No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday 22 October 2012

የወያኔ ፕራይቬታይዜሽን: በኢትዮጵያ ኪሳራ ሃብታሞች ይበልጥ ሃብታም የሚሆኑበት ሥርዓት

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሃብት ዘርፎ ከሚያዘርፍባቸው በርካታ መንገዶች አንዱ ፕራይቬታይዜሽን ነው።
በመሠረቱ የፕራይቬታይዜሽን ዓላማ በመንግሥት ይዞታነት የተያዙ የማምረቻና የንግድ ተቋማትን ይበልጥ ውጤታማ ነው ተብሎ ወደሚታሰበው የግል ኢኮኖሚ ዘርፍ በማዛወር የገበያ ውድድር እንዲበዛ እና ምርታማነት እንዲያድግ ማድረግ ነው። ፕራይቬታይዜሽን በብዙ አገሮች ተቀባይነት ያገኘው የግሉ ሴክተር በርካታ “ተዋንያን” ያሉበት እና ውድድርም የጦፈበት በመሆኑ በጥራት፣ በዋጋ፣በምርታማነትና በፍትሃዊነት አንፃር ከመንግሥት ሴክተር የተሻለ ነው ተብሎ የሚታመን በመሆኑ ነው።
በአገራችን ያለው ሃቅ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው።
ወያኔ ፕራይቬታይዜሽንን እየተገበረ ያለው ለሁለት ዋነኛ ዓላማዎች ነው። እነዚህም
አንደኛ፤ የተመረጡ ሃብታሞችን ይበልጥ ሃብታም ማድረግ፤ እና
ሁለተኛ፤ ከብድር ሥርዓት ጋር በማቀናጀት ቀድሞ የረባ ንብረት ያልነበራቸው የሥርዓቱ ደጋፊዎችን በፍጥነት ሃብታም እንዲሆኑ ማድረግ ናቸው።
የወያኔ አገዛዝ ፕራይቬታይዜሽንን ተጠቅሞ ስላደረገው ዘረፋ እና ሕገወጥ የሃብት ክፍፍል በርካታ ማስረጃዎች ማቅረብ ቢቻልም ለዛሬው የሚከተሉትን ብቻ ማንሳት ይበቃል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ኦገስት 1 ቀን 2008 በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለአሜሪካ መንግሥት የላከው ሚስጢራዊ ሰነድ አምልጦ ከሌሎች ብዙ ሰነዶች ጋር ዊኪሊክስ በተሰኘው ድረገጽ ጋር ለሕዝብ ይፋ ሆኗል። በዚህ ሰነድ እንደተገለፀው ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሰነዱ እስከተፃፈበት 2001 ዓም ድረስ ከመንግሥት ወደ ግል ይዞታነት ከተሸጋገሩ ንብረቶች ውስጥ ከእሴት አካያ ስልሳ በመቶው የተዛወሩት ለአንድ ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ ሼህ መሃመድ አላሙዲን ይባላሉ። ያኔ ሼህ መሃመድ አላሙዲን 64ኛው የዓለም ሃብታም ነበሩ። ከዚያ ወዲህ ደረጃቸውን አሻሽለው ዛሬ 61ኛው የዓለማችን ሃብታም ሆነዋል፤ የብዙዎች የዓለም ሃብታሞች ሃብት ሲቀንስ የእሳቸው ጨምሯል። ለዚህ የኢትዮጵያ ወርቅና ሌሎች ማዕድናት እንዲሁም ሌሎች ቢዝነሶች ሚና የላቸውም ማለት አይቻልም።
ቀሪዎቹ 40 በመቶዎቹን የወሰዷቸውስ እነማን ናቸው? ከላይ የጠቀስነው የአሜሪካ ኤምባሲ ሰነድ እስከ 2001 ዓም ድረስ ፕራይቬታይዝድ ከተደረገው ሃብት 60 በመቶው ለሼህ አሙዲን መሰጠቱን እንጂ ቀሪው 40 በመቶ ለማን እንደተሰጠ የሚናገረው የለም።
በመሠረቱ ስለ ፕራይቬታይዜሽን ለማወቅ የዊኪ ሊክስ ሰነዶችን ማገላበጥ ግዴታ አይደለም። መረጃው ከራሱ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ማግኘት ይቻላል። እኛ እያልን ያለነው ነገር በራሳቸው መረጃ የሚረጋገጥ ነገር ነው።
የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲን መረጃዎች በጥንቃቄ ያጠና ማንም ሰው ቀሪው 40 በመቶ የተሰጠው የሥርዓቱ ምሰሶና ማገር ለሆኑት የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ምስለኔዎቻቸው መሆኑን በቀላሉ ይደርስበታል።
በአዲስ አበባ ሌሎች ከተሞች እጅግ ዘመናዊ ህንፃዎችን እየገነቡ ሃገሪቷ በእርግጥም ያለፈላት እንዲመስል እያደረጉ ያሉት በብድርና በፕራቬታይዜሽን ሃብታም እንዲሆኑ የተፈቀደላቸው በዘራቸው የተመረጡ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች ናቸው። ብዙዎቹ ከሃያ ዓመት በፊት አንዳችም ሃብት ያልነበራቸው ሰዎች ናቸው፤ ዛሬ ግን ሚሊዮንን ተሻግረው ቢሊየነር የመሆን ህልም ውስጥ ገብተዋል። የእነዚህ ሰዎች የሃብት ምንጭ ከታታሪነትና ከፈጠራ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። እነዚህ በሕዝብና በመንግሥት ንብረት የወፈሩ መዥገሮች ናቸው
የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በዚህ ዓመትም ወደ 30 የሚጠጉ የመንግሥት ድርጅቶትን ሊሸጥ ተዘጋጅቷል። ከእነዚህም ውስጥ ትላልቆቹ የእርሻ ልማት ድርጅቶች ለአላሙዲን ተሰጥተዋል። በቅርብ ዓመታት የጠቀለሏቸው ኩባንያዎች ሲሰሉ የአላሙዲንን የፕራቬታይዜሽን ድርሻ በእሴት ወደ 70 በመቶ አድጓል። አላሙዲን የተውዋቸው በአንፃራዊ መልኩ ትናንሾቹ ኩባንያዎችና ሆቴሎች ደግሞ ለማን መስጠትና በኢትዮጵያ ኪሳራ መክበር እንዳለበት ውሳኔ እየጠበቁ ነው
በለገጣፎ እና በሌሎችም የአዲስ አበባ አካባቢዎች እንደሚታየው ድሆች ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ በራሳቸው መሬት ላይ ለሚገነባ ህንፃ የቀን ሠራተኛ ለመሆን ልመና ውስጥ ገብተዋል። በብድርና በፕራይቬታይዜሽን ጥቂቶች በሃብት ላይ ሃብት ሲያካብቱ በርካታ ድሆች ይበልጥ ደህይተዋል።
ይህ ኢፍትሃዊነት ብቻ አይደለም። ይህንን ዓይን ያወጣ ገፈፋን ማነፃፀር የሚቻለው ከቅኝ አገዛዝ ጋር ነው። የጂኖሳይድ ዎች ዳይሬክተር እንዳብራሩት ሁሉ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የአገር ውስጥ ቅኝ አገዛዝ ነው። ወያኔ ኢትዮጵያን ወሮ እንደያዛት አገር ነው እየዘረፈና እያዘረፈ ያለው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በፕራይቬታይዜሽን ስም እየተደረገ ያለውን ግልጽ ዘረፋ አጥብቆ ይቃወማል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመብቱ፣ ለአገሩ፣ ለሃብቱ፣ ለንብረቱ ሲል ወያኔን ለማስወገድ ቆርጦ ይነሳ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

No comments:

Post a Comment