No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday 5 November 2012

በመከላከያ የጄኔራሎች ፍጥጫ ከኢየሩሳሌም አርአያ


በመከላከያ ያለው ሽኩቻ እየበረታ ሄዶዋል። በጄ/ል ሳሞራ ትዕዛዝ የአየር ሓይል አዛዥ የነበሩት ጄ/ል ሞላ ሃ/ማሪያም ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጎዋል። በምትካቸው ደግሞ ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ እንደሚቀመጡ ታውቓል። በቅርቡ የሜ/ጄኔራልነት ሹመት ያገኙት እና ወዲ ዘውዴ በሚል የሚጠሩት ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ ከበረሃ አንስቶ ከሳሞራ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላቸው ከዚህ ቀደም ጠቁሜ ነበር። የሹመታቸው ምስጢሩ ሳሞራ ናቸው። ካኤርትራ የሚወለዱት ወዲ ዘውዴ ከሳሞራ ባለፈ ለመለስ ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ናችው። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት « ፈሪ» ተብለው እንደተገመገሙ ታማኝ ምንጮች አስታውሰዋል።

በአንጻሩ ጄ/ል ሞላ ወደ አየር ሃይል አዛዥነት ከመምጣታቸው በፊት የላቀ ጀብዱ እንደፈጸሙ ምንጮች ጠቁመዋል። በሻእቢያ ጦርነት ወቅት ኰ/ል ማእረግ የነበራቸው ሞላ በባድመ፡ አስመራ፡ ተሰኔ….በመሳሰሉ ከባድ ውጊያዎች ላይ የጦር ጄቶችን በማብረር ሻእቢያን ድባቅ የመቱ ኢትዮጵያዊ ጀግና ናቸው።
ጄ/ል ሞላ ለአቶ መለስና ለሳሞራ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደነበራቸው ሲታወቅ በተለይ በጦርነቱ የተፈጥጸመው ሴራ፡ አሰብ ወደብን ለመያዝ የተነደፈው ፕላን መኮላሽትን ጨምሮ ባድመን እንስጥ የሚለውን ባለ 5 ነጥብ የክህደት አጀንዳና ሌሎች የነመለስ – ሳሞራ ሕገ ወጥ አካሔዶችን አጥብቀው ያወግዙ እንደነበረ ተጠቁሞል። « በራሱ እምነት የሚጉዝ ጠንካራ ሰው» ተብለው በባልደረቦቻቸው የሚሞካሹት ጄ/ል ሞላ ያራምዱት በነበረው አቁዋም በነመለስ- በረከት ጥርስ ተነክሶባቸው ቆይቶዋል። ከዚያም ባለፈ « የአንጃ ደጋፊ» በሚል ተገምግመዋል። ቢሆንም ግን ከአቖማቸው ዝንፍ ሳይሉ ቖይተዋል።
ከጄ/ል ሞላ ጋር የቅርብ ወዳጅ የነበሩትና የአየር ሃይል ባልደረባ የነበሩት ኰ/ል ክብሮም በ1996ዓ.ም የመለስን – ባድመን አሳልፎ የመስጠት አጀንዳ በመቃወም ሰራዊቱን ሰብስበው እንዲያወግዝ የማነሳሳት ጥሪ በማድረጋቸው አንዲባረሩ ተደርጎዋል። በ1999 ዓ.ም ማእረጋቸው ተገፎ እንዲባረሩ የተደረጉት የቀድሞ የአየር ሃይል አዛዥ ጄ/ል አለምሽት ደግፌ ፡ መጀመሪያ ያራምዱት የነበረውን – መለስን የመደገፍ አቁዋም በመተው መቃወም በመጀመራቸው ውሳኔው ሊተላለፍባቸው ችሎዋል። ጄ/ል አለምሽት ከስልጣን ከመነሳታቸው በፊት አንድ አስገራሚ ነገር ሰርተዋል፤ በ1993 ዓ.ም የአቶ መለስን ተሃድሶ በማውገዝ ጥለው የወጡት ጄ/ል ታደሰ በርሄ (ጋውና) እና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ « መታሰር አለባቸው » ሲሉ በወቅቱ የተከራከሩት ጄ/ል አለምሽት ከጊዜ በሁዋላ ለሁለቱም የቀድሞ ባለስልጣናት ስልክ ደውለው ይቅርታ መጠየቃቸው ነበር። « በናንተ ላይ ሳራምድ የነበረው ተግባር አሳዝኖኛል፤ የመለስን አካሄድ ያወቅኩት ዘግይቶ ነው። ይቅርታ አድርጉልኝ።» እንዳሉዋቸው ታማኝ ምንጮች አረጋግጠዋል። በነገራችን ላይ አለምሽት ቦሌ አካባቢ በየእለቱ መጠጥ ሲጎነጩና ሲበሳጩ ይታያሉ።
በአለምሽት ቦታ የተተኩት ጄ/ል ሞላ ለ4 አመት አየር ሃይልን ሲመሩ ከቆዩ በሁላ መነሳታቸው ከጀርባ ያለውን ከባድ የፖለቲካ ሽኩቻ ወደከፋ ጫፍ እንደሚያሽጋግረው የቅርብ ምንጮች ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ጄ/ል ሞላ በአየር ሃይልና በመከላከያ በርካታ ደጋፊዎች እንዳላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።
በሌላም በኩል ጄ/ል መሃሪ ዘውዴ በአንድ የአየር ሃይል አንጋፋ መኮንን ላይ የፈጸሙት አሳዛኝ ድርጊት ይገኛል። መ/አ ለማ ይባላሉ፤ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ለ25 አመታት በአየር ሃይል አገልግለዋል። በኢትዮጵያ በግራውንድ ስኩል እንዲሁም በሩሲያ ከፍተኛ ስልጠና ወስደዋል። ኤል-39 የመለማመጃ አውሮፕላን ሴፍቲ ሃላፊ ነበሩ። ከተግባርድ ጀርባ ኪራይ ቤቶች በሰጣቸው መኖሪያ ተከራይተው ይኖሩ ነበር። በ1996ዓ.ም ለውሽማቸው ቤቱን መስጠት የፈለጉት ጄ/ል መሃሪ መ/አ ለማን ቤቱን ይጠይቃቸዋል፤ « ለምን እለቃለው?» በማለት እምቢ ይላሉ። ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ለማስፈራራት ይሞክራሉ። ለማ ግን አልተበገሩም። ጄኔራሉ የአየር ሃይል ኤር-ፖሊሶችን በማሰማራት መ/አ ለማ በመኖሪያ ቤታቸው በምሽት ያስደበድባሉ። በአጋጣሚ ፓትሮል የሚዞሩ ፌደራል ፖሊሶች ደርሰው ያስጥሉኣቸዋል።
መ/አ ለማ ለደታ ፍ/ቤት ይከሳሉ፤ ደብዳቢዎቹ ፍ/ቤት ቀርበው ሲጠየቁ « ወዲ ዘውዴ ነው የላከን » ይላሉ። ከዚያም ጄ/ሉ ተከሰሱ፤ በአስገራሚ ሁኔታ ፍ/ቤቱ ክሱን በማቓረጥ «ጉዳዪ በወታደራዊ ፍ/ቤት ነው መታየት ያለበት» አለ። መ/አ ለማ በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ አንድ ጆሮቸው አይሰማም፤ኩላሊታቸውና እግራቸው ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበረ፤ የሃኪሞች ቦርድ « መስራት እንደማይችሉ በመግለጽ ቦርድ እንዲወጡ ወሰነ።
ይህን ተከትሎ ጄ/ል ወዲ ዘውዴ ባሳለፉት ቀጭን ትእዛዝ መ/አ ለማ እስር ቤት ተወረወሩ፤በየቀኑ ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸው ነበር። ክእስር ቤት በተደጋጋሚ ደብዳቤ ጽፈዋል፤ በወቅቱ የመከላከያ ሚ/ር ለነበሩት አባዱላ ገመዳ ጭምር የአቤቱታ ጥሪ አሰምተዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።
መጀመሪያ በአየር ሃይል ከዛም በታጠቅና ናዝሬት እስርቤቶች የታሰሩትና ከፍተኛ ግፍና ሰቆቃ የተፈራረቀባቸው መ/አ ለማ መጨረሻቸው ምን እንደሆነ አይታወቅም።

No comments:

Post a Comment