ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አዲሱ መንግስትና ነባር ታጋዮች ፣ በአቶ መለስ ሞት የህዝብ ድጋፍ ለማሳበሰብና የተዳከመውንና በቋፍ ላይ የሚገኘውን ፓርቲያቸውን ነፍስ ለማዘራት እየተሯሯጡ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮቻችን ገልጠዋል።
የአብአዴን ኢህአዴግ የአመራር አባል የሆነው ምንጫችን እንደገለጠው፣ ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ጭንቅት ውስጥ ይገኛል። በአንድ በኩል “የታጋይ መለስ የሽኝት ኮሚቴ” የሚል ኮሚቴ በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች በማቋቋም ህዝቡ ለድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ፣ በሰልፉም ለኢህአዴግ ያለውን ታማኝነት እንዲገልጥ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መላ የደህንነት አባላቱን በህዝቡ ውስጥ በመበተን የህዝቡን ስሜት ለማወቅ ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው።
አብዛኛው የኢህአዴግ ታጋይ በከፍተኛ ሁኔታ በመደናገጡ ነው አመራሩ
በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዲገባ ያደረገው እንደምንጫችን መረጃ። በዚህም መሰረት ድርጅቱ በአቶ መለስ አስከሬን
የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘትና የራሱን ስልጣን ለማመቻቸት ደፋ ቀና እያለ ነው።
በተለያዩ ወረዳዎች ለጓድ መለስ ዜናዊ ሽኝት በሚል ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ፣ ሀዘኑን በእንባ እንዲገለጥ እየተደረገ ነው። ሀዘኑን በይፋ ያልገለጠ ሰው እንደተቃዋሚ ተቆጥሮ ጉዳት እንደሚደርስበት ነው ምንጫችን የገለጠው።
ምንጫችን ” እነ አቶ በረከት ስምኦንና መሰል የህወሀት ባልደረቦቻቸው ስልጣናቸውን ለማደላደል፣ በአቶ መለስ ሞት ሲነግዱ እየታዘብን ነው” በማለት ገልጠዋል።
ምንጮቻችን እንደጠቆሙት ኢህአዴግ በሞት በተለዩት ሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በቀጣዩ መስከረም ወር 2005 ዓ.ም 9ነኛ ጉባዔውን በማካሔድ ግንባሩን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት በሊቀመንበር የሚመራ ሰው ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የግንባሩ ሊቀመንበርነት ሹመት የሚያገኘው ሰው ሹመቱ በፓርላማ ቀርቦ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡እንደምንጮቻችን ገለጻ አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ሆነው የሚቀጥሉበት ዕድል ጠባብ መሆኑን ጠቁሞ ምናልባት የሚሾመው አዲስ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያምን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ቦታቸው ያስቀጥላቸዋል ተብሎ ተገምቶአል፡፡
አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የካቢኔ አባላትን በድጋሚ በመሾም ሥራውን የሚቀጥል ሲሆን ከነባሮቹ ሚኒስትሮች በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የማይቀጥሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ከወዲሁ ተገምቷል፡፡በተለይ የአቶ መለስ ቀኝ እጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሚኒስትሮች በሙሉ በአዲስ ሊተኩ ይችላሉ ተብሎአል፡፡
የግንባሩ ስብሰባ ከመካሄዱ አስቀድሞ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ማለትም ህወሃት፣ብአዴን፣ኦህዴድ፣ደኢህዴን በተናጠል ስብሰባ በማድረግ የማዕከላዊ እና የስራአስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ የሚያካሄዱ ሲሆን ለግንባሩ ሊቀመንበርነት ቦታም እያንዳንዳቸው ዕጩ አቅርበው ለግንባሩ 9ነኛው ድርጅታዊ ጉባዔ አቅርበው በውድድር ያስመርጣሉ ተብሎ
ኢሳት ዜና:-አዲሱ መንግስትና ነባር ታጋዮች ፣ በአቶ መለስ ሞት የህዝብ ድጋፍ ለማሳበሰብና የተዳከመውንና በቋፍ ላይ የሚገኘውን ፓርቲያቸውን ነፍስ ለማዘራት እየተሯሯጡ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮቻችን ገልጠዋል።
የአብአዴን ኢህአዴግ የአመራር አባል የሆነው ምንጫችን እንደገለጠው፣ ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ጭንቅት ውስጥ ይገኛል። በአንድ በኩል “የታጋይ መለስ የሽኝት ኮሚቴ” የሚል ኮሚቴ በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች በማቋቋም ህዝቡ ለድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ፣ በሰልፉም ለኢህአዴግ ያለውን ታማኝነት እንዲገልጥ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መላ የደህንነት አባላቱን በህዝቡ ውስጥ በመበተን የህዝቡን ስሜት ለማወቅ ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው።
በተለያዩ ወረዳዎች ለጓድ መለስ ዜናዊ ሽኝት በሚል ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ፣ ሀዘኑን በእንባ እንዲገለጥ እየተደረገ ነው። ሀዘኑን በይፋ ያልገለጠ ሰው እንደተቃዋሚ ተቆጥሮ ጉዳት እንደሚደርስበት ነው ምንጫችን የገለጠው።
ምንጫችን ” እነ አቶ በረከት ስምኦንና መሰል የህወሀት ባልደረቦቻቸው ስልጣናቸውን ለማደላደል፣ በአቶ መለስ ሞት ሲነግዱ እየታዘብን ነው” በማለት ገልጠዋል።
ምንጮቻችን እንደጠቆሙት ኢህአዴግ በሞት በተለዩት ሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ምትክ በቀጣዩ መስከረም ወር 2005 ዓ.ም 9ነኛ ጉባዔውን በማካሔድ ግንባሩን ለቀጣይ ሁለት ዓመታት በሊቀመንበር የሚመራ ሰው ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የግንባሩ ሊቀመንበርነት ሹመት የሚያገኘው ሰው ሹመቱ በፓርላማ ቀርቦ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሆኖ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡እንደምንጮቻችን ገለጻ አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ሆነው የሚቀጥሉበት ዕድል ጠባብ መሆኑን ጠቁሞ ምናልባት የሚሾመው አዲስ ጠ/ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያምን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ቦታቸው ያስቀጥላቸዋል ተብሎ ተገምቶአል፡፡
አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የካቢኔ አባላትን በድጋሚ በመሾም ሥራውን የሚቀጥል ሲሆን ከነባሮቹ ሚኒስትሮች በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የማይቀጥሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ከወዲሁ ተገምቷል፡፡በተለይ የአቶ መለስ ቀኝ እጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሚኒስትሮች በሙሉ በአዲስ ሊተኩ ይችላሉ ተብሎአል፡፡
የግንባሩ ስብሰባ ከመካሄዱ አስቀድሞ የግንባሩ አባል ድርጅቶች ማለትም ህወሃት፣ብአዴን፣ኦህዴድ፣ደኢህዴን በተናጠል ስብሰባ በማድረግ የማዕከላዊ እና የስራአስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ የሚያካሄዱ ሲሆን ለግንባሩ ሊቀመንበርነት ቦታም እያንዳንዳቸው ዕጩ አቅርበው ለግንባሩ 9ነኛው ድርጅታዊ ጉባዔ አቅርበው በውድድር ያስመርጣሉ ተብሎ
No comments:
Post a Comment