No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday, 13 December 2013

ሌላው ኢትዮጵያዊ የተዋረደበት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን – በኦጋዴን!

የራስን እድል በራስ መወሰን፣ እርስ በርስ እስከ ማጣላት…
ዘንድሮ በኢትዮጵያ ተከበረ የተባለውን የብሄሮች  ቀን ምን ያህሎቻችሁ እንደተከታተላቹህ አላቅም። ላላያችሁት ግንዛቤ ለመፍጠር ያህል… ዘንድሮ በአሉ የተከበረው ሱማሌ ክልል፣ በኦጋዴን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን በመንገር ወጋችንን እንጀምራለን። ይህ ዝግጅት እስከዛሬ በትግራይም፣ በአማራውም ክልል ተደርጓል… ሆኖም በአሉ ላይ ሁሉም የየብሄሩን ባህል ለማሳየት ሲጥር እንጂ፤ አንደኛው ብሄር ሌላውን ሲሰድብ ያየንበት አጋጣሚ አልነበረም። የዚህ አመቱ የብሄር ብሄረሰቦች ወይም የብሄረተኞች ቀን ሌላውን ኢትዮጵያዊ በመውቀስ ላይ የተመሰረተ ነበር።
“አማራው፣ ደገኛው፣ የመሃል አገር ሰው…” እያሉ ቀጠሉ አስተያየት

Thursday, 12 December 2013

ሰበር ዜና መንግስቱ ሃይለማሪያም ከኢሳት ጋራ ቃለ መጠይቅ አደረገ/ጉ

mmm
Former ‪#‎Ethiopia‬-n President Mengistu Hailemariam holds an interview with ESAT Tv/Radio. He told the media Station from his residence today that the late South African President Madela was invited by the current Ethiopian regime to visit Ethiopia and recieve honorary Doctorate so many times but had refused saying that he would not like to visit a Country that “is divided”.

Tuesday, 3 December 2013

የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ – ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)


አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።

Friday, 8 November 2013

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራር አባላትላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ።

          

በጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ሃይለማሪያም ደሳለኝ እውቅናና ትእዛዝ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች በሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሄድ አመራሩን ለመግደል ሙከራ ቢደረግም ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል ከፍተኛ ክትትል ሙከራው መክሸፉን ሕዝባዊ ሃይሉ ገለጸ። ይህ ልዩ ትእዛዝ ጥቅምት 30 2006 ዓ/ም ተፈጻሚ እንዲሆን እቅድ የነበረ ቢሆንም ሕዝባዊ ሃይሉ ጥቅምት 27 2006 ዓ/ም ሊያከሽፈው ችሏል። ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን።
ምንጭ :- http://www.ginbot7pf.org/

Thursday, 7 November 2013

ስየ አብርሃ የኢትዮዽያ ሰራዊት አሰባስቦ የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት ለመገልበጥ እያሴረ ነው በሚል ህወሓቶች ተሸብረዋል



ህወሓቶች ባስቸኳይ ስብሰባዎች ተወጥረዋል። ሰሞኑ በመቐለ ከተማ የደህንነቶች፣ የታማኝ ካድሬዎችና የምክርቤት ስብሰባዎች ነበሩ/አሉ። የተጨናነቁበት አንድ ጉዳይ አለ።
ህወሓቶች ካድሬዎችን ሰብሰበው የሆነ ግለሰብ ወይ አካል ዒላማ አድርገው ስሙ በማጥፋት ከህዝብ ለመነጠል ጥረት ያደርጋሉ። ቀደም ሲል “አብርሃ ደስታ የሚፅፋቸው ነገሮች ዉሸት ናቸው እያልን ህዝብ እንዳይሰማው እናድርግ” በሚል አብርሃ ደስታ በመላው ትግራይ በራሳቸው አንደበት አስተዋውቀውታል።
አሁን ደግሞ በመላው ትግራይ ስለ ስየ አብርሃ መጥፎ በመናገር ስሙ ለማጥፋት ታቅዷል። በህወሓት መንደር ዋነኛ ስጋት የፈጠረው (ባሁኑ ሰዓት) አብርሃ ደስታ ወይ ዓረና ፓርቲ አይደለም፤ ስየ አብርሃ እንጂ። ስየ እንዴት ለህወሓቶች ስጋት ፈጠረ? ‘ስየ ከፖለቲካ ራሱ አግሏል’ እየተባለ አልነበረም?

Monday, 4 November 2013

Mining Corruption in Ethiopia November 3, 2013 by Alemayehu G. Mariam


The Shame of a Nation
In my seventh commentary on corruption in Ethiopia this year, I focus on the mining sector. For other commentaries on the subject, visit my blog site at “Al Mariam’s Commentaries”.
corruption in Ethiopia is not a simple problem limited to a few rogue
I continue to offer commentaries on corruption in Ethiopia to keep public attention sharply focused on the structural nature of the issue. In the past few months, the ruling regime has been grandstanding its “anti-corruption” efforts by corralling a few officials of the “Revenue and Custom’s Authority” and businessmen on charges of corruption. The kangaroo court corruption drama for those suspects is an amusing political theater staged for the entertainment of international loaners and donors who have recently intensified their pressure on the regime to show greater transparency and public accountability. For the domestic crowd, the regime’s grandstanding

Sunday, 3 November 2013

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ:


ወይዘሮ አዜብ መስፍን የፓርቲ መልቀቂያ አቀረቡ: ተቀባይነት አላገኘም::#Ethiopia
ሕወሓት ለወይዘሮ አዜብ ስልጣን በመስጠት በስልት ልታጠምዳቸው ነው::#TPLF

"ለእኔ ስም የሚያወጡልኝ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ የሕወሓት ሹሞች ናቸው::" የሚሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት የሆኑት እና የሙስናዋ ወይዘሮ በመባል የሚታወቁት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለፓርቲያቸው ያቀረቡት የፖ
ለቲካ በቃኝ ማመልከቻ ተቀባይነት ማጣቱ ሲገለጽ የሕወሓት ከፍተኛ ሰዎች ወይዘሮ አዜብን ለማጥመድ በሚያስችል ስልጣን ላይ ሊያስቀምቷቸው እንዳሰቡ ምንጮቹ ጠቁመዋል::የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው በወይዘሮ አዜባ ጋር በዋዛ አንላቀቅም በማለት ቂም በቀላቸውን ሊወጡባቸው ይችላሉ የሚል ግምቶች በሕወሓት አከባቢ እየተነገሩ ነው::

ለወይዘሮ አዜብ የታሰበው ስልጣን የትኛው እንደሆነ ባይታወቅም በስልት ከፖለቲካ ለማፈግፈግ እና ለመልቀቅ ከአገር ለመውጣት እንደማይቻል ተነግሯቸዋል:: ወይዘሮ