No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday 18 February 2013

ስለ አሕበሽ በጥቂቱ:-

1. ከካፊር ጋር ቁማር መጫወት፣ የካፊርን (ክርስቲያን) ጎረቤትመስረቅና ማጭበርበር ይቻላል ብሎ
ያስተምራል።ዋናው እንዳይነቃ በድብቅ ማድረግና ዋናው መጠንቀቅ ነው ብሎ ያስተምራል፡፡ (መጽሐፉ
ሰሪህ አል-በያን፣ገጽ 133)
2. ሰሀቦችን ይሳደባል፡፡ አንዳንዶቹን ሰሀቦች ካፊር ናቸው የጀሀነም ናቸው ብሎ ጽፏል፡፡ ለምሳሌ ታላቁን የነብዩ
(ሶ.ዐ.ወ) ሆሃባ ሙአዊያ ኢብኑ አቢሱፍያን ካፊር የጀሀነም ሲልገልጿል፡፡ የነብያችን (ሶ.ዐ.ወ) ባለቤት
አዒሻን ተሳድቧል፡፡
3. በነጃሳ መስገድ ይፈቀዳል ይላል፡፡ (መጽሐፉ ቡግየቱ ጧሊብ፣ገጽ 99-100)
4. ዘካ የለም ይላል፡፡ ዘካ ከእስልምና ማዕዘናት አንዱ ነው፡፡ አህባሾች ግን ሰው ዘካ እንዳያወጣ ከወረቀቱ ብር
(ኖት) ላይ ዘካ የለበትም ይላሉ፡፡ ይህ ማለት በባንክም ይሁን በቤትዎ ቢሊዮን ብር እንኳ ካለዎ ዘካ አይስጡ
ብሎ ይቀሰቅሳሉ፡፡

5. ሪባ (ወለድ) መውሰድንያበረታታሉ፡፡ ባንክ ገንዝ አስቀምጠው ባንኩ የካፊሮች(ወይም ስራ አስኪያጁ ካፊር ከሆነ ጠላታችን ስለሆኑ ወለዱን መውሰድ ይቻላል ብለው ያስተምራሉ።
6. ሴቶቻቸው ሻሽ ብቻ አድርገው ሱሪ ማድረግ ይችላሉ ይላሉ። ጂንስና ፋሽንንም ያበረታታሉ፡፡
7. በሊባኖስ አገር የሙዚቃ ባንድ አላቸው ይህ ባንዳቸው ‹‹James last›› ይባላል፡፡ ዓመታዊ የሙዚቃ
ድግስ ያደርጋሉ:: በዛ ላይ ሴቶችና ወንዶች በጋራ ይጨፍራሉ፡፡
8. የአጅነቢ ሴትን ፎቶ፣ ቪዲዮ አልያም በመስታወት ውስጥ ራቁቷን እንኳ ብትሆን በስሜትም ቢሆን
ማየት ይቻላል:: ከቁርአንና ሱና ተቃራኒ ሆነው የተከለከለው በዓይን በቀጥታ ማየት ብቻ ነው ብለው
ያስተምራሉ፡፡

9. ‹‹ሪፋዒ›› የተሰኘ ጦሪቃን ያስፋፋሉ:: በኢትዮጵያ ጀምረዋል ይህ ጦሪቃ ከሺዓ ጋር የሚያመሳስለው
ብዙ እምነት አለው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ግን ሱኒ ነው፡፡

10. እምነት በልብ ነው ባይሰግዱም ኢባዳ ባይሰራም አንዴ አመንኩ ማለት በቂ ነው ብለው ያስተምራሉ::
(መጽሀፍ አ-ደሊል አልቀዊም፣ ገጽ 7)

11. ተከታዮቻቸው በአሜሪካና ካናዳ የቂብላ አቅጣጫ ካልተቀየረ ብለው ረብሻ ፈጥረዋል፡፡ በመጨረሻም ከመስጊድ ሲባረሩ የራሳቸው መስጊድ በተለየ ቂብላ ላይ ሰሩ። አሁን ከሙስሊሙ በተለየ ቂብላ ነው
መስጊዳቸው፡፡

12. ድግምትን አይቃወሙም። ራሳቸውም ይፈፅማሉ፡፡ ለሲህር የሚጠቀሙበት ‹‹ሁቡብ አል-አሀብ››
ብለው የሚጠሩት ነገር አላቸው፡፡

13. ቁርኣን የጂብሪል ቃል እንጂ የአላህ ቃል አይደለም ብለዋል። የአላህ ቃል አይፃፍም ይላሉ፡፡

14. የሚገርመው ይህን ሁሉ የጥመት መንገድ እየተከተሉ ሱፊያ ነን፣ ሻፊዒ መዝሀብ ተከታይ ነን ይላሉ፡፡

15. ከነርሱ እምነት ዉጭ ያሉ ዓሊሞችን እንደያስተምሩ ሆን ብለው ያስተጓጉላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሳስራሉ፣
ያውካሉ፣ በአንድ ወቅት በሊባኖስ ይህችግር በስፋት ፈጥረው ‹‹ሸሪዓመጽሔት›› በቁጥር 574 እትሙ ‹‹ሊባኖስ ጦርነት በመስጂዱ ውስጥ›› በሚል ርዕስ ጽሑፍ አስነበቦ ነበር፡፡

16. ዓመታዊ የሴቶቻቸው የሂጃብ ፋሺን ሾው አላቸው፡፡ በዚያ ላይ ሂጃብከሚለብሱት ሴቶች ጋር በጋራ ይጨፍራሉ ፡፡
አለህ ይጠብቀን
source: Minilik Salsawi
source Minilik salswa
source

No comments:

Post a Comment