ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት
አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም
በውድ አገራቸው የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ
ታወቀ። አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ
ያደረጉት አቶ በረከት “አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል
ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በሚኒስትር ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ
በረከት ይህንን የተናገሩት Eritrean Oppositions Arabic Paltalk በሚሰኝ የኤርትራ ተቃዋሚዎች
የፓልቶክ መወያያ ክፍል እንግዳ ሆነው ባካሄዱት የጥያቄና መልስ ነው።





