
ጨፋሮቢት ጀምሮ ደቡብ ወሎ ዞን እየተባሉ መጠራታቸውን ይጀምራሉ ፣ጨፋሮቢት ከሚሴ ፣ሃርቡ ፣ወለዲ ፎንተኒና ፣ኮምቦልቻ እንዲሁም ራቅ ብለው የሚገኙት ደጋን እና ገርባን ጨምሮ ደሴ እና ሌሎችም አጎራባች አገሮችንም እንደዚያው ጥሪያቸውን በደቡብ ወሎ ከተሰየመ ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በሰላማዊ ተቀምጠው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ባለፈው አመት የተጀመረውን የሙስሊሞች የተቃውሞ ሰልፍ መውጣት እና የመጅሊሱ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መመራት አለበት መንግስት እጁን ከሃይማኖት ስር ያውጣ የሚሉትን ጥያቄዎች አስመልክቶ ምንም ነገር ድምጻቸውን ሳያሰሙ መክረማቸው ይታወሳል ።ሆኖም ግን ያደፈጡበት ዋነኛ አላማ ይኖረዋል ተብሎ ግምት ተሰጥቶታል ይላል የማለዳ ታይምስ የፖለቲካል አናላሲስት ሲጠቁም ዛሬ ባልታሰበ ወቅት ድንገት ወጥተው መንገድ መዝጋት የቻሉበት ዋነኛ ምክንያት ለለውጥ ፍለጋ እንደሆነ እና ይህም ሃይላቸውን አጠናክረው እንደመጡ የሚያሳይ ነው ፤የወሎ ሰው ካልደረስክበት አይደርስብህም ነገር ግን እልህ አስጨራሽ የሆነ ነገር ላይ ከደረሰ እና ትእግስቱ ካለቀ አትመለሰውም ያለው ይሄው አናላሲስት ምናልባትም ከማይወጡት አዘቅት ውስጥ የገቡትን የወያኔ አባላቶች ትእቢቶቻቸውን ሊያስተነፍሱ ይሆናል የወጡት ሲል ገልጾአል ።በትላንትናው እለት መንገድ ዘግተው ከ4 ሰአታት በላይ ሲጮሁ የነበሩት እነዚሁ የሙስሊሙ ህብረተሰቦች ድምጻችን ይሰማ የማይሰማ ከሆነ እና ተግባራት ላይ የማይውሉበት ነገር ከተፈጠረ እኛም ከአላማችን ፈቀቅ አንልም በማለት ለዞኑ አስተዳደር የገለጹ ሲሆን የመወሰኛ ደብዳቤም መላካቸውን ከስፍራው የደረሰን ሪፖርት ያመለክታል ።የዞኑ መስተዳድር ምንም ምላሽ ሳይሰጥ የሰልፉን መበተኛ ሰራዊት ቢልክም ሰራዊቶቹ ሊገድቧቸው እንዳልቻሉ እና መንገዶቹን ሁሉ በመኪኖች እና በድንጋይ አጥረዋቸው ስለነበር በምንም መልኩ አልፈው ጥቃት ሊፈጽሙባቸው እንዳልቻሉ ሰኢድ ዋርሶ የተባለው የፌስቡክ አባላችን ለማለዳ ታይምስ በላከው ሪፖርት ላይ ጠቁሞአል።
source maleda times.
itis good news
ReplyDelete