No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday 23 August 2012

ወያኔ ሃይማኖቶችን አብዮታዊ ዲሞክራሲ ካላጠመቅኩ እያለ ነው

በኢትዮጵያ ውስጥ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ማህበረሰብ መሃከል ለረጅም ዘመናት
ጸንቶ ያለ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል ባህል እንዳለ ዒትዮጵያውያን ያወቁት ብቻ
ሳይሆን እጅግ ብዙ የውጭ አገር ዜጎች የሚመሰክሩት እውነታ ነው፣ ነገር ግን በአቶ
መለሰ  ዜናዊ እና  በጥቂት የህወሃት ጭፍሮቻቸውና አሽከሮቻቸው  ለስልጣነ መንበራቸው
መቆያ ሲሉ ይህን ለአለም ህዝብ አርአያ የሚያደርገንን ማንነት ለማበላሸት መሞከር
ከጀመሩ አመታትን አስቆጥሯል ከነዚህም ውስጥ በከፊሉ   ለማንሳት ያህል
ጅማ ላይ ከ1997 ምርጫ በኌላ ወያኔ የደህንነት ሰራተኞቹን መሳሪያ አስታጥቆ እንዲሁም
 የመቅረጫ ካሜራ አስታጥቆ ምንም የማያውቀውን ህብረተሰብ በገጀራና በጥይት
ሲጨፈጭፉና ሲቀርጹ  ከቆዩ በሁዋላ በዲቪዲ ካሴቶች በማባዛት ለህዝቡ በአደባባይ
እንዲሸጥ በማድረግ የዒትዮጵያን ህዝብ ወደ ሃይማኖት ትርምስ ውስጥ ለመክተትና
በወቅቱ ወያኔ የነበረበትን የፖለቲካ ክስረት ለመሸፈንና የህዝቡን ትኩረት ለማሳት ያለመና
ነገር ግን ወያኔ ያልተሳካለት ስትራተጂ፥ በማስከተል ደግሞ በልደታ ቤተክርስቲያን

የተደረገውን ድብደባ እንዲሁም የምእመናኑን ክብር በሚያሳጣና በሚያዋርድ መልኩ
የመደብደብና የማሰቃየት ተግባር  ደግሞ ሌላው የወያኔ እኩይ ምግባር ሲሆን  ይህንንም
 ያደረጉት ደግሞ ቤተክርስቲያኗን በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊኛ በእጅ አዙር 
ለማስተዳደር ካላቸው ትማት ሲሆን ይህም በከፊልም ቢሆን አባሎቻቸውን በመሰግሰግ ተሳክቶላቸዋል   ፥
 አሁን ወቅታዊ የሆነው ደግሞ  ሙስሊሙን ህብረተሰብ እርስ ለመከፋፈልና ለማጋጨት  እንዲሁም አዲስ ሃይማኖት ለመጫን ወይም በግድ እንዲቀበሉ ለማድረግ  ከጀመረ እነሆ ስምንት ወራት ተቆጥሯል ህዝበ ሙስሊሙም ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሀይማኖታዊ መብቱን እያሰማ ሲሆን ነገር ግን ወያኔ እንደተለመደው አወሊያ ቅጥር ጊቢ ድረስ በመሄድ በእለቱ የሰደቃ  ወይንም  ምስኪኖችን
የማብላት ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት  የፌዴራል ፖሊሶች ያደረሱትን በአስለቃሽ አፍኖ
ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብና በማሰቃየት   ለምስኪኖች የተዘጋጀውን ምግብ  ከመውሰድ ባለፈ ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመብት ጥያቄዎቹን እንዲያቀርቡለት የወከላቸውን ሰዎች ለመወንጀል የታሰበ ሴራ ነበር ይኧውም ስጋና ሽንኩርት ሲከትፉ የነበሩትን ሰዎች ቢላዎቹን ለሽብር ሊጠቀሙበት እንደነበረ እንዲናገሩ በማስገደድ የቪዲዮ ቀረፃ አካሂደዋል በቀጣዮቹ ጊዜያትም በማስገደድ
የቀዱትን ቪድዮ ወያኔ በለመደው የማቀነባበር ቴክኒክ ተጠቅመው በተሳሳተ ኢንፎርሜሽን ህዝቡን
 ማደናገር ከዚያም በባሰ ህዝበ  ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻከር መመኘት በቅርቡ የምንተብቀው የአዲሱ ድራማ ግብ ነው፥
ምንም እንኳን የማይሳካ ይዘትና ግብ ቢኖረውም ሌሎች ዘዴዎችን ይዞ ብቅ ብሏል ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል
1 ኛ= የአህባሽን አስተምህሮት ህዝቡ በግድ ሄዶ እንዲማር ማስገደድ ፣ አጃዒብ እኮ ነው   ሰዎች አህባሽ የሚሉት እምነት እምነታቸ
        በአላህ ሳይሆን በጅብሪል ነው ፣ ይህ ማለት ደግሞ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወይም 99 ፕርሰንት የሚያምነው
        በአላህ ነው፣
2 ኛ'= ከአህባሽ ትምህርት ሌላ ደግሞ ልማታዊነት ወይም የወያኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ጠበል በግድ ማጥመቅ፣
3 ኛ= ወያኔ በተቆጣጠራቸው ሚዲያዎች በመጠቀም የሙስሊሙን  መሰረታዊ የህገ መንግስት ጥያቄዎች  ሆን ብሎ ሃላፊነት
        በጎደለው ሁኔታ የሙስሊም መንግስት እንመሰርታለን የሚል ጥያቄ ነው የጠየቁት በማለት የለመደው የውሸት ፕሮፖጋንዳ
        እያሰራጨ ይገኛል  ፣ ሥለዚህም የዒትዮጵያ ህዝቦች ሆይይህንን አስቀድመን  በመረዳት እንደተለመደውእራሳችንንም ሆነ ወገኖቻችንን ከማንኛውም
        መታለል ወይም መጭበርበር እንጠብቅ ለዚህም ይረዳን ዘንድ ይህንን እና ይህንን መሰል የህዝቡን ሰላም እና አብሮ የመኖር
        ባህል የሚያጠነክሩ ከመሸርሸር የሚጠብቁ መልእክቶችን ላልሰሙ  ወገኖቻችን   ጊዜው ባፈራቸው  እንደ ፌስቡክ ፣ሜይል
        የመሳሰሉትን በመጠቀም በማስተላለፍ ሃላፊነታችንና ግዴታችንንም እንወጣ፣
ከኤፍሬም ዳባ ከኖርዌይ

No comments:

Post a Comment