No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Sunday, 2 February 2014

የድንጋይ ዉርወራ ፖለቲካ በዓዲግራት by Abraha Desta


ዓረና-መድረክ ለጥር 18, 2006 ዓም በዓዲግራት ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል። ዓዲግራት ከተማ ከመቐለ በስተሰሜን በኩል በ120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። የስብሰባው ዓላማ ከዚህ ቀደም በዉቅሮ፣ ማይጨው፣ ዓብይ ዓዲና ሽረ ከተሞች እንዳደረግነው ሁሉ የዓረና ፓርቲ ዓላማዎችና ፖሊሲዎች ከህዝብ ጋር ለማስተዋወቅ እንዲሁም ህዝብን ፖለቲካ ማስተማርና ማደራጀት ነበር።

ስብሰባ ለማካሄድ ተፈቀደልን። የማዘጋጃቤት አዳራሽም ተሰጠን። ስብሰባ ለማድረግ ማስፈቀድና አዳራሽ ማግኘት በቂ አልነበረም። ህዝብ በስብሰባው እንዲሳተፍ የጥሪ ወረቀት መበተን ነበረብን። በማይክሮፎንም ማወጅ ነበረብን። ዓረና በዓዲግራት ከተማ ስብሰባ መጥራቱ ለማብሰር የዓረና ፓርቲ ልኡክ ወደ ዓዲግራት ከተማ ሐሙስ ጥር 15, 2006 ዓም ተላከ።

ዓርብ ጥር 16, 2006 ዓም ጧት የልኡካን ቡድኑ ለሁለት ተከፍለው ዓዲግራት አቅራቢያ በሚገኙ የዕዳጋ ሐሙስና የፋፂ ከተሞች የስብሰባው ቅስቀሳ አደረጉ። ወደ ፋፂ የተላከው ቡድን የተሳካ ቅስቀሳ አድርጎ በሰላም ወደ ዓዲግራት ሲመለስ በዕዳጋ ሐሙስ የነበረ ቡድን ግን “ሕጋዊ አይደላችሁም” በሚል ሰበብ የዓረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙት ሐላፊ የሆነው አቶ ዓምዶም ገብረስላሴና መምህር ሃይለ ገብረፃዲቅ ታሰሩ። ከሰዓታት እስር በኋላ ተፈቱ። ወደ ዓዲግራትም ተመለሱ።

በጎንደር መስቀል አደባባይ በከፍተኛ ድምቀት ሲካሄድ ያረፈደው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠናቋል።

February 2, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር የተፈጸመው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ በአይነቱ በጎንደር ያልተለመደ ነው።
ሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ህዝብን አስተባብሮ ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ወያኔ በሚስጥር ከሱዳን መንግስት ጋር ተደራድሮ መሬት ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱንና ወደፊትም ተጨማሪ መሬት ለመስጠት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የጎንደር ህዝብ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርጓል።

Thursday, 23 January 2014

የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’ by Abraha Desta

          ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።
በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

Monday, 13 January 2014

የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’ By Abraha Desta.


ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።
በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

እኔና አፄ ምኒሊክ By Abraha Desta


ቆይ ግን እኔ የምኒሊክ 'አድናቂ' ነኝ እንዴ? ባጋጣሚ ስለ አፄ ምኒሊክ ጥሩም መጥፎም ፅፌ አላውቅም። ግን ብዙ የህወሓት ደጋፊዎች የምኒሊክ አገዛዝ እንደምደግፍ አድርገው ለህዝብ ይነግራሉ። የፌስቡክ ጓደኛዬ ዳንኤል ብርሃነም "የምኒሊክ ቲፈዞነትህ ለማስቀጠል ከፈለክ የሱ ወራሾች የሆኑ 'አንድነቶች' (ፓርቲው መሆኑ ነው) አሉልህ፤ ከነሱ ጋር ተቀላቀል" የሚል መልእክት ያለው አስተያየት ሰጠኝ።
...
የህወሓት ደጋፊዎች ከምኒሊክ ጋር የሚያገናኙኝ ምናልባት ህወሓት ስለምቃወም ይሆን? ወይስ እንደነሱ 'ሸዋ አማራ ጠላታችን ነው' ብዬ አለመፃፌን ነው? ህወሓትን መቃወም ከምኒሊክ አገዛዝ ጋር ምን ያገናኘዋል? ግን'ኮ ህወሓቶች በስልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙት ስትራተጂ 'ከፋፍለህ ግዛ' ነው። 'እኛና እነሱ' ብለው ይከፋፍላሉ። በዚህ መሰረት 'ህወሓት ከተቃወምክ የሸዋ ፖለቲከኞች ትደግፋለህ ማለት ነው' ይሉሃል። ቆይ የሸዋ ፖለቲከኞች ሳንደግፍ ህወሓትን መቃወም አንችልም ማለት ነው?

Saturday, 11 January 2014

Harvard lecturer and the author of “The Battle of Adwa” Raymond Jonas defending Menelik’s legacy




In March 1896 a well-disciplined and massive Ethiopian army did the unthinkable—it routed an

የዓሰብ ጉዳይ by Abraha Desta
--------------

ገና በጠዋቱ "ዓሰብን ማስመለስ አለብን የምትለው እንዴት ነው? ወደ አላስፈላጊ ጦርነትና ደም ማፋሰስ ልታስገቡን ፈለጋቹ?" የሚል አስተያየት አዘል ጥያቄ አገኘሁ።
...

መጀመርያ ወደ ጭንቅላታችን መምጣት ያለበት ጉዳይ 'የዓሰብ ወደብ የማነው?' የሚል ነው። ዓሰብ የኢትዮጵያ ልአላዊ ግዛት (ንብረት) ስለመሆኑ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ሕጋዊ (በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት) ማረጋገጫዎች አሉን። ዓሰብ የኛ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ምንም ምክንያት የለም። ማስረጃዎቹ (ማረጋገጫዎቹ) እዚሁ ፌስቡክ ላይ ባልፅፋቸውም በወደቡ ባለቤትነታችን ጥርጣሬ አይግባቹ። ስለዚህ ጥያቂያችን ፍትሐብሄር ነው።