No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday 16 October 2012

ኦክቶበር 14/ 2012 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የሦስተኛው ሩብ ዓመት አጠቃላይ የአባላት መደበኛ ስብሰባ አደረገ

Dr Murlualem proposing idea for the house.










የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በእንግሊዘኛው አጠራር Democratic
Change in Ethiopia Support Organization Norway DCESON* ሲባል አላማውም የወደፊቷን የምንመኛት ኢትዮጵያን የሰላም የነጻነት
እንዲሁም የፍትህ የበላይነት ለማስፈን ለሚጥሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ድጋፍ የሚሰጥ ድርጅት ነው፣
ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ድጋፍ የሚሰጣቸው ድርጅቶች  የግንቦት 7 ወይም GINBOT 7  እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ከአገር ውስጥ ናቸው.
ድርጅቱ  በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት በየሦስት ወሩ የሚያደርገውን አጠቃላይ ጉባዔ እሁድ ኦክቶበር 14 ፣ 2012
ኦስሎ Oslo ከድርጅቱ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አዳራሽ የተደረገ ሲሆን በእለቱ ወደ ሰማንያ ፡80 የሚጠጉ
አባላቶች የተገኘን ሲሆን  በእለቱ የፕሮግራሙ መሪና የድርጅቱ ሊቀመንበር  አቶ ዳዊት መኮንን የእንኳን ደህና
መጣቹ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ መስዋት ለሆኑት ኢትዮጵያውያን የአንድ ደቂቃ የህሊና
ጸሎት የተደረገ ሲሆን በመቀጠል አቶ ዳዊት በቀጥታ መድረኩን ለድርጅቱ ጸሀፊ ጋብዘዋል

አቶ ግዛቸው  የሦስተኛውን ሩብ ዓመት የስራ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ ከተዘረዘሩት ተግባራት መካከል
ድርጅቱ ድጋፍ ለሚሰጣቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ማለትም ለአንድነት እና ለግንቦት 7 የተለመደውን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን
ከነዚህም መካከል ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት በአሁኑ ሰአት የአንድነት የፖለቲካ ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት
ዶ\ር ነጋሶ ጊዳዳ በቅርቡ በደረሰባቸው ህመም ህክምናውን የግድ ውጭ ሃገር መታከም ስለነበረባቸው ድርጅቱ ጊዜያዊ ኮሚቴ
አቌቊሞ ወደ ሁለት ሺ አምስት መቶ ዩሮ 2500 EURO  ያሰባሰበ ሲሆን ገንዘቡንም ቀጥታ ጀርመን ሆነው
በካሽ የተቀበሉ ሲሆን ዶ|ር ነጋሶም ከድርጅቱ ለተደረገላቸው እርዳታ የምስጋና ደብዳቤ የላኩ ሲሆን ሌላው የድጋፍ
ድርጅቱ ክንውን ደግሞ በቅርቡ የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነስርአት በኢትዮጵያ   ሲደረግ ድርጅቱ ከኢህአፓ ጋር
በመሆን  ትልቅ የሰማዕታት ቀን ሴፕቴምበር September 02፣2012 በኦስሎ OSLO ልዩ ስሙ ታይገር ስታቱ ወይም የነብር ሃውልት
ያለበት ቦታ ላይ ያዘጋጁ ሲሆን  በእለቱም የሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች ስለ ዘረኛው መለሥ ዜናዊ የ 21 አመታት
አገዛዝና ስለዘረጋው ብልሹ ፖሊሲ በሰፊው የዘረዘሩ ሲሆን ፣ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ሊቀመንበር አቶ ፋሲል
የወያኔን የ 21 ዓመት የጭካኔና የዘር ማጥፋት ክስተቶችን በመዘርዘርና የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ የሚያደርገውን
ርብርቦሽ ከምንግዜውም በላቀ ተቻችሎና ተደራጅቶ  መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፣
በመቀጠልም የተለያዩ አክቲቪስቶች የተለያዩ ግጥሞችን ያቀረቡ ሲሆን ለአብነት ያህል አቶ ልኡል ያቅረቡት የእንግሊዝኛ
ግጥም በተሰብሳቢው ላይ አድናቆትን ያጫረ ሲሆን ፣ አቶ እንግዳ ታደሰም የአማርኛ ግጥም  ያቀረቡ ሲሆን ታዳሚውም
አድናቆቱን በጭብጨባ ገልጿል ፣ የምንጊዜውም ጸረ ወያኔ የሆኑት አቶ አምሳል የወያኔን የ 21 አመት የዘረፋ ፣ በዘር
የመከፋፈል ፣ የዘር ማትፋት፣ በሃይማኖት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ ለመከፋፈል ያደረገው ጥረት፣  የአገሪቱን
የመከላከያ ሰራዊት 98 ፐርሰንት የሚሆነውን ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ማስያዝ ፣የፈጠራ
ወሬ የሆነውን የ 11 ፐርሰንት የኢኮኖሚ እድገት፣ በየአረብ አገራቱ የሚሰደዱ እህቶቻችንና እንዲሁም የሚደርስባቸውን
ተደጋጋሚ የሆኑ አሰቃቂ ግድያዎችንና በደሎችን የወያኔ ፋሽስት መንግስት አይቶ እንዳላየና ይባሱኑ የራሱን ዜጎች
እንደ ጥፋተኛ በመቁጠር ለጉዳዩ ምንም ቁብ የማይሰጥ መሆኑ፣ የጭቁኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ለም መሬቶች ለውጭ
ዜጎች በችሮታ ወይንም እጅግ ዝቅተኛ በሚባል ዋጋ እየሸጠ መሆኑንና ከ 70 ሺህ በላይ ድሃው ገበሬ መሬቱን
ተነጥቆ ለስደት፣ለረሃብ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ፣ ከ 70 ሺህ በላይ በደቡብ ክልል ከ30 አመት በፊት ሰፍረው የነበሩ
የአማራ ብሄር ተወላጆችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በአንድ ጀምበር በማባረር የዜጎችን የመኖር ህልውና አጠያያቂ ያደርገዋል
ሲሉ አቶ አምሳል ሃሳባቸውን ለተሰበሰበው ህዝብ ከጨዋታ ጋር እያዋዙ ገልጸዋል፣
በመቀጠልም አቶ ፍቅሬ ዘለቀው የድርጅቱ ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ በድርጅቱ እንቅስቃሴ ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ውዝፍ
ወርሃዊ ክፍያ ያለባቸውን አባላት በጊዜው መክፈል እንዳለባቸው አሳስበዋል ፣ ከአባላት መካከልም አቶ ይታገሱ እና አቶ
ፍቅሬ አሰፋ በሁለተኛው ሩብ ዓመት አጠቃላይ ስብሰባ ላይ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ከተሰብሳቢው
ላቅ ያለ አድናቆትን አግኝተዋል፣
በመጨረሻም አቶ ዳዊት መኮንን ስለ ሁለቱ ድጋፍ የሚሰጣቸው ድርጅቶች ማለትም ግንቦት ሰባት እና አንድነትን እንደበፊቱ
ይቀጥል አይቀጥል የሚለውን ቤቶ ድምጽ እንዲሰጥበት ተደርጎ በሙሉ ድምጽ ሁለቱንም ድርጅቶች እየደገፍን መጓዝ
እንዳለብን ተወስኗል ነገር ግን ከተሰብሳቢዎቹ የተነሳው ሃሳብ ማለትም መድረክን እንደግፍ የሚል ሲሆን ቤቱ ብዙ
ከተወያየበት በኌላ ለሚቀጥለው ስብሰባ ቤቱ  የበለጠ እንዲወያይበት ሲል አዟል፣ አቶ ዳዊት መኮንንም ለተሰብሳቢው
ምስጋና ካቀረቡ በኌላ ስብሰባውን ዘግተዋል፣፣

written by  Efrem Tadesse








No comments:

Post a Comment