No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday 23 April 2013

ግብጽ የውሃ ጦርነት ለማድረግ ሃይል እያደራጀች ናት።


በአሜሪካ ከፍተኛ እገዛ የሚደረግለት የግብጽ ጦር ሃይል የናይል ወንዝን ለመቆጣጠር ሲባል መጠሪያው የዉሃ ጦርነት ሊባል የሚችል ጸብ አጫሪ ተግባር ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ይገኛል። የምዕራብ የደህንነት ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ የጦር ክፍሉ የሃገሪቱን ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ሞርሲን ማንኛውንም የናይል ወንዝ ፍሰት የሚያስተጓጉል ተግባር ለመቀልበስ ጦሩ የሚደራጅበትን ፈቃድ ጠይቋል።
 አካላቱ የሚሉት የጦር ሃይሉ ከኢትዮጵያ ጋር ከፍተኛ ጸብ ሊፈጠር እንደሚችል እና ያም የግብጽን እና የሱዳንን የውሃ ፍጆታ አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት ይሆናል ያለው ሜንልነው።
”ለግብጽ የጦር ሃይል እና መንግስት ይህ ምናልባትም የዛሬው ትልቁ እና አንገብጋቢ የጸጥታ ጉዳይ ነው” ብለዋል ምንጮቹ።

ምንጮቹም አክለው ሞርሲ ከሱዳን ጋር የጦር ሃይል ውህደት በማድረግ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ የምታደርገውን የግድብ ግንባታ ለማስቆም በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ሲሉም ለኢትዮጵያ የአደጋ ማስጠንቀቂያ ሊባል የሚችል ሃሳብ ሰንዝረዋል። የህዳሴ ግድቡ ወደ 84 ቢሊዮን ኪዩቢክ ዉሃ በማስቀረት ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ በቂ የሆነ ክምችት ለማድረግ ታስቦበት እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል።
”የጦር ሃይሉ በቅርቡ የአየር ጥቃት ለማድረግ ትእዛዝ የሚደረግበትን መንገድ እና የግድቡን ግንባታ ለማስቆም ወይም የኢትዮጵያዋን ልዕልት በቀላሉ ለማውደም እየተዘጋጀ ይገኛል” ይላል ይህ ምንጭ።
የዉሃውን ስልሳ በመቶ የምትጠቀመው ግብጽ የቀድሞውን ያለፈ ”መብት” ለማስጠበቅ የሙጥኝ ማለቷ የማያለሰልስ አቋም እየሆነ መጥቷል።
በማስቀጠልም ምንጮቹ የሞርሲ መንግስት ለአዲስ አበባ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ግምታቸውን አስታውቀዋል። ይህም ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው በመጪው የግንቦት ወር መገባደጃ አከባቢ በግብጽ-ሱዳን-ኢትዮጵያ ሶስትዮሽ የቴክኒካል ቀጣይ ስብሰባ ነው ተብሏልም።
ናይል በአስር ሃገራት የጋራ ሃብትነት ይታወቃል።
”ኢትዮጵያ ለግድቡ ተግባር የሚጠቅማትን  ወይም የሚሆናትን ዉሃ ብቻ ማጠራቀሟን ማረጋገጥ የሚቻልባቸው እርምጃዎች መወሰዳቸው ግድ ነው ይህም ከግብጽ ፈቃድ እና መስመር ጋር የተስማማ መሆን አለበት” ሲሉ የተደመጡት ደግሞ የዛሬ አራት ቀን በግብጽ የመንግስት ዜና አውታር አል አህራም ዴይሊ ንግግር ያደረጉት የሃገሪቱ ባለስልጣን ናቸው።
የዜና ምንጮች ይህን ያሉት የግብጽ የጦር ሃይል  ከዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ኤፍ-አስራ ስድስት ብሎክ ሃምሳ ሁለት የተባለ ለብዙ ተግባራት የሚውል የጦር አውሮፕላን መረከቧን እንደ ዋቢ መረጃ በመጥቀስ ነው። በማስቀጠል እንዳሉትም  በአ.አ 2013 ወደ ሃያ የሚሆን ቁጥር ያላቸው መሰል የጦር አውሮፕላኖች የሚቀበለው የግብጽ የአየር ሃይል በሰጠው መረጃ የቅርብ ጊዜው ኤፍ አስራ ስድስት ቫሪያንት ተቀጥያ የነዳጅ መያዣዎች ያሉት በመሆኑ በኢትዮጵያዋ ልዕልት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ያስችለናል ሲል አስታውቋል።
የህዳሴው ግድብ በየዓመቱ ከአስራ ስምንት እስከ ሃያ ሚሊዮን ኪዩቢክ ዉሃ እንድናጣ ያደርገናል ስትል ግብጽ አስታውቃለች። ምንጮቹ እንደሚሉትም ግብጽ ለዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ግድብ ፕሮጀክት አደገኛነት ማሳሰቧን ገልጸዋል።
”በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ ድርሻ በጣም ወሳኝ ነው ምክንያቱም በኢትዮጵያ ሊደረግ የሚችለው ጥቃት ላይ ምርቷ የሆነው የጦር አውሮፕላን ግልጋሎት ላይ ሊውል ታቅዷል እና ነው” ያለው ይህ ምንጭ ነው።
ይህ ዜና የተገዛ በመሆኑ ማሰራጨት የሚፈልግ ከዝግጅት ክፍላችን ፈቃድ መውሰድ አለበት።
wolaita.com

No comments:

Post a Comment