ለሊት በደሴ ከተማ ከ30ሽ በላይ በራሪ ወረቀቶች ተበተኑ!
የደሴ መንግስት ባልስልጣናት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ናቸው መንግሰት የደሴ
ሙስሊሞችን ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል መስጂዶቻችንን
በመቀማት እና ኢማሞቻችንን በማባረር ከመስጂድ እንድንርቅ
ለማድረግ እንደሞከረም ይታወቃል
በዚህም ደሴ የነበረው እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ተቀዛቀዞ የነበረ
ሲሆን ዝምታው ለሊት ተሰብሯል፡፡ የተለያዩ ጹሁፎችን የያዙ
ከ30ሽ በላይ በራሪ ወረቀቶች ከተማውን አጥለቅልቀውት
አድረዋል ፡፡ወረቀቶቹ የተበተኑት በሙሉ በደሴ ከተማ ሲሆን
በቧንቧውሀ፤በሮቢት፤በአሬራ፤በሸዋበር፤በአራዳ፤በሳ ላይሽ፤በሰኞ
ገባያ፤በአሬራ፤በሜጠሮ ፤በቢለን እና በሌሎች በርካታሰ ሰፈሮች ወረቀቱ
ተበትኗል፡፡ወረቀቱ የተለያዩ ጹሁፎችን እና መፈክሮችን የያዘ ሲሆን
ከመፈክሮቸቹ ውስጥ “ኢትዮጵያን እየበጠበጠ ያለው የእስልምና
አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ አክራሪነት ነው” ፤”ኢቲቪ የውሸት
ኢንዱስትሪ ነው”፤”በእምነታችን አንደራደርም”፤ “አሚሮቻችን ማሰራ
እኛን ማሰር ነው”፤የእምነት መቻቻል እያደፈረሰ ያለው ሙስሊሙ
ህብረተሰብ ሳይሆን መንግስት ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡የመንግሰት
ባለስልጣናት ወረቀት እንደተበተነ መረጃው ከደረሳቸው በኋላ ከፍተኛ
መደናገጥ ውስጥ እንደገቡና አሁን በመራወጥ ላይ እንደሚገኙ
ታውቋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ተቀዛቅዞ የነበረው ትግላችን ከዛሬ ጀምሮ
አጠናክረን እንደምንቀጥል እናሳውቃለን፡፡
ሌሊት የተበተኑትን በራሪ ወረቀቶች ተከትሎ ፖሊሶች በተለያዩ
ሰፈሮች ተበታትነው ሙስሊሞችን በማሰር ላይ ይገኛሉ
ከቄራ መስጂድ አካባቢ ቤት ተከራይተው ቂርዓት ይቀሩ የነበሩ 8
ደረሶች ታፍሰው ተወስደዋል፡፡ እስር እና ድብደባ ትግላችንን ማስቆም
እንደማይችል ደግመን እናሳውቃቸዋለን፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ
ቆርጠን እምደተነሳን የሚገልጽ በድምጽ የተዘጋጅ ኦዲዮ አዘጋጅተናል
ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ እንለቃለን፡፡
source:Minillik Salsawi fb page.
የደሴ መንግስት ባልስልጣናት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ናቸው መንግሰት የደሴ
ሙስሊሞችን ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል መስጂዶቻችንን
በመቀማት እና ኢማሞቻችንን በማባረር ከመስጂድ እንድንርቅ
ለማድረግ እንደሞከረም ይታወቃል
በዚህም ደሴ የነበረው እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ተቀዛቀዞ የነበረ
ሲሆን ዝምታው ለሊት ተሰብሯል፡፡ የተለያዩ ጹሁፎችን የያዙ
ከ30ሽ በላይ በራሪ ወረቀቶች ከተማውን አጥለቅልቀውት
አድረዋል ፡፡ወረቀቶቹ የተበተኑት በሙሉ በደሴ ከተማ ሲሆን
በቧንቧውሀ፤በሮቢት፤በአሬራ፤በሸዋበር፤በአራዳ፤በሳ
ገባያ፤በአሬራ፤በሜጠሮ ፤በቢለን እና በሌሎች በርካታሰ ሰፈሮች ወረቀቱ
ተበትኗል፡፡ወረቀቱ የተለያዩ ጹሁፎችን እና መፈክሮችን የያዘ ሲሆን
አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ አክራሪነት ነው” ፤”ኢቲቪ የውሸት
ኢንዱስትሪ ነው”፤”በእምነታችን አንደራደርም”፤ “አሚሮቻችን ማሰራ
እኛን ማሰር ነው”፤የእምነት መቻቻል እያደፈረሰ ያለው ሙስሊሙ
ህብረተሰብ ሳይሆን መንግስት ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡የመንግሰት
ባለስልጣናት ወረቀት እንደተበተነ መረጃው ከደረሳቸው በኋላ ከፍተኛ
መደናገጥ ውስጥ እንደገቡና አሁን በመራወጥ ላይ እንደሚገኙ
ታውቋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ተቀዛቅዞ የነበረው ትግላችን ከዛሬ ጀምሮ
አጠናክረን እንደምንቀጥል እናሳውቃለን፡፡
ሌሊት የተበተኑትን በራሪ ወረቀቶች ተከትሎ ፖሊሶች በተለያዩ
ሰፈሮች ተበታትነው ሙስሊሞችን በማሰር ላይ ይገኛሉ
ከቄራ መስጂድ አካባቢ ቤት ተከራይተው ቂርዓት ይቀሩ የነበሩ 8
ደረሶች ታፍሰው ተወስደዋል፡፡ እስር እና ድብደባ ትግላችንን ማስቆም
እንደማይችል ደግመን እናሳውቃቸዋለን፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ
ቆርጠን እምደተነሳን የሚገልጽ በድምጽ የተዘጋጅ ኦዲዮ አዘጋጅተናል
ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ እንለቃለን፡፡
source:Minillik Salsawi fb page.
No comments:
Post a Comment