No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday, 14 September 2012

የኢህአዴግ ምክርቤት ያለውጤት ተበተነ ፣ስብሰባው ነገም ይቀጥላል

የኢሃዴግ ምክርቤት በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ ከአራቱ  ድርጅቶች ጋር በመሆን ስብሰባውን ያደረገ ሲሆን  በስብሰባው ላይ የተገኙት  ከደቡብ ህዝቦች (ደህዴግ)  ፣አማራ(ብአዴን) ፣አሮሞ (ኦህዴድ) ትግራይ (ህወሃት)የተውጣጡ የምክር  ቤት አባላት ስብሰባውን የመሩት ሲሆን  ሌሎችም አጋር ድርጅቶች በታዛቢነት ተገኝተዋል ::በስብሰባው መጀመሪያ ላይ በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ  ሞትን አስመልክቶ የህሊና ጸሎት በማድረግ ፣የቀድሞውን መሪያቸውን በታሳቢነት ሲያስታውሷቸው እና በጸሎታቸው ፣ሲወድሷቸው እንደነበር ፣የውስጥ ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል።
በዛሬው እለት የተጀመረው ይኼው ስብሰባ በመላው ሃገሪቱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ እና ጠቅላይ የአመራሩን አካል ይመርጣል ተብሎ ሲጠበቅ ሳይመርጥ በመቅረቱ ጉዳያቸውን በሌላ አጀንዳ ላይ ለማተኮር ከመቻላቸውም አንጻር የውሎአቸውን ውይይት ቅድመ ከአቶ መለስ ሞት እና እንዲሁም ድህረ አቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሃገሪቱ ላይ ስለነበረው ውስጣዊ እና ውጫዊ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ትኩረት በመስጠት ስብሰባቸውን ጀምረዋል።በዚህም ጉዳይ ላይ መንግስት በድርጅቱ አንጻር ያለውን እንቅስቃሴ እና እየሰራ ባለው ሂደት ላይ በተለይም በሌሎች አለማትንም  ጭምር  እየተካሄደ ያለውን ሂደት መገምገማቸው የደረሰን ሪፖርት አጠናቅሯል ።እስከዛሬ ድረስ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስራ ገበታቸው ተሰውረው  ከጠፉም ሆነ እስከ ህልፈተ ሂወታቸውም ድረስ ከዚያም አልፎ  ስርአተ ቀብራቸው ከጠፉ ከዘጠና ቀናት በላይ  ያሳለፉ ሲሆን ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ግምገማ ሳይካሄድ ፣አገሪቱንም የሚመራት አካል ሳይኖር እነሱ እንደፈለጋቸው በደፈናው ሲጨፍሩበት የነበረበት ይህ ድርጅት ዛሬ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይነት ሩጫቸው የሚመርጡትን አካል ለማወቅም ሆነ ለመገምገም እንዳስቸገራቸው ፣የሚገልጽ ነው ከዚያም አልፎ ግራ አጋቢ የሆነ አቅጣጫ እንደ ደረሱ የሚያመላክት ነው ሲል ሪፖርተራችን ከስፍራው አትቷል ።
ባሳለፍነው ወር ም/ጠ/ሚንስትሩ የቀድሞውን ሚንስትር ተክቶ እየሰራ ነው ብለው በመገናኛ ብዙሃን ከመለፈፍ አልፈው ለይስሙላ  አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን አስቀምጠው ይጫወቱባቸው እንደነበር አክሎ የጠቆመ ሲሆን ፣በወቅቱ ምንም ነገር የሰሩት ነገር ባለመኖሩ ለዛሬ ታስቦ የነበረው ስብሰባ ለመምረጥ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው የሚጠቁም ትልቅ አጀንዳ ነው ብሎአል ።
   በሌላም በኩል የዛሬውን ስብሰባ ለማራዘም የተፈለገበትም ዋነኛ ጉዳይ የሚፈልጉትን ሰው በቅድሚያ ከመረጡ በኋላ ፣በስብሰባው አዳራሽ ለይስሙላ የእጅ ብልጫቸውን እይታ የሚረዳበት መንፈስ ለመፍጠርም የሚችል ጊዜ ለማግኘት ማምሻቸውን በግል ስብሰባ ሊወጠሩ ይችላሉ ፣ይህም  ከልምድ እንደ ምናውቀው ወያኔዎች ቀድመው እርስ በእርሳቸው ተመራርጠው ፣ምርጫ  በጨዋታው አሸናፊ አበቃ ብለው  ሊያጃጅሉን ይከጅላሉ ሲል የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ፍንትው አድርጎ ለማሳየት ይሞክራል።
በዚህ በዛሬው ስብሰባቸውም ላይ ስለሃገሪቱ ምን ሰራን የሚል ሃሳብ ይዘው የቀረቡ ሳይሆኑ እንዴት ነበር ብለው እየጠየቁ ነው ያሉት ! “ እንዴት ነበር ማለት “ይላል ዘጋቢያችን “የተጠቀምነው ፍልስፍና አዋጥቶናል ወይ ?እንዴትስ እንቀጥል ?አሁንም ብንጠቀምበት ሊረዳን ይችላል ወይ” እያሉ እራሳቸውን በማታለል ቴክኒክ ላይ ይገኛሉ ።በእርግጥም ማድረግ የሚገባቸው ነገር ቢኖር ይህንን ሰርተናል የተሳሳትነው ይሄ ነው በዚህ መልኩ መስተካከል ይገባዋል ብለው ማለት ሲገባቸው ዛሬ ግን ምን ሰራን ብለው ሳይሆን እንዴት ነበር ብለው ማለታቸው ያለፈውን ሞኝነታቸውንም ገልጦ ያሳያል በማለት ገልጾአል።በሃገሪቱም ላይ ምንም አይነት ስራ እንዳልሰሩ  የዛሬው የምርጫ ስብሰባ አለአግባብ ያለምንም ውጤት ሲበተን ሊገልጽ  የሚችለው ለሃገሪቷ ግድ የለሾች መሆናቸውን ሲያሳይ ለስልጣን ጥቅማቸው ብቻ እንደሚሮጡ የሚያመላክት ነው ይላል ። ምርጫው የምክርቤቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ለመምረጥ ያደረገውን ወደ ጎን በመተው ስለ ኮብልስቶን ልማት እና የፖለቲካ አስተዳደር እንደዚሁም የፖለቲካ ድርጅቶች አሰላለፍ በቀድሚያ የሚመረምር እና የሚገመግም ሲሆን ቀጣዩ የመለስን ቦታ ሊተካ የሚችል ሊቀመንበሩን ምርጫ ሊያከናውን የሚችለው በነገው እለት ሊሆን ይችላል ሆኖም ግን አሁንም የጊዜጥበት ይኖራል በማለት ጊዜውን ሊያስተላልፉት ይችል ይሆናል የሚል ግምት ተሰጥቶታል ሲል ማለዳ ታይምስ አትቷል ።
    በምርጫው ላይ በከፍተኛ ደረጃ  ይመረጣሉ ተብለው የሚጠበቁት አባይ ጸሃይዬ እና አርከበ እቁባይ ይሆናሉ ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን በድርጅቱም ውስጥ ባለው ጭምጭምታ መሰረት እነሱ ይሻላሉ የሚል እሳቤም ተጥሎባቸዋል ። በአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኩል ያለው የምርጫ ጉዳይ ግን ተስፋ አስቆራጭ ከመሆኑም በላይ ምንም ነገር ስለ እሳቸው በመድረኩም ሊነሳም ሆነ ሊነገርም አልተቻለም በማለት ያክላል ።በዚህ ሁኔታ ግን የሚቀጥለው የህወሃት ስብሰባ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን የሚመርጥ ከሆነ  እሳቸውን ከበላይ በማድረግ ህወሃት ከስር በመሆን አገሪቱን ለማሽከርከር በተለመደው ስልታቸው እንቆቅልሽ ጨዋታ እንደሚጀምር ጠቁሞአል ።በሌላም በኩል አሁንም በእነ አቶ በረከት በኩል ክፍፍሉ እንደቀጠለ ነው ።ውዝግቡ በዚህ ስብሰባ ላይ ሊነሳም ምክክርም ሊደረግ አልታሰበም በውስጣቸው ያለውን ቁስል ደብቀው በስውር ስብሰባቸውን ማካሄዳቸውን ገልጧል ።
በእለቱ  በስብሰባው ላይ የአፋር የጋንቤላ፣ የሃረሪ እና ጉምዝ አጋር ድርጅቶች እና ሊቀነመናብርት በተጋባዥነት የተሳተፉ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ከተመልካችነት ያለፈ ምንም ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደማይችሉ እና እንዳላደርጉ በስብሰባው ላይ የተገኘው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ አክሎ ገልጾአል።

No comments:

Post a Comment