No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday 21 August 2012

መለስ/ለገሰ/ ዜናዊ - የእናት ጡት ነካሽ - አፈርንብህ

1. “አፈርንብህ” - በትግል ወቅት ከትግራይ ሕዝብ ድጋፍ ብታጣ የሃውዜንን ሕዝብ በደርግ ጀቶች ገበያ ላይ እንዲደበደብ በማሴርህ፣
2. “አፈርንብህ” - በትግል ወቅት በረሃብ ለተጎዳ ወገን የመጣውን የምግብ እርዳታ ዘርፈህ በመሸጥህ፣
3. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን የዘመናት ታሪክ ጨፈላልቀህ የ 100 አመት ታሪክ በማድረገህ፣
4. “አፈርንብህ” - የአገርህን ባንዲራ ጨርቅ ነው ብለህ በማንቋሸሽህ፣
5. “አፈርንብህ” - የጣሊያን ባንዳነት ውርስህን እውን ለማድረግ ለ UN የተማጽኖ ደብዳቤ ጽፈህ ኤርትራን በማስገንጠልህ ፣
6. “አፈርንብህ” - አገርህን ወደብ አልባ በማድረግ ህዝብህን ለኑሮ ውድነት በመዳረግህ፣
7. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን የነዳጅ ማጣሪያ አስገንጥለህ ለነዳጅና ትራንስፖርት ውድነት በመዳረግህ፣


8. “አፈርንብህ” - የአገርህን ድንበር ቆርሰህ ለሱዳን ገጸ በረከት የሰጠህ የመጀመሪያው ከሃዲ መሪ በመሆንህ፣
9. “አፈርንብህ” - የአገራችንን ቡና እና ቆዳ ለኤርትራ በፎርጅድ ብር አስለውጠህ አንድ እግር ቡና የሌላትን ኤርትራን ከአፍሪካ አንደኛ ኤክስፖርተር እንድትሆን በማድረግህ፣
10. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን ሰራዊት በነፍሰ ገዳይ የዘረኛ የጎሳ መሪዎች ቡድን በመምራትህ፣
11. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን ፖሊስ የአንተ ታዛዥ ባሪያና የአንድ ጎሳ የወሮበላ ቡድን አገልጋይ በማድረግህ፣
12. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን ደህንነት የአንድ ጎሳ ቡድን ስብስብ እና የቋንጃ ቆራጮች መሰበሰቢያ በማድርገህ፣
13. “አፈርንብህ” - በጎንደር: በደሴ; በአዲስ አባባ: በአዋሳ: በጋምቤላ; በበደኖ በአርባ ጉጉ ንጹሃንን በግፍ በማስጨፍጨፍህና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸምህ፣
14. “አፈርንብህ” - አገሪቱን እና ሕዝቦቿን በጎሳና በሃይማኖት ለመከፋፈል በመጣርህና የአክሱም ሃውልት ለወላይታ ለኦሮሞ ምኑ ነው ብለህ ኢትዮጵያዊነታቸውን በመፋቅህ፣
15. “አፈርንብህ” - የኢትዮጵያ ሕዝብ ሴራህን ሲነቃብህና አንድ ሲሆንብህ ያንቋሸሽካትን ባንዲራ አንስተህ - የባንዲራ ቀን፣ የጎሳ መርዝ ነዝተህ - የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ስታውጅ፣ የሃይማኖት ጥላቻ ነዝተህ - መቻቻልን ስትሰብክ ባለማፈርህ፣
16. “አፈርንብህ” - 20 አመት ሙሉ የሕዝብ ፍቅርና ክብር አጥተህ በስልጣን በመቆየትህ፣
17. “አፈርንብህ” - አንተ ስትወጣና ስትግባ በፍርሃት በአጋዚ ሰራዊት ተከብበህ ሕዝብህ ከየመንገዱ በመባረሩ፣
18. “አፈርንብህ” - የትግል ጓደኛህን የገ/መድህንን ሚስት ቀምተህ በማግባትህ፣
19. “አፈርንብህ” - ሃቀኛ የትግራይ ተወላጅ ታጋዮችን /እነ ሃየሎምንና ገ/መድህን የመሳሰሉትን/ በግፍ በማስገደልህ፣
20. “አፈርንብህ” - ደርግ ከጦርነት ጋር ያለምንም እርዳታ የሠራቸውን የልማት ተቋማት ጀነሬተሮችና መሣሪያዎች ነቃቅለህ ለኤርትራ አሳልፈህ በመስጠትህ፣
21. “አፈርንብህ” - የፖለቲካየ ደጋፊ ካልሆናችሁ በማለት ደሃ ገበሬዎችን ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘርና ብድር ከልክለህ በረሃብ በማሰቃየትህ፣
22. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን የልማት ተቋማት በፕራይቬታዜሽን ስም የአንተና የወሮበላ ድርጅታችሁ ሃብት ማካበቻ በማድረግህ፣
23. “አፈርንብህ” - የሕዝብ ሃብት በማግበስበስ ቀዳማይት እመቤት ሚስትህ ከዓለም ሃብታም ሴቶች ቁጥር ስትገባ ሃብቶቼ መጽሃፎቼ ብቻ ናቸው በማለትህ፣
24. “አፈርንብህ” - ነፃ ገበያ ሰባኪው መሪ የአገሪቱን ንግድ በአንድ ጎሳ ቡድን ኤምፓየር በሞኖፖል በመያዝህ፣
25. “አፈርንብህ” - የአንድ ጎሳ ቡድን በኮንትሮባንድ ንግድ እና ያለግብር እያስነገድክ ሰፊውን የንግድ ማኅበረሰብ በግብር እና በቀረጥ በማዳከምህ እና ኪራይ ሰብሳቢ በማለትህ፣
26. “አፈርንብህ” - ባድሜ ላይ ብዙ ሽህ ንጹሃን ዜጎችን ያለአግባብ አሳርደህ በአልጀርስ ፍርድ ቤት ያለይግባኝ ለኤርትራ እንዲሰጥ በማስደረግህ፣
27. “አፈርንብህ” - የዓለም ሙቀት መጨመር ተሟጋቹና የአፍሪካው አፈ-ቀላጤ ደርግ ያስጠበቀውን እና ያስለማውን ደን በማስጨፍጨፍህና በእሳት በማቃጠልህ - እሳት እናጥፋ ያሉትን የኦሮሞ ተወላጆች ከዩኒቨርስቲ በማባረርህ፣
28. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን የመንግሥት እርሻ ተቋማት አፈራረስህ ሕዝብህን ለከፍተኛ የእህል እጥረት በመዳረግህ፣
29. “አፈርንብህ” - በገበሬዎች የአምራቾች የኅብረት ሥራ ማኅበራት አድጎ የነበረውን ሜካናይዝድ እርሻ አውድመህ ወደ ኋላቀር የእርሻ ዘዴ በመመለስህ፣
30. “አፈርንብህ” - የጎንደርን ሰፋፊና ለም ወረዳዎች ቆርሰህ አማራውን አፈናቅለህ ለትግራይ ህዝብ መደለያ በመስጠትህና ወቅቱን ጠብቆ የሚፈነዳ አደገኛ የጥላቻ ቦምብ በመቅበርህ፣
31. “አፈርንብህ” - የአገሪቱን ስልጣን በሙሉ በአንተና ከአንድ ጎሳ ተወላጅ በሆኑ ወሮበሎች ስር በማድረገህ፣
32. “አፈርንብህ” - ለቁጥር አዳጋች የሆኑ ተለጣፊና አድርባይ የጎሳ ድርጅቶችን በመቀፍቀፈህ፣
33. “አፈርንብህ” - ያላንተ ጀግና የሌለ መሳዩ - ገለልተኛ ምርጫ ቦርድና ነፃ መገናኛ ብዙሃን ለማቋቋም ወኔ እና ድፍረት በማጣትህ፣
34. “አፈርንብህ” - በምርጫ 97 በዝረራ ስትሸነፍ ስልጣን ወይም ሞት ብለህ አሸናፊዎቹንና ደጋፊዎቹን አስረህ በማሰቃየትህ፣ ንጹሃን ዜጎችን በአጋዚ ጦር ጨፍጭፈህ እንደ ጋዳፊ ሕዝቤ ይወደኛል እያልክ እስከ አሁን በጠመንጃ ሃይል በመቆየትህ፣
35. “አፈርንብህ” - በምርጫ 97 ሃቀኞቹ የትግራይ ተወላጆች አልመርጥህ ሲሉ ከነሱ ድጋፍ ለማግኜት በማለት "አዲስ አበባ ገጀራ ተወደደ - ምክንያት ትግራዮችን ለመጨፍጨፍ" በማለት ሃላፊነት የጎደለው የኢንተርሃምዌይ ሽብር በመንዛትህ፣
36. “አፈርንብህ” - ሽብርተኛን አውጋዡ መሪ - በትግራይ ሆቴል ላይ ራስህ ፈንጅ አፈንድተህ ኦነግ ነው በማለትህ፣
37. “አፈርንብህ” - በአውቶቡስና በታክሲ ውስጥ ራስህ ቦምብ አጥማጅ፣ ራስህ ጠቋሚ፣ ራስህ ፈንጅ አምካኝ ሆነህ በሕዝብ ላይ ሽብር በመፍጠርህ፣
38. “አፈርንብህ” - ከአዲስ አበባ ያስወጣኸውን የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት በምርጫ 97 ስትሸነፍ በፍርሃት አዲስ አበባ እንዲመለሱ በማድረግህ፣
39. “አፈርንብህ” - ከምርጫ 97 ሽንፈት በኋላ የአዲስ አበባ አስተዳደርን ገቢ እና የአገሪቱን ጦር እንደ መንግሥቱ ኃይለማርያም በቁጥጥርህ ሥር በማዋልህ፣
40. “አፈርንብህ” - በምርጫ 97 የተሸነፍኩት በከተሜው ቅስቀሳ ነው በማለት ለሸማቹ ሕዝብ ገበሬው ምርቱን እንዳይሸጥ በማድረግ ሸማቹን ኅብረተሰብ በረሃብ በመቅጣትህ፣
41. “አፈርንብህ” -በአብዮታዊ ዴሞከራሲ ፍልስፍና ፍትሕ የሚያጣምሙ፣ ራሳቸው ከሳሽ፣ ራሳቸው መስካሪ፣ ራሳቸው ፈራጅ፣ የሆኑ ዳኞችና ፍርድ በቶች በመመስረትህ፣
42. “አፈርንብህ” - በሙስና የተካነ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በማቋቋምህ፣
43. “አፈርንብህ” - የህዝብ እንባ የሚያስፈስሱ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመመሥረትህ፣
44. “አፈርንብህ” - ሕዝባችን በረሃብና በችግር እየተሰቃየ ደርግ የሠራቸውንና ግጭት የማይነሳባቸውን ሰፋፊ የመስኖ መሬቶችና ተቋማት ለ20 ዓመታት ጦም አሳድረህ ስለአባይ ወንዝ ስብከት በመጀመርህ፣
45. “አፈርንብህ” - ዴሞክራሲ ሰባኪውና ቀይ ሽብርን አውጋዡ መሪ - ዴሞከራሲን እና ሰብአዊ መብቶችን በመርገጥህ፣ ሲቪክ ማህበራትን በመዝጋትህና ንጹሃንን በአደባባይ በአጋዚ መትረየስ በማስጨፍጨፍህ፣
46. “አፈርንብህ” - ቤተክርስቲያን ውስጥ መነኩሴ በጥይት የሚያስደበድብ፣ ቤተክርስቲያኔ አድኝኝ ያሉትን መጠጊያ ያጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አባርሮ ለአጋዚ ጥይት የሚዳርግ ታጋዳላይ ጳጳስ ከሲኖዶስ ሕግ ውጭ በመሾምህ፣
47. “አፈርንብህ” - በጎንደርና በልደታ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ በአጋዚ ጦርህ፣ በጅማ በሃረር በከሚሴ የኦርቶዶክስ ምዕመናንን በቅጥረኞችህ በማስጨፍጨፍህ፣
48. “አፈርንብህ” - ለጠንካራ ተቃዋሚ አልታደልንም ያልከውን ጉራ ረስተህ - ህዝብ የሚያፈቅራቸውን የነፃነት ታጋዮች በፍርሃት በማሰርህና በማሳደድህ፣ አንዳንዶቹንም ደብዛቸውን በማጥፋትህ፣
49. “አፈርንብህ” - የአገራችን ገበሬ የሚያርሰው መሬት አጥቶ ሰፊ የመስኖ ተቋም ለአረቦች በመሸጥህ፣
50. “አፈርንብህ” - ለቁጥር የሚታክቱ ወያኔያዊ የንግድ ኢምፓየሮች በመፍጠርህና ሌሎች ተፎካከሪዎችን በማጥፋትህ፣
51. “አፈርንብህ” - ጄሌዎችህን በኮንትሮባንድ ንግድ እና ያለ ግብር እያስነገድክ የንግዱን ማኅበረሰብ በግብር እና በዋጋ ተመን በማዳከምህ፣
52. “አፈርንብህ” - ለልማት የመጣ የሴፍቲ-ኔት (በእናንተ አጠራር ሶፍት-ኬክ) እርዳታን በፖለቲካ ስብሰባ በልተህ በመጨረስህ፣
53. “አፈርንብህ” - በድርቅና በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች የመጣን የምግብ እርዳታ ለድርጅት ደጋፊዎችህ ብቻ በአድሎ እንዲደርስ በማድረግህ፣
54. “አፈርንብህ” - በትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲህ ተወዳዳሪና ለሥራ ብቁ የማይሆኑ መሆን የማይችል አንድ ትውልድ በማፍራትህ፣ አዳዲስ ሥራ አጦችንና ርሃብተኞችን በየቀኑ በመፍጠርህ ሳታፍር አደገኛ ቦዘኔ ብለህ በመሰየምህ፣
55. “አፈርንብህ” - የትምህርት ፖሊሲህን የተቃወመውን የመምህራንን ማኅበር በማፈራረስህ፣ አመራሩን በማሰርህና አሰፋ ማሩን በጠራራ ፀሓይ አስገድለህ እንደገና ወደ ድሮው የትምህርት ፖሊሲ ልመለስ ስትል ባለማፈርህ፣
56. “አፈርንብህ” - ድንጋይ ማምረቻ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ከፍተህ ለባሪያዎችህ ዲግሪ በማደልህና ከፍተኛ ትምህርት የነበረውን ክብርና ደረጃ በማውረድህ፣
57. “አፈርንብህ” - በደናቁርት የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ምርት በማስገመት ለዓለም በሚተርፍ መጠን በቲቪ ምርት እያስመረትክ - በጎን የምግብ እርዳታ ስትለመን ባለማፈርህ፣
58. “አፈርንብህ” - ዴሞክራሲን ሰባኪው መሪ ነፃዎቹን ጋዜጦች ዘግተህ - ሰሚ ባጡ ሃሰተኛ ጋዜጠኞችና እውነት በማያውቁ ዜናዎች ሕዝብን በማደንቆርህ፣
59. “አፈርንብህ” - ልማታዊ ቢሮከራቶች፣ ልማታዊ ስጋ ቤቶች፣ የሥራ ቅጥር ጥገኛ ተማሪዎች፣ ወዘተ በመፍጠርህ፣
60. “አፈርንብህ” - አገሪቱን መጭ ብዙ ትውልዶች የማይከፍሉት የእዳ ጎተራ በማድረግህ፣
61. “አፈርንብህ” - በቤተሰብ ምጣኔ ሰበብ የአማራውንና የኦሮሞን ሕዝብ ቁጥር በመቀነስ ስውር የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀምህ፣
62. “አፈርንብህ” - የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት ነስተህ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ የነፃነት ታጋይ እሆናለሁ ስትል ባለማፈርህ፣
63. “አፈርንብህ” - የዓለም አምባገነኖችን የምርጫ ሪኮርድ በማሻሻል 99.96% በሆነ ውጤት ተመረጥኩ ስትል ባለማፈርህ፣
64. “አፈርንብህ” - አንተ ብቻ የምትናገርበት የደናቁርት ስብስብ ፓርላማ በመፍጠርህ፣
65. “አፈርንብህ” - ፓርላማ ውስጥና መግለጫ ስትሰጥ ለምትለቃቸው አስጸያፊና ስድ አደግ ባለጌ ስደቦችህ፣
66. “አፈርንብህ” - በአጠቃላይ በሙስና የደለበ፣ በአምባገነንነት ወገኑን የሚገዛ፣ በዘረኛነት ሕዝቡን የሚከፋፍል፣ በውሸት፣ የተካነ መንግሥት በመመሥረትህ፣
“አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ” - “አፈርንብህ





No comments:

Post a Comment