No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday, 4 September 2012

የኢህአዴግ ቡድን የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ዘመቻ መጠቀሙ እንዳሳፈራቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ተናገሩ

ነሀሴ ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ፌደራሊስ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ የበላይ ጠባቂና የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ቡልቻ ፣ አቶ መለስ ዜናዊ እንደ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ዲክታተር ነበሩ ብለዋል::

የኢህአዴግ ቡድን የአቶ መለስን ሞት ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል ኢስነምግባራዊ እና የሚዘገንን ነው በማለት መላውን የኢህአዴግ አመራሮች ወቅሰዋል ::

ኢህአዴግ ህዝቡን አልቅሱ ብሎ አለማስገደዱን ይልቁንም በራሱ ፈቃድ ፈንቅሎ እንደወጣ ይናገራል ተብለው ለተየጠቁት አቶ ቡልቻ፣ ኢህአዴግ በህዝብ ሀብት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በግልጽ ቅስቀሳ ያደርግ እንደነበር ጠቅሰዋል ::

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ልኡክ የሆኑት ሱሳን ራይስ ለአቶ መለስ የሰጡት ምስክርነት የግል ስሜትን ከመንግስት አቋም ጋር የቀላቀለ ነው ብለው እንደሚረዱት አቶ ቡልቻ ተናግረዋል::

አንድ ቡድን ስልጣኑን ይዞ ለመቀጠል የሚያስብ ይመስላል የሚሉት አቶ ቡልቻ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜቱን እንዲገልጥ ሊፈቀድለት ይገባል ሲሉ መክረዋል::

No comments:

Post a Comment