No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Sunday 21 April 2013

ባንባሲ ያለው የህወሓት ካድሬ አካባቢውን ከአማራ ሳላፀዳ ዕረፍት የለኝም፤ እያለ በግልጽ ይፎክራል


ህዝብ እየተፈናቀለ ያለው ከፌዴራል መንግስት በሚሰጥ ትዕዛዝ መሆኑን መኢአድ አሳወቀ
“የአገሪቱ ህዝብ በተለይ የአማራው ህዝብ  ከሥራውና ከመኖሪያ እየተፈናቀለ ያለው በክልል ወይም በወረዳ ባለሥልጣናት ውሳኔ ሳይሆን ከፌዴራል መንግስት በሚሰጥ ትዕዛዝ ነው፡፡” ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ አስታወቀ፡፡ መኢአድ ይህንን ያሳወቀው ባለፈው አርብ ረፋዱ ላይ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ethiopia distract
ፓርቲው ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት በመሄድ የኢትዮጵያ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ እየተዘሰጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡ መኢአድ “በአማራ እና በአፋር ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የአምባገነኖች እና ዘረኞች ጥቃት እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን፡ ፡” በሚል ርዕስ ባለ አራት ገጽ መግለጫ  አውጥቷል፡፡ መግለጫው በመግቢያው ላይ “ኢህአዴግ የምኒሊክ ቤተመንግስትን ከተቆጣጠረ ጊዜ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ዘመቻ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

በበደኖ፣በአርባጉጉ፣በአረካና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ጭፍጨፋ ፈጽሟል፡፡ ጥቃቱ ለ22 አመት ቀጥሎ ዛሬም በጉራፈርዳና በአፋርና በቤኒሻንጉል የዘር ማጥፋት ሥራ እየተሰራ ነው፡፡

በማለት ይዘረዝራል፡፡ መግለጫው በመጨረሻም “እንዲመለሱ ለተደረጉ ወገኖች ተገቢው የህግ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ ለደረሰባቸው አካላዊና ሞራላዊ ጥቃት ተገቢው ካሳ እንዲከፍል፣ ድርጊቱን የፈፀሙትን ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ጥላቻንና ክፍፍልን የሚያራግቡ ኃይሎች ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው ባስቸኳይ እንዲታቀቡ፣ ሕዝብን በዘርና በኃይማኖት ከፋፍሎ በማፋጀት ሥልጣንን ለማራዘም የሚደረገው ጥረት ላለፉት 21 ዓመታት ደም ያፋሰሰ በመሆኑ ባስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን ብሏል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ፕሬዘዳንት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፣ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የቀጠና አደራጅ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ናቸው ፡፡ መግለጫው በንባብ ከተሰማ በኃላ ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቆዎች መልስ ተሰቷል፡፡ ኢ/ር ኃይሉ በሰጡት መልስ “ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉት ሰዎች በወረዳ ባለሥልጣናት እንደሆነ በመግለጽ ስህተቱ ታርሞ ተፈናቃዮች ወደ ሥፍራቸው ተመልሰዋል ይባላል፡፡ ሐሰት ነው፡፡ የዘር ማጥፋት ዘመቻው የሚከናወነው የፌዴራል መንግስት በሚሰጠው ትእዛዝ መሆኑን መረጃ አለን፡፡ ህዝቡን እየደበደበ እያሰረ የሚያፈናቅለው ልዩ ኃይል የሚባለው ጦር ነው፡፡ ልዩ ኃይልን የሚያዘው ደግሞ ፌዴራል መንግስት ነው፡፡ ተፈናቃዮች ፍኖተ ሠላም በሠፈሩበት ወቅት ውሃ አጥተው የወንዝ ውሃ ሲጠጡ ነበር፡ ፡ ብዙዎቹ በተቅማጥ እየተሰቃዩ ናቸው፡ ፡ አሁን ወስደው ያስገቧቸው ቤታቸው በፈረሰበት፤ መዝጊያቸtplf-eprdf-chairman-abay-woldu-and-dep-chair-debretsion-gebremikaelው ተነቅሎ በተወሰደበት ቤት ውስጥ ነው፡፡ ቻግኒ ያሉትን አልመለሷቸውም ፍኖተሠላም ያሉትንም የወሰዳቸው የአገር ውስጥና የውጭ ጩኸት ስለደረሰባቸው 2 ተቃውሞውን ለማብረድ ተብሎ እንጂ በድርጊቱ ባንባሲ ያለው ካድሬ አካባቢውን ከአማራ ሳላፀዳ ዕረፍት የለኝም፤ እያለ በግልጽ ይፎክራልባንባሲ ያለው ካድሬ አካባቢውን ከአማራ ሳላፀዳ ዕረፍት የለኝም፤ እያለ በግልጽ ይፎክራል ተፀጽተው አይደለም መንግስት በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡ ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት ሄደን ለመክሰስ የሚያስችለን ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን ፡፡
ለመክሰስ ዝግጅት እያደረግን ነው፡፡ ኮስማና መስለን ብንታይም ይህንን ለማድረግ አቅም አለን፡፡ ከጉራፈርዳ ተፈናቅለው በእኛ ጽ/ ቤትና በአዲስ አበባ ከተማ ተጠልለው
የነበሩት ተፈናቃዮች ለሊት አፍነው የት እንዳደረሷቸው አይታወቅም፡፡ በህይወት መኖር አለመኖራቸውም መረጃ የለም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በበኩላቸው በሰጡት መልስ በቅርቡ ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉትን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡

“ በአሶሳ ኩምሩክ 60 ኢንቬስተሮች አሉ፡፡ 60ዎቹም የቀድሞ የህውሃት ታጋዮች ናቸው፡፡ በአካባቢው ከ200 በላይ ትግሪኛ ተናጋሪዎች አሉ፡፡ በርካታ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችም ይገኛሉ፡፡ ማንም የነካቸው የለም፤ አማርኛ ተናጋሪዎችን እየለቀሙ እየደበደቡ እያሰሩ ከአካባቢው ያባርራሉ፤ ባንባሲ ያለው ካድሬ አካባቢውን ከአማራ ሳላፀዳ ዕረፍት የለኝም፤ እያለ በግልጽ ይፎክራል፡፡ ሰብስበው ጭድ የተከመረበት ቦታ ሜዳ ላይ አስረዋቸዋል፡፡ ጭዱን ለኩሰው በእሳት ሊፈጁን ነው ብለው ሥጋት ላይ ናቸው፡፡ አንድ ተፈናቃይ የኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ተጠቃሚ ነኝ በፖሊስ ሄጄ መድኃኒት ላምጣ ብሎ ቢጠይቅ አትሄድም ድብን በል ተብሎ ተከልክሏል፡፡ ስለዚህ ወደ ዓለም አቀፍ ፍ/ቤት መሄዳችን የማይቀር ነው፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment