋግሞ ሲዝት ተስምቷል። እንግዲህ ይህ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በግዛቷ ማንም በነጻነት መኖር በሚችልባት ኖርዌይ ምድር ነው። እነኝህ የግዢው ድርጅት ደጋፊዎች እዚህ አገር የመለስ ስርአት አሰቃየን ብለው ስደት ጠይቀው መልስ ከተሰጣቸው በኻላ ብዙም ሳይቆዮ አሳደደን ያሉትን መንግስት ሲደግፉ ማየት እየተለመደ መጥቷል እነኝሁ ደጋፊዎች ከኦገስት24-26፤ 2012 የአምባገነኑን ሞት ምክንያት በማድረግ በሶፊንበርግ ቢተክርስትያን ሲያዝኑ ሲሰበሰቡ የፈለጉትን መደገፍ የዲሞክራሲ መብታቸው ስለሆነ መረጃው ቢደርሰንም ምንም አላደረግንም ነገር ግን ሸሽተን የመጣንበት አገር እኛ የነሱን መብት ስናከብር እነሱ ግን እኛን ከመሰለልና ከማሸማቀቅ አልፈው ሊደበድቡንና ሊገሉንም እየዛቱና እየተጋበዙ ይገኛሉ። እንግዲህ ብዙ አልኩ መለስ ሞቶአል ከፊት ለፍታችን ሁለት አማራጮች አሉ አንደኛ ለኢትዮጵያ አገራችን ሰላም በማሰብ ገዢው ፓርቲ በዛች አገር ጉዳይ ላይ ያገባኛል የሚሉ ወገኖችን ሁሉ በመጋበዝ ለአገራችን እና ህዝባችን የወደፊት ብሩህ ተስፋን መክፈትና ታሪክን መስራት ሲሆን ሁለተኛው መለስ የጀመረውንና የገነባውን ሁሉን ጠቅልሎ የሚይዝ የሚያፍን የሚገል የሚያስር የሚያሰቃይ ስርአት በጠነከረ ሁኔታ ማስኬድ ሲሆን ደሞም በአሁን ሰአት የሚታየው እንቅስቃሴ በሁለተኛው መንገድ እየገፉበት እንዳለ ነው። ታዲያ ይህንን ሁሉ መከራ በህዝቤ ላይ ያወረደን መሪ ቢሞት እንዴት አድርጌ ልዘንለት፤ ይህንን መራርነትና ጭካኔ የፈጠረብኝ እርሱ ነው ስለዚህ ምንም ሰው ይሙት ባይባልም መለስ ዜናዊን ይሙት እላለሁ ሰለሞተም ደስ ብሎኛል።
ኢትዮጵያ የሚለው ያገሬ ስም ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ የፍልስፍና የሃይማኖት እንዲሁም ትላልቅ መጽሃፍት ብዙ ጊዜ የተጠቀሰች
የህዝብ ብዛቷ ወደ 90 ሚሊዮን የተጠጋ ከመቶ በላይ ብሄረሰቦችና ቋንቋ ለዘመናት ተፈቃቅረው ያሉባት ሙስሊሙና ክርስትያኑ
ተቻችሎ የሚሮርባት በተፈጥሮ የታደለች የበለጸገች አገር ነች።
እንዲህ በባህልና በታሪክ የምትጠቀስና የሚኮራባት አገር ብትሆንም ይህችን አገር እና ህዝቧን ልትኮራበት የምትችልና ለተጠማችው
የነጻነት የፍትህ የዲሞክራሲ ህልሟ እውን ሊያደርግላት የሚችል መሪ እስካሁን አልታደለችም»
እንደ እድል ሆኖ ሁለተኛ መንግስት ማየቴ ነው ማርክስሲቱ የወታደራዊው አገዛዝ ደርግ ለአገራችን ውድቀት ተጠያቂ ተደርጎ
በብዙዎች ዘንድ ቢገለጽም በአገር አንድነትና በኢትዮጵያዊነት ላይ እንደማይደራደር የሚወጉት የነበሩ
የአሁኖቹ ባለስልጣናት
እንኳን ይመሰክሩለታል»
የቀሪውን ዘመኔን ያሳለፍኩት በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ስለሆነ ስለሳቸው ብዙ ነገር ማለት እችላለሁ እኝህ አምባገነን መሪ ከደፈጣ
ውጊያ አገር ለመምራት የአለፈውን ስርአት ገረሰስሁ ቢሉም ውነታው ግን በዛ ወቅት ገበሬው ወታደሩ ተማሪውና ወጣቱ በረዘመና
በተንዛዛ ጦርነት ሰልችቶ ስለነበር የወያኔ ወታደርን እየመራ አዲስ አበባ ያስገባቸው በዘመናቸውም ያመሱትና ያሰቃዩት ይህ
ኢትዮጵያዊ ነው
ባለፉት 21 የአገዛዝ ዘመናቸው አገራችንን ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን በመጥላትና በማዋረድ የገዙ መሪ ሲሆኑ ህዝቡን በምግደል
በማሰር በማሰቃየት ወደር ያልተገኘላቸውም መሪ ነበሩ ዛሬ አፈር ውስጥ ከገቡ በኻላ አንዳንድ እውር ደጋፊዎቻቸው በአለም ላይ
እሳቸውን የሚተካ ጀግናም እንደሌለ እየነገሩን ነው።
እሳቸው ሳይሞቱ የኢትዮጵያን ህዝብ በስቃይና በመከራ ማስለቀሳቸው ሳያንስ ዛሬ የአገሬን እዝቦች በየቀበሌና በየ አደባባዩ ህዝቡን
በግድና በገንዘብ እየከፈሉ ውጡ እያሉ እያስለቀሱት ይገኛሉ። ይህዝብም ምርጫ የለውም ውስጡ እያረረና እየራበው ለመሪው
ሳይሆን ምን መከራ ውስጥ እንደገባ በመማረር ለራሱና ለትውልድ ያለቅሳል ያነባል።
ለመሆኑ መለስ ዜናዊ በሃያ አንድ አመት የስልጣን ዘመናቸው ለኢትዮጵያ ምን ሰሩላት አዎ ዛሬ ደጋፊዎች የሚኩራሩበት አዲስ
አበባን በቀለም ለመቀባት ሞክረዋል ትልልቅ ህንጻም ሰርተዋል መንገድም ነገር ግን ሁላችንም የማንዘነጋው አንድ ነገር አለ እሱም
ኢትዮጵያ በአመት አራት ቢሊዮን ዶላር እርዳታ እንደምታገኘ በአለምም ሁለተኛዋ እርዳታ ተቀባይ አገር መሆንዋን ነው
መረጃዎች የሚያሳዩት እንግዲህ ይህንን ያህል እርዳታ እየተቀበለች ገንዘቡ የት ገባ ወይስ ይህ ብቻ የተሰራው በቂ ነው ወደፊት
የምንመረምረውና የኦዲተሮች ስራ ይሆናል ይህም ሆኖ ግን የተባለለትና የተመሰከረለት ይህ እድገት ማንን ነው የጠቀመው ብለን
ብንመረምር ጥቂት የተወሰኑ የድርጅቱ አቀንቃኘ አባላትን እና የትግራይ ልማት ማህበር ንብርት የሆነውን የኤፈርት የኢኮኖሚ
ኢምፓየር ነው ዛሬ ይህች አገር ለተወሰኑ መደሰቻ ለብዙሃን ማልቀሻና መሰቃያ አገር እየሆነች እንዳለ ግልጥ ያለ እውነታ ነው
ለዚህም እንደማስረጃ ማየት ካስፈለገ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ፈሰው ያሉትን ከአራት መቶ ሺህ በላይ የጎዳና ተዳዳሪዎችን
ማየትና ከነሱ ምንም ሳይርቅ የገዚው መደብ አባላት በሼራተን የሚያረጉትን መዝናናት ተገንዝቦ እድገቱ የመጣው ለማን እንደሆን
መገመት አያዳግትም።
የሚገርመው መለስ የዛሬ ሃያ አንድ አመት ሰለኢትዮጵያ በአስር አመት ሊሰሩ የሚያስቡትን ሲነግሩን ይህ ህዝብ አሉን በቀን ሶስቴ
እንዲበላ ከዛም ልብሱን በየተወሰነ ግዜ እንዲቀይር ተግቼ እሰራለሁ አሉ ብዙ አሉ ዛሬ ግን ያለው እውነታ 90 % ህዝብ ጦሙን
የሚያድርበትና በቀን አንዴ መብላት የሚያቅተው ሲሆን የቀረው 10% ጠግቦ የሚቦርቅበት የሚያበራ የኢኮኖሚ እድገትን
አውርሰውን አልፈዋል።
እርሳቸው ባስተዳደሩበትና በገዙብት ዘመን የሚቃወማቸው እንዳይኖር ምለው በመነሳት የሰላም ሆነ ማንኛውንም አይነት ትችት
የሚሰነዝሩባቸውን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች እየለቀሙ በውሸት ክስ በመክሰስ ዛሬ የኢትዮጵያ እስርቤቶች
በንጹሃን ዜጎች ተሞልተዋል።
መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ በሃያ አንድ አመታት ያበረከቱት ትልቅ አስተዋጾ ውስጥ በጥቂጡ የሚዲያ ህግን በማውጣት የነጻውን
ሚዲያ ሙሉ ለሙሉ አሽመድምደውታል ይህም ተሳክቶላቸዋል፣ የየበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህግ በማውጣት ለሚሊዪን ድሃ
ኢትዮጵያውያን ድጋፍና በሰላምና በዲሞክራሲ ግንባታ ላይ ይሰሩ የነበሩ የእርዳታ ድርጅቶችን ሁሉ አዘግተዋል፣ የጸረ ሽብር
አዋጅን በማውጣት በአገር ቤት የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ማፈኛ መሳሪያ አድርገውታል
በዚህም ህግ በመጠቀም በርካቶችት ዘብጥያ ወርውረውበታል።ገበሬውን ከመሬቱ አፈናቅለው ጭሰኛ አድርገውታል ድምጼ ተነጠቀ ብሉ አደባባይ የወጣውን ሰላማዊ ዜጋ መንግስቴን ሊንድ ነው በማለት ክሁለት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ቀጥተኛ ትእዛዝ እስፍጭፈዋል ከደቡብ የኢትዮጵያ ክልል ለረጅም ግዜ ተደላድሎና ቤተሰብ መስርቶ የነበረውን ሰባ ሺህ የአማራ ገበሬ አፋናቅለውታል፣ በጋምቤላ ክልል አኝዋኮችን አስጨፍጭፈዋል ጥቅጥቅ ደኖችን አስመንጥረው ለባእዳን መሬቱን ሰጥተወል፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በቤንሻንጉል እንዲኡህም በኦጋዴን ህዝብ አስፈጅተዋል፣ የወታደራዊ፣ የደህንነትና የኢኮኖሚውን ዘርፍ በራሳቸው ጥቂት ቡድኖች ቁጥጥር ስር እንዲሆን አድርገዋል። መለስ ዜናዊ ሁለት ፊት ሲኖራቸው አንደኛው እሳቸውን ለሚረዷቸው ምእራባውያንና ደጋፊዎቻቸው ሁል ግዜ የሚያሳዩት የተማሩ ፈገግታ ከፊታቸው የማይለይ አስተዋይ አስመሳይና ብልጣብልጥንት የተላበሱ ጮሌ ሲሆኑ ለአገራቸው ህዝብ ደግሞ አንድ ቀን አደባባይ ያላያቸው የማያነጋግሩት የሚጠሉት ደስ ሲላቸው የሚሰድቡት የሚያሳስሩት የሚያሰቃዩት ወዘተ ሲሆን ይህንን ባህሪያቸውን ቀረብ ያሉ አጋሮቻቸው የሚያውቁ ሲሆን የማያውቁት ግን ጮሌ ነታቸውን እንደትልቅ አዋቂነት እየቆጠሩ የሚያሞጋግሱዋቸው ብዙዎች አሉ። መለስ የአገራቸውን ተቃውሞ በመግታትና ብቻ ጸጥ በማድረግ አልተቆጠቡም እንደውም እጃቸውን ወደ አውሮፓና አሜሪካ በማስረዘም በሳቸው ለይ የሚደረግ ማናቸውንም አይነት ተቃውሞ ጸጥ ለማድረግ ላይ ታች ሲሉ ያልተሳካላቻው መሪ ነበሩ ከዚህም ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የተቃውሞ እንስቃሴዎችን ከንቱ ሊያስቀር የሚችል የቅጥር የዲብሎማሲ ስራ ማሰራት ይገኝበታል ይህም በአውሮፓም ሆነ በአሜሪካ ተጽእኖ ማምጣት የሚችሉ ፖለቲከኞችን መቆጣጠርና ደጋፊ ባይሆኑ እንኳን ተቃዋሚ እንዳይሆኑ ማድረግ ለይ የተኮረው ስራቸው ደግሞ በአንዳንድ ቦታዎች በብዙ መቶ ሺህ ዶላር እየከፈሉ ይህንን ሊሰሩ የሚችሉ የውጭ ዜጎችን መቅጠርንም ያጠቃልላል። ሌላው በኢንባሲዎቻቸው አማካኝነት የስለላን ስራ ማከናወን ሲሆን ለዚህም እንደማስረጃ የሚጠቀሰው ከኢንባሲዎች አካባቢ ሾልኮ የወጣ መረጃ ሲኖን ይህም በየትኛውም አካባቢ የሚከናወን የተቃውሞ እንቅስቃሴ በፊልም ተቀርጾ፤ በፎቶ የተደገፈ ሰልፋ ላይ የተሳተፉ ስም ዝርዝር፡ ሰልፋን ያስተባበሩ ግለሰቦች ስም የት ቦታ እንደተደረገ፤ ቀኑና ሰአቱ አንዲሁም የስልፋ አላማ የሚያጠቃልል መረጃ ለውጭ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኮፒ እንዲደረግ ለኤምባሲዎቻቸው የሚያከናውኑት ተግባር መሆኑ ይታወቃል። ሌላው ኢምባሲ በሌለበት ቦታ የሚደረግ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሚጠቀሙበት አሰራር ሁለት አይነት ሲሆን አንደኛው ነጻ የሆኑ ግለሰቦችን በመጠቀም በዛ አካባቢ ያለ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ከተቻለ ደጋፊ እንዲሆን ካልተቻለ ከማንኛውም እንቅስቃሴ እንዲርቅ የሚንቀሳቀስ ከሆነ የሚያረገውን እንቅስቃሴ መከታተልና ሪፖርት ማድረግ ማስፈራራት ማሸማቀቅና ከእንቅስቃሴው እንዲገታ ማድረግ ሁለተኛው የአገዛዙ ደጋፊዎችና አቀንቃኞች በየአካባቢ የሚደረግ እንቅስቃሴን የመከተተልና ሪፖርት የማድረግ፤ የማስፈራራት የማሸማቀቅ አላፊነት አለባቸው። ለምሳሌ ሰፕቴምበር 2፣ 2012 ባደረግነው በአለፋት 21 አመታት የተጨፈጨፉ፤ የተገደሉ የታሰሩ ሰማእታትን የማሰብ ሰልፍ አምባገነኑ መለስ በሚቀበርበት ቀን እዚሁ ኦስሎ የርንባርንቶገት አድርገን ነበር ይህ ሰልፍ ከመደረጉ በፊ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ማህበረሰቡን የማስፈራራት ዘመቻ ቁጥሩ በመይታይ በስልክ በመደወል ዘመቻ አድርገው ነበር አልፎ አልፎም በግምባር ሰዎች ጋር በመሄድ ለማስፈራራት ያደረጉት ሙከራም እንዳለ የቃል ሪፖርት ደርሶናል። ይህ አልበቃ ብሎአቸው በሰልፋ ቀን ከሚጠበቀው በላይ ሰው በመገኘቱ የተበሳጩ የገዢው መደብ ደጋፊዎች እና ሲምፓታይዘሮች ተደራጅተው በመምጣት ከየአቅጣጫው ጠርዝ ይዘው ፎቶ ሲያነሱና የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሲከታተሉ እንደነበር በፎቶም በምስክርም ይዘንዋል እንደውም ይህ አልበቃ ብሏቸው አንደኛው ግለሰብ ከካሜራማንና ከጥበቃ ስራ ላይ ያሉ አባሎቻችንን ካልደበደብኩ ብሎ ሲጋበዝም ነበር ከዚህም አልፎ እንኝህን ግለሰቦች እና ሰልፉን ያስተባበሩትብ እንደሚገሉ ደጋግሞ ሲዝት ተስምቷል። እንግዲህ ይህ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በግዛቷ ማንም በነጻነት መኖር በሚችልባት ኖርዌይ ምድር ነው። እነኝህ የግዢው ድርጅት ደጋፊዎች እዚህ አገር የመለስ ስርአት አሰቃየን ብለው ስደት ጠይቀው መልስ ከተሰጣቸው በኻላ ብዙም ሳይቆዮ አሳደደን ያሉትን መንግስት ሲደግፉ ማየት እየተለመደ መጥቷል እነኝሁ ደጋፊዎች ከኦገስት24-26፤ 2012 የአምባገነኑን ሞት ምክንያት በማድረግ በሶፊንበርግ ቢተክርስትያን ሲያዝኑ ሲሰበሰቡ የፈለጉትን መደገፍ የዲሞክራሲ መብታቸው ስለሆነ መረጃው ቢደርሰንም ምንም አላደረግንም ነገር ግን ሸሽተን የመጣንበት አገር እኛ የነሱን መብት ስናከብር እነሱ ግን እኛን ከመሰለልና ከማሸማቀቅ አልፈው ሊደበድቡንና ሊገሉንም እየዛቱና እየተጋበዙ ይገኛሉ። እንግዲህ ብዙ አልኩ መለስ ሞቶአል ከፊት ለፍታችን ሁለት አማራጮች አሉ አንደኛ ለኢትዮጵያ አገራችን ሰላም በማሰብ ገዢው ፓርቲ በዛች አገር ጉዳይ ላይ ያገባኛል የሚሉ ወገኖችን ሁሉ በመጋበዝ ለአገራችን እና ህዝባችን የወደፊት ብሩህ ተስፋን መክፈትና ታሪክን መስራት ሲሆን ሁለተኛው መለስ የጀመረውንና የገነባውን ሁሉን ጠቅልሎ የሚይዝ የሚያፍን የሚገል የሚያስር የሚያሰቃይ ስርአት በጠነከረ ሁኔታ ማስኬድ ሲሆን ደሞም በአሁን ሰአት የሚታየው እንቅስቃሴ በሁለተኛው መንገድ እየገፉበት እንዳለ ነው። ታዲያ ይህንን ሁሉ መከራ በህዝቤ ላይ ያወረደን መሪ ቢሞት እንዴት አድርጌ ልዘንለት፤ ይህንን መራርነትና ጭካኔ የፈጠረብኝ እርሱ ነው ስለዚህ ምንም ሰው ይሙት ባይባልም መለስ ዜናዊን ይሙት እላለሁ ሰለሞተም ደስ ብሎኛል።
No comments:
Post a Comment