No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday 6 June 2013

ኢትዮጵያ ለግብፅ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

EMF: በአባይ ግድብ የተነሳ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ፍጥጫ ከዚህ በፊት ከነበረው ሁኔታ በተለየ መልኩ ውጥረት የነገሰ ይመስላል። በተለይም የግብፁ ፕሬዘዳንት “ቅንጣት ውሃ አናስነካም!” ከማለት አልፈው ካቢኔያቸውውን ሰብስበው ሲነጋገሩ በቀጥታ በቴሌቪዥን ሲተላለፍ፤ ኢትዮጵያን ለመምታት የተለያዩ ሃሳቦች ሲያቀርቡ ከታየ በኋላ፤ የግብፅ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በተለይም ሰሜን ሱዳን እና ግብፅ የናይል ወንዝን አስመልክቶ የሁለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ስላላቸው፤ ሱዳን ለግብፅ በመወገን… መንደርደሪያ ከሰጠቻት ግብፅ ከሳምንት በፊት የገዛቻቸውን ኤፍ 16 ጄቶች ልትጠቀም ትችላለች የሚል ስጋት አለ።
F 16 ተዋጊ ጄቶችን በመጠቀም ግብፅ በአለም 4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከነበራት 240 ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በተጨማሪ ነው - 20 ጄቶችን የገዛችው። እንዲህ አይነት ጄቶች ደግሞ በፍጥነትም ሆነ ረዥም ርቀት በመሄድ እና በማናቸውም አቅጣጫና ማዕዘን መገለባበጥ የሚችሉ ናቸው።
F 16 ተዋጊ ጄቶችን በመጠቀም ግብፅ በአለም 4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ከነበራት 240 ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በተጨማሪ ነው – 20 ጄቶችን የገዛችው። እንዲህ አይነት ጄቶች ደግሞ በፍጥነትም ሆነ ረዥም ርቀት በመሄድ እና በማናቸውም አቅጣጫና ማዕዘን መገለባበጥ የሚችሉ ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ለግብፅ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከመላክ አልፋ፤ በኢትዮጵያ የሚገኘው የግብፅ አምባሳደር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ተገኝቶ የአገሩን የግብፅን አቋም እንዲያስረዳ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተልኮለታል። እንግዲህ አምባሳደሩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የሰጣቸውን ማሳሰቢያ ተቀብለው ቃላቸውን ይሰጣሉ ወይስ ጥሪውን ንቀው ይተዉታል?  የአምባሳደሩ ምላሽ ብዙ ነገር ሊለውጥ ይችላልና መጨረሻውን  አብረን እንከታተላለን።
EMF

No comments:

Post a Comment