No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday 30 August 2012

ውሸት ሲደጋግሙ እውነት የመሰላቸው ወያኔዎች

ጌዲዮን ደሳለኝ ከኖርዎይ
Forcing people to mourn Meles Zenawi's death in Ethiopiaይገርማል እኔ በበኩሌ ይኀው ነፍስ ካወኩ ጀምሮ ከወያኔ እውነት የሰማሁበት ቀን አንድም ግዜ ትዝ አይለኝም፥ ውሸታቸው ለራሳቸውም እውነት እስኪመስላቸው ድረስ ነው፥፥
ታድያ ሌላውም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደነሱ ውሸትን እውነት አድርጎ እንዲቀበል ይፈልጋሉ፥ እስከማስገደድ ድረስ፥፥
ሰዎችን የተለያየ የውሸት ማስረጃ እያቀረቡ ማሰር ከመዘውተሩ ብዛት እውነት እየሆነ ማቷል፥
ሲሳይ አጌና ለእትም ያቀረበው ያቃሊቲው መንግስት የሚለው መፅሃፉ ለዚህ በጣም ብዙ ማስረጃ ይሰጠናል፥
በመጀመርያ ለሲሳይ ትልቅ ምስጋና ይቅረብልኝ፥፥
የወያኔ መንግስት ምን ያህል ለተንኮል ቆርጦ እንደተነሳ፥ስልጣኑን ላለማጣት የት ድረስ እንደሚቆፍር ለመረዳት አያዳግትም፥ የሚያቀነባብሩአቸው ውሸቶች ደሞ ከትልቅ ውሸት እስከ ተራ ውሸት ሊሆን ይችላል፥ ይሄ ለወያኔዎች Normal ነው፥፥
የሚገርመው ግን ህዝቡ ሊጠረጥር ይችላል ብለው እንኩአን አለማፈራቸው ነው፥፥
እስቲ ወደሲሳይ አጌና መፅሃፍ መለስ ላርጋችውና  ገፅ 372 ተመልከቱ፥

ከ 1997 ምርጫ በሁዋላ በተከሰተው ብጥብጥ ምክንያት ስለተከሰ ፥ሰለተጎዱት፥ስለተገደሉት፥ስለታሰሩት ሰዎች የሚያጣራ 10 አባላት ያሉት ኮሚሽን ተቁዋቁሞ ነበር፥ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የነበሩት ዳኛ ፍሬህይዎት ሳሙኤል ነገሩ ውስብስብ ሲልባቸው እንዲህ አይነት ማጭበርበር መንግስትን አይመጥንም ብለው እርፍ፥፥
ገፅ 363 ስንመለከት ደሞ 
ይህን ሪፖርት መቀየር ህሊናዬ ስላልተቀበለው ከሃገሬ ተሰደድኩ ያሉት ደሞ ምክትል ሰብሳቢ የነበሩት ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ሲሆኑ ዋና ሰብሳቢው አቶ ፍሬህይዎት ከሃገር ከወጡ በሁአላ በውና ሰብሳቢነት ካገለገሉ በሁዋላ እሳቸውም በደረሰባቸው ጫና ሪፖርቱን ይዘው ከሃገር ለመሰደድ በቅተዋል፥፥
እረ ስንቱን መዘርዘር ይቻላል፥
መፅሃፉ ላይ ብዙ መረጃዎች ቀርበዋል በጣምም ጠቃሚዎች ናቸው በዚህ አጋጣሚ መነበብ ያለበት መፅሃፍ ነው፥
ለነገሩ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ከሰሩዋቸው ሴራዎች ትንሽዋን ላንሳ ብዬ ነው እንጂ ተነግሮ አያልቅም፥
ብቻ ምን አለፋችው የወያኔ ውሸት ይሄ ነው ተብሎ አያልቅም ከላይ እንዳልኩት ከትልቅ ውሸት እስከ ተራ ውሸት፥
ሰሞኑን ደሞ የአምባገነኑ መለስ መሞት ውሾቻቸውን ድምብርብራቸውን ነው ያጠፋው፥ ብዙ አስገራሚ የሃዘን አይነት አስተውለናል፥ ምናልባትም በአለም ትልቁ የተቀነባበረ የለቅሶ ስርአት ልለው እችላለው፥ አላማው ባይገባኝም ያሳፍራል፥ የገረመኝ ደሞ ካሳንችስ አካባቢ የተወሰኑ ጭፈራ ቤቶች ሙዚቃ ከፈታችው ተብለው ታሸጉ ሲባል መስማቴ፥
ብቻ ይገርማል የተለያዩ ሰዎች አስተያየትም ግርም ይላል፥ የጎዳና ተዳዳሪ ነኝ የሚለው እያለቀሰ መለስ እኮ ለኛ ብዙ እቅድ ነበረው፥ከአሁን በሁአላ safe አደለንም ሲል ተደምጧል፥ አንድ ግለሰብ ደሞ ምነው እሱ ኖሮ ዕኔ በሞትኩ ሲል በetv.  ታይቷል፥ባዶ ሬሳ ሳጥን ፊት ለፊት ተንበርክኮም ሲሰግድ የታዩም አልጠፉም፥  የአዜብማ በቃ ይሄን ጉድ የአለም መንግስት ይመልከትልኝ የምትል ነው የምትመስለው፥፥
እኔ ኢትዮጵያዊ ሰው ለሚያመልከው አምላክ ሲሰግድ ነው የማቀው፥፥ ለጥቅም እንኳን ቢሆን አምላክን ትቶ ለሰው ለዛውም የኢትዮጵያን ህዝብ ለ 21 አመት ለገደለ፥ ላሰረ፥ላሰደደ፣ ያገርን ጥቅም ለሸጠ ከሃዲ መስገድ በምድርም በሰማይም ገሃነም ያስገባል፥፥
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

No comments:

Post a Comment