No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday 9 July 2013

አቶ መለስ ዜናዊ ለትውልድና ለሀገራችን ጥለውት ያልፉት እኩይ፣ መራራና አሳዛኝ ሀቆች ከፊሊጶስ




የአቶ መለስ፣ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ግንኙነት ሁሌም ይደንቀኛል። በሀገርና በትውልድ ላይ የፈጸሙትንና
ጥለውት የሄዱትን ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሚትላልፍ መርዝ ሳስብ፤ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን የነበራቸውንጥላቻ ስቃኝ ፤ በ’ርግጥ የሰው አዕምሮ ተመራምሮ ይደርስብት ይሆን? እላለሁ። አሁንም ከኢትዮጵያና ከዚች ዓለምተለይተው ሄደው ግፋቸውን ሳስታውስ እጅግ አድርጎ ይገርመኛል ። ዘፋኙ ምን ነበር ያለው?……’’….ግርም ያደርገኛል ያሰበኩት እንደሆንሰው በገዛ ሀገሩ ስደተኛ ሲሆን።….”እስቲ ባለፉት አመታት አቶ መለስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊያን ላይ የሰሩትንና የፈጸሙትን መራራ ሀቆችና ለዚህትውልድ ጥለውት ያለፉትን ታሪክ እጅግ ባጭር ባጭሩ (የውቅያኖስን ውሀ በጭልፋ ጨለፎ ለመጨረስ እንደመሞከርይቆጠራል።) እናስታውስ።1ኛ/ አቶ
መለስ፣ኢትዮጵያናኢትዮጵያዊነታቸው፤አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵም ሆነ
በኢትዮጵያዊነታቸው አያምኑም ነበር። ”ኢትዮጵያዊነኝ” ወይም ”ኢትዮጵያ ሀገራችን” ወይም ”ሀገሬ”ሲሉ ተሰምተው አያውቁም።አቶ መለስ የድሮው ለገሰ ዜናዊ ሚያዚያ 30/1947በኢትዮጵያ በትግራይ ክፍለ ሀገር በአደዋ ተወለዱ።ገና ከጅምሩ አቶ መለስ ለኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያንአልታገሉም። የወላጆቻቸው ክፍለ ሀገር፤ “ኤርትሪያናትግራይ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛቶች ናቸውና።”እሳቸውም በኢትዮጵያዊነታቸው አያምኑም ነበር።ሕወሓትን እንደተቀላቀሉ፤ ላልተወሰነ ግዜ ጠፍተውወደ ኤርትራ፣ ወደ እናታቸው መንደር አዲቋላ ነበሩ። ከዚያም ተመልስው ለሕወሓትን እጅ ሰጡ። የሻአቢያን ትግልለመቀላቀል ፈልገው ግን ስላልተመቻቸላችው ወይስ ተቀባይነት ስላጡ? ይህ መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው። ትውልድእውነቱን እንዲያውቅ። (‘’ኤርትራ ከየት ወዴት” የሚለውን የራሳቸውን ድርሳን ይመልከቱ) ታዲያ ”ኢትዮጵያዊያልሆኑና በኢትዮጵያ ቅኝ ተገዥ የሆኑት” አቶ መለስ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመት የቻሉትን ያህል ከፋፍለውና አፈራርሰውገዙ። ሸጡ። በታሪካችንና በትውልድ ላይ ቀለዱ።2ኛ/ አቶ መለስ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ግንዛቤ፤አቶ መለስ ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ ያላትና በአጼ ምኒሊክ የተቆረቆረች ሀገር ናት ብለው የራሳቸውን የፈጠራታሪክ ያምናሉ። ማመን ብቻ አይደለም፤ እምነታቸውን ባገኙት መድረክና አጋጣሚ ሁሉ ሌላውን ወገን፣ በተለይምለአፍሪካዊያንና ለምዕራባዊያን በኢትዮጵያዊያን ላይ የበታችነትና የንቀት ስሜት እንዲያሳድሩ ከማስረዳትና ታሪክንከማዛባት ቦዘነው አያውቁም። ደጋፊዎቻቸውንም በዙ ድርሳናት እንዲደርሱ አድገዋል። የክህደትና የፈጠራ ታሪካቸውንለፓለቲካ ግባቸው ተጠቀሙበት። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ”ኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ያላትና ታላቅ ሀገር ነች።” ለማለትሲከጅሉ ተሰምተዋል። ዋይ!…..ንሰሀ ሊገቡ አስበው ነበር ይሆን? ወይስ አዲሱ የፓለቲካ አክሮባት? ግን ተቀደሙ።3ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ባንዲራ፤አቶ መለስ ለኢትዮጰያ ባንዲራ ያላቸው ጥላቻ እጅግ የከፋ ብቻ ሳይሆን “ከጨርቅ ጉዳይ የለንም!” በማለትየራሳቸውን ባንዲራ ሰርተው፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳይፈልግ ”እንዲቀበል” አድርገውታል።4ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ሠራዊት፤አቶ መለስ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያላቸውን ጥላቻና ማን አለበኝነት ካሳዮበት መንገድ አንዱ በብዙ ድካምናወጭ ሲገነባ የኖረውን የኢትዮጵያን ሠራዊት በአንድ ጀምበር በመበታተንና በማፈራረስ የጎዳና ተዳዳሪ አደረጉት።የባህርና የጦር መርከቦቻቸን ከፊሎቹን ለሻአቢያ ሰጡ፤ ሻአቢያ የማትፈልጋቸውን ደግሞ ለታሪካዊ ጥላቶቻችን ተሸጡ።5ኛ/ አቶ መለስ፣ የኢትዮጵያ ለዕልናና ዳር ድንበር፤በ1983 አቶ መለስ ከደርግ ጋር በሚደራደሩበት ወቅት፤ የሳቸው አሸናፊነተ ሲረጋገጥ፤ አሜሪካዊ አደራዳሪ ኸርማንኮኸን ለንደን ላይ ‘’የባህር በር ጉዳይ እንዴት ነው? መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል።’’ ሲሏቸው፤የአቶ መለስ መልስ “ስለ ባህር በር ጉዳይ ከሻአቢያ ጋር እንነጋገርበታለን” ነበር ያሉት። እናም ታሪካዊ ጥላቶቻችንዘመናት ሙሉ ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት የማድረግ ህልም አቶ መለስ እውን አደረጉላቸው። በእርግጥ አቶ መለስሌላም ዓላማ ነበራቸው። ኢትዮጵያን ከቻሉ አፈራርሰው፣ ካልቻሉ ደግሞ ደካማና የተከፋፈለ ህዝብ በመፍጠር፣ታላቋን ትግራይን በመመስረት ከኤርትራ ጋር በመስማማት አሰብን የትግራይ ማድረግ ነበር። ይህን ህልማቸውን እውንሳያደርጉ አቶ መለስ አለፉ። ግብረ-አበሮቻቸው ግን ”ትግላችን ይቀጥላል” በማልት ሲፎክሩ ይሰማሉ።6ኛ/ አቶ መለስና የኤርትራ ተውኔት፤ተውኔት-1፡ አቶ መለስ “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነች።” በማለት፤ ይህን ቋንቋ ሊገጸው፣አዕምሮ ሊያስበውየሚከብደውን ዓይን አውጣ የክፍለ ዘመኑን የክህድት ታሪክ ለመስበክና ለማስተማር ያላቸውን ሀይል ሁሉ ተጠቀሙ።በታሪክና በትውልድ ላይ አፌዙ።ተውኔት-2፡ ”ኢትዮጵያዊያን ስለ ኤርትራ ምንም የሚመለከታቸው ነገር የለም።” በማለት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብየዳር ተመልካች ሆኖ ቀረ። ለሺ’ ዘመናት ሙሉ ሲከፈል የነበረው የደምና የአጥንት መሰዋዕትነት ትርጉም የሌለውና”የትምህክተኞች” እንደነበር በመግለጽ፤ በጀግኖች ሙታን ወገኖቻችን ላይ ሲደነፉ ኖሩ።ተውኔት-3፡ ‘’ነጻነት ወይም ባርነት’’ ለሚጠይቀው ህዝበ ውሳኔ ህጋዊ እውቅና በመስጠት ኢትዮጵያን የመበታተኑንየጥላቶቻችንን ሴራ ተገበሩ:: አቶ መለስ በዚህም አድራጎታቸው በጣም ይመኩ ነበር።ተውኔት-4: “ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነበረች።” በማለት “ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነጻ መውጣቷን” ለተባበሩትመንግሥታትና ለአፍሪካ አድነት ድርጅት ደበዳቤ በመጻፍ እውቅና እንዲሰጧት ተማጸኑ፤ አቶ መለስ። ባለስልጣናቱከዓለም ህግ አንጻር እንደማይቻል ሊያስረዷቸው ቢሞክሩ (ከቡትረስ ቡትረስ ጋሊ ውጭ፤ እሳቸው ያገራቸውንየግብጽን ዓላማ ማስፍጸም ነበረባቸው።) ”ባገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ” አሏቸው።ተውኔት-5: በኤርትራ ምድር ከአሁን በኋላ ጥይት አይጮህም። ወ.ዘ.ተ.አቶ መለስ ኤርትራ ከኢትዮጵያዊ እንድትገነጠል ሳይሆን ገንጥለዋል። አቶ ኢሳያስ አፈወርቂም የአቶ መለስን ያሀልየደከሙ አይመስለኝም። አቶ መለስ ኤርትራን ገንጥለውና አስገንጥለው ከጨረሱና ሁሉንም ካመቻቹ በኋላ፤ የኤርትራተወላጅ ወገኖቻችን ኢትዮጵያን እንዲገዙ ይፈልጉ ነበር። (በእርግጥ ፍታዊ በሆነ መንገድ ከሆነ አቶ ኢሳያስምየኢትዮጵያ መሪ ቢሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተኛ በሆነ። ችግራችን ከሚከተሉት ዓላማ እንጅ።) ለዚህም ሲሉበሻአቢያ የወርቅ ጥርሳቸውን ሳይቀር እየተወለቀ ለተባረሩት ዜጎች፤ ”ይህም ሲያንስ ነው፣ እንዲያውም ኢትዮጵያ ካሳመክፈል ነበረባት” ነበር ያሉት። እናም ቀጠሉ… ለሻቢያዎች ኢትዮጵያዊያኖችን የሚያስሩብት ከርቸሌ አዘጋጅተውአሳሰሩ፣ አስገርፉ፣ አስገደሉ። ሻአቢያዎች የሀሰት ገንዘብ አሳትመው የፈለጉትን ነገር ሁሉ እንዲሸጡ፣ እንዲገዙ፣እንዲለውጡና እንዲያግዙ ተደረገ። እናም ሻአቢያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ቡና ላኪ ሆኑ።7ኛ/ መሬት ለሱዳንና ኢትዮጵያን መግዛት ለሚፈለጉ ሁሉ፤አቶ መለስ ኤርትራን ገንጥለውና አስገንጥለው ከወገኖቻችን ለያይተውን ብቻ አልቀሩም። ስልጣናቸው መደላደሉንሲያረጋግጡ፣ ሱዳኖች ጫካ በነበሩበት ወቅት ለዋሉላቸው ውለታና ተቀናቃኝ ጠላት ቢነሳባቸው አሳልፈውእንዲሰጧቸው የኢትዮጵያዊያን ገበሬዎችን በማባረር የኢትዮጵያን ክቡር መሬት ቆርሰው በገጸ-በረከትነት አበረከቱ።አቶ መለስ በዚህ አላቆሙም….. የሀገሪቱን አንጡራ መሬትና ማዕድን ዜጋውን እያፈናቅሉ ለባዕዳንና ለታሪካዊጠላቶቻችን ቸበቸቡ። እስከልተ ሞታቸው ድረስ እንግሊዝን የሚያክል ሀገር እንደሸጡ ይገምታል። አላማውምኢትዮጵያ ማፈራረስ ቀላሉ መንግድ በመሆኑ ነው።8ኛ/ የአቶ መለስና ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤አቶ መለስ የስልጣን ኮርቻቸውን እንደተፈናጠጡ፣ አ’ዱና ዋና ስራ አድርገው የያዙት ኢትዮጵያዊ ስብእናና ለኢትዮጵያክብርና አንድንት ሊታገሉ ይችላሉ ያሏቸውን ምሁራንን ከየትምህርት ትቋሞት አሳደዋል። አባረዋል። ገለዋል።የትምህርት ተቋማቱንም ለሆዳቸው ባደሩ ሆድ አምላኪ ‘’ምሁራንን’’ ተኩበት። ዓላማቸውም ተጠራጣሪ፣የማይትማምን፣ ለኢትዮጵያ አንድንትና ለክብሩ ብዙም የማይጨነቅ፣ እንደገዥዎቻችን በአፍቅሮ ንዋይ የታወረ፣ገንዝብ (ሀብት) የሁሉም ነገር መጀመሪያና መጨረሻ ነው ብሎ የሚያምን ለውጭ አለም ማንነቱን ያስረከበ ትውልድለማፍራት የታቀደ ነበር። ነውም።9ኛ/ የአቶ መለስ የዘር ጥላቻ፤አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ያፈራረሳል ብለው የተጠቀሙበትና ዋና መሳሪያ ያደረጉት ኢትዮጵያዊያንንበተቻለ መጠን በዘርና በቋንቋ በመከፋፈል፤ ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ ጥላቻንና ቂምን በማሰራጨት፤”የክልልይገባኛል” የርስ-በ’ርስ እልቂት እንዲኖር ማድረግ ነው። ” ከወርቅ ዘር መወልዴ፣ ለወላይታው አክሱም ምኑ ነው፣ወዘተ. የመሳሰሉትን አባባሎቻቸውን ስናሰብ፣ አቶ መለስ የጥላቻና የበታችነት ስሜታቸውን ለመወጣት፤የኢትዮጵያንየህዝብ እልቂት እንደማለዳ ጸሀይ ይናፍቁና ሌት ተቀን ይደክሙ ነበር።10ኛ/ አቶ መለስና የኢትዮጵያ ሃይማኖት፤አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አዳክሞ ያፈራርሳታል ብለው ካምኑበት ውስጥ አንዱ በሃይማኖት ከፋፍሎእርስ በ’ርስ ማናቆርና ማበጣብጥ ነው። በተለይም የኦርቶዶክሳዊያንን ዶግማ እምነት በማፈራረስ፤ ጳጳሱን በማባረርከራሳቸው መንደር የሚወልዱ “ጳጳስ” አስቀመጡ። ቤተክርስቲያንን ለሁለት ከፈሉ። እስልምናንም ከክርስቲያኑ ጋርማበጣበጡ እንደፈለጉት አልሆን ሲል እርስ-በርስ ለማነካከስ ብዙ ጥረዋል። ሞት ቀደማቸው እንጅ።11ኛ/ የአቶ መለስ ሰባአዊ ‘ረገጣዎች፤አቶ መለስ ገና ጫካ እያሉ ከ’ርሳቸው የተለየ ሀሳብ ያራምዳሉ ወይም ያስባሉ ብለው የጠርጠሯቸውን፤ በተለይ ደግሞኢትዮጵያዊነትን በሚያንጸባርቁና ትግላችን የመደብ ትግል ነው በሚሉ ታጋዮችን ያለ ‘ርኅራሄ ‘ረሽነዋል።አስረሽነዋል።መሀል ሀገር ከገቡም በኋላ በተለያዮ የሀገሪቱ ክፍሎች ዜጎች በቀለማቸው፣ በቋንቋቸውና በአመለካከታቸው ብቻከገደል ከነ ነፍሳቸው ተወርውረዋል። ቤታቸው ተዝግቶባቸው እንዲቃጠሉ ተደርጒል። ተረሽነዋል። ተሳደዋል።ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ በጥይት ተደብድበዋል። ታስረው ተገርፈዋል። ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ስደተኛና እንደሁለትኛ ዜጋተቆጥረዋል።አቶ መለስ ከወዳጃቸው ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂም ጋር በኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት አዘራረፋ ላይ አለመስማማትሲፈጠር “አማራ ለያይቶን እንጅ፤ እኛ እኮ በአንድ ሳንባ መተንፈስ የምንችል አንድ ህዝቦች ነን!” እንዳልተባለሁሉ፤በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ማግደው አቃጠሉ። ብዙ ዜጎችንም ተወልደው ካደጉበትና በስጋም በነፍስምከተሳሰሩበት ወገናቸው ለይተው አባረሩ።ለአሜሪካ ተላለኪ በመሆንም በሱማሊያ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች ሬሳቸው በመቋድሾጎዳናወች እንዲጎተትና የዓለም መሳለቂያ በማድረግ ከትውልድ ትውልድ የሚተላልፍ ጥላቻና ቂም በቀል ዘሩልን።12ኛ/አቶ መለስ፣ የሀገር ሀብትና ሙስና፤በአጠቃላይ ማለት ይቻላል፤ የሀገሪቱ ሀብት በሳቸው አካባቢ ባሉ ሰዎች፣ ለስልጣናቸው ታማኝና ለኢትዮጵያንኢትዮጵያዊያን ደንታ በሌላቸው ባባእዳን የኢትዮጵያ ጠላቶች በሆኑ ዜጎች እጅ እንዲገባ አደረጉ። ሀገሪቱን የግልሀብታቸውና ንብረታቸው በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆነ። ከፊሉ ተሰደደ። ከፊሉንም በርሀ፣ባህርና ውቅያኖስ በላው። ወጣት እህቶቻችን ለዝሙትና ለአረብ ግርድና አደሩ። አንዳንዶቹም እራሳቸውን አጠፋ።በፈላ ውህ ተቀቀሉ። ህጻናት ለስዶማዊያን ሳይቀር በጉዲፈቻ ተቸበቸቡ። ኢትዮጵያዊ ከዓለም ዜጋ ሁሉ የተጠላናየተዋረደ ሆነ።አቶ መለስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያን ከምድረ-ገጽ መጥፋት ከሚፈልጉ ምእራባዊ አጋሮቻቸው ቢያንስ በአመት 4ቢልዮን ዶላር ያገኙ ነበር። ግን ለሀገሪቱ ልማት የዋለው 14% ብቻ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት አረጋግጦላቸዋል።ቀሪው ግን የአቶ መለስንና የመሰሎቻቸውን ካዝና እያጣበበ፣ኢትዮጵያኖችን ግን እያራቆተ ነው። ከ11.4 ቢሊዎንዶላር በላይ በውጭ ሀገር ባንኮች አስቀምጠዋል። በቀርቡ ደግሞ ገዥዎቻችን በያዝነው ዓመት ብቻ ከ3 ቢሊዎን ዶላርበላይ ከሀገር አሽሽተዋል። እንገዲህ ይህ ጸሀይ የሞቀው ዓለም ያወቀው ነው። በድብቅ፣ በቤተሰብ ስምና በንግድ ስም21 ዓምት ሙሉ የተዘረፈውን እሱ ይቁጠረው። ሙስናማ በአቶ መለስ ዘመን አዲሱ ባህላችን አድርገውልናል።13ኛ/ አቶ መለስና ፍትህ፤የአቶ መለስ ፍርድ ቤቶች አስቂኝና አሳዛኝ ቲያትር ቤቶች ናቸው። የፈለጉትን ሰው በፈለጉት መንገድ በአንድ ቀንውስጥም ቢሆን ህግ አርቅቀው የማሰር፣ የመወንጀል፣ የመግደልና የመፍረድ መብት በእጃቸው መዳፍ ውስጥ ነው።በአሁኑ ወቅት ብዙ ዜጎች በእስር ቤት በፍትህ እጦት ይሰቃያሉ።14ኛ አቶ መለስ፣ ተሳዳቢነትና ውሸታምነት፤አቶ መለስ የበታችነት ስሜታቸው ሲገነፍልባቸውና የተደፈሩ ሲመስላቸው፤ አንድ አዕምሮው የተነካ ሰው እንኳንቢናገረው ሊቀፈን የሚችል የስድብና የንቅት ቃላቶችን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከመለደፍ ቦዝነው አያውቁም ነበር።ውሸታምነታቸው ግን አገርን ሲያፈርስና ህዝብን ሲያበጣብጥ ከመኖሩ አልፎ፤ ተከታዮቻቸው ሞታቸውን እንኳንሲዋሹን ከርመዋል።ማጠቃለያ፤አቶ መለስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስና የማጥፋት ተግባራቸውን እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስሰርተው በጽናት አልፈዋል። ስለዚህም ተከታዮቻቸው ‘’ሳያርፍ ያረፈው መለስ” ቢሏቸውና ሌላም ሌላም የመወድስስም ቢያወጡላቸው ያንሳቸዋል እንጅ አይበዛባቸውም። በእርግጥ አላማ አድርገው የተነሱበትን ሙሉ በሙሉአላሳኩም። ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርና ዜጋ አሁንም አለና። እንዲያውም ይህ ትውልድ አቶ መለስና ባልደረቦቻቸውለፈጸሙብን ግፍና በደል፤በኢትዮጵያዊነታችን ላይ ላደረሱብን ውርደትና ከፋፍልህ ግዛው የበለጠ ግንዛቤ እያገኘንመ’ተናል።-4-አዎ…አቶ መለስ ላይመለሱ ሄደዋል። ነገር ግን ላለፉት ዓመታት የደከሙበትና የለፉበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የስደት፣የክህደትና የሙስና በአጠቃላይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስና የማጥፋት ዓላማቸውን ለተከታዮቻቸውጥለው አልፈዋል። አዲሱ ገዥዎቻችን ደግሞ የአቶ መለስን ዓላማ ተከትለው እስከመጨረሻው እንደሚጓዙ አበክረውገልጸውልናል። ታዲያ እኛስ አሁንም እንዳለፈው በዚሁ በተገዥነት ጉዞ እንቀጥላለን? ወይስ ካለፈው ተምረን፣ አዲስየትግል ስልት ቀይሰን ኢትዮጵያን ከመፈራረስ አድነን፣ ሁሉም ዜጎቿ በፍትህና በእኩልነት የሚኖሩባት የሁላችን ሀገርእገነባለን? ጥያቄውና ጠሪው ለሁላችንም ነው።
——————-//——————
ፊልጶስ / ጳጉሜ 3/2004 ኢ-ሜል፡philiposmw@gmail.com
(በዚህ አጋጣሚ ይህችን የመለስን ምግባር እንድጽፍ ሀሳቡን ላቀረብክልኝና ለገፈፋህኝ ለያደቴ ሙሉጌታ የከበረ
ምስጋና ይድረስህ።)

No comments:

Post a Comment