No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Wednesday 17 July 2013

“የአዲስ አበባ መሪ ፕላን የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅና ለማፈናቀል የታቀደ ሴራ ነው” ኦፌኮ

ኦህዴድ በአዲስ አበባ መሪ ፕላን ላይ
የአመራሩን ብዥታ ሊያጠራ ነው
“የአዲስ አበባ መሪ ፕላን
የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅና ለማፈናቀል የታቀደ ሴራ ነው”
ኦፌኮ
 
በዘሪሁን ሙሉጌታ
የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ከአዲስ አበባ መሪ ፕላን ጋር በተያያዘ በዙሪያዋ ካሉ ከተሞች ጋር በቀጣይ ሊኖር ስለሚችለው ግንኙነት በተመለከተ የድርጅቱ አመራርን ብዥታ ለማጥራት እንደሚንቀሳቀስ አስታወቀ። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በበኩሉ የአዲስ አበባ መሪ ፕላን የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅና ለማፈናቀል የታቀደ ሴራ ነው ብሏል።
ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት የአዲስ አበባ የኢኮኖሚ ግለት ሀገሪቱ እንደ አቅጣጫ ካስቀመጠችው የመካከለኛ ገቢ ደረጃ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመመደብ የሚደረገው ጥረት አመላካች በመሆኑ በከተማዋ ያለው የኢኮኖሚ ሙቀት ለአጎራባች ከተሞች የሚጠቅምበት ሁኔታ መፈጠር ስላለበት፤ በመዲናዋ ዙሪያ ያሉ ከተሞች አስተዳደራዊ ቅርፃቸው ሳይለወጥ ከአዲስ አበባ ጋር ተመጋግበው የሚሰሩበትን አቅጣጫ በተመለከተ ለከፍተኛ አመራሮቹ ማብራሪያ በመስጠት የጠራ አቅጣጫ ለመያዝ ታቅዷል።
በቅርቡ የተሾሙት አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ እና የኦሮምያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ ጉዳዩን በበላይነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ምንጫችን ጠቅሷል።
እስካሁን ጉዳዩ በጥሬው ያለ በመሆኑ የባለሙያዎችን ጥናት መነሻ በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ያለውን የአመለካከት ማጥራት መታሰቡን ከምንጫችን ገለፃ መረዳት ተችሏል።
“በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የኦሮምያ ልዩ ዞን ውስጥ ያሉ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ሊደፈቁ ነው” የሚለው አስተያየት በሰፊው እየተነዛ በአመራሩና በኅብረተሰቡ መካከል ብዥታ መፈጠሩ ስለታመነበት አመራሩን ተገቢውን መረጃ ከጨበጠ በኋላ ወደ ሕዝቡ እንደሚወርድ ምንጫችን ጠቁሟል።
“ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የግዴታ ተያይዘን ማደግ አለብን” በሚለው መርህ መሠረት እንደ ሀገር የመንግስት እንደ ድርጅት ደግሞ የኦህዴድ ድል በመሆኑ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ለራሳቸው ዓላማ ሲሉ ሁኔታውን እያራገቡት መሆኑ ለብዥታው መፈጠር አስተዋፅኦ ማድረጉ ታምኖበታል። ለዚህም ሲባል የማጥራት ስራውን በቅርቡ ይከናወናል ሲል ምንጫችን አመልክቷል።
በተያያዘ በዶ/ር መረራ ጉዲና የሚመራውና በቅርቡ የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረንስ (ኦህኮ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን)ን የተዋሃደበት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) “የአዲስ አበባ መሪ ፕላን የኦሮሞን መሬት ለመንጠቅና ለማፈናቀል የታቀደ ሴራ ነው” ሲል መሪ ፕላኑን የሚቃወም መግለጫ ሰሞኑን አውጥቷል። ፓርቲው በመግለጫው በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን በልማት ስም ከኦሮምያ ወደ አዲስ አበባ ክልል በማዘዋወር መሬቱን ላለመሸጥ ስለመታቀዱ ምንም ዋስትና የለም ብሏል። በተጨማሪም በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 49 ቁጥር 5 ላይ የኦሮምያ ክልለ ለአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ጥቅም ሊያገኝ እንደሚገባ እና ይህም ጥቅሙ በሕግ እንደሚከበር ቢጠቅስም ሕገ-መንግስቱ መጣሱን የማያሳይ ነው ብሏል።
ስለሆነም በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች በልማት ስም ወደ አዲስ አበባ መታጠፋቸው ቆሞ በኦሮምያ ስም መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው መጋቢ ከተሞች ሆነው በነፃነት ማደግ እንዳለባቸው ኦፌኮ በመግለጫው አሳስቧል
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 410 ሐምሌ 10/2005
 

No comments:

Post a Comment