No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday, 30 July 2013

የዘመኑ መንፈስ (በእውቀቱ ስዩም) July 29, 2013

በእውቀቱ ስዩም
Bewketu Seyoum is a young Ethiopian writerባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡
ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡
ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡
‹‹…ኢትዮጵያን የመሠረታት የሶሰትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡በአማራው፣በኦሮሞው፣በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭት እና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡…የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለው የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው››
ጃዋር የኢትዮጵያን መሠረት የሦስት ብሄረሰቦች የስልጣን ግብግብ አድርጎ ወስኖታል፡፡ በመጀመርያ፣ ሌሎች ብሄረሰቦች በግብግቡ ተሳትፎ እንዳልነበራቸው አድርጎ ማቅረቡ አንድ

Monday, 29 July 2013

ከ“ሙስና”ው ክስ በስተጀርባ ከተመስገን ደሳለኝ


  • የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለትንተና አዳጋች መሆኑን የሚናገሩ ምሁራን መከራከሪያቸው ፖለቲከኞቹ ከርዕዮተ-ዓለም ይልቅ ‹‹ሴራ››ን ማስቀደማቸውን በመጥቀስ ነው፡፡ በርግጥም አብዛኛው የፓርቲዎቹ የአመራር አባላት ከክህሎት እና ርዕዮተ-ዓለም መራቀቅ ይልቅ በዘልማዱ ፖሊቲካ የተካኑ ናቸው፡፡ በተለይም የ1966ቱ ‹‹አብዮት›› ያሰረፀው የ‹‹ፓርቲ ፖለቲካ›› የተደራ ‹‹ሴራ›› ምን ያህል ኩነትንም ታሪክንም መቀየር እንደሚችል አሳይቷል፡፡
    የሁሉንም ፓርቲ የአመራር አባላት አመዳደብ መስፈርት ከምር ከፈተሽነው ከፊት መስመር ከምናገኛቸው አብዛኞቹ በዚህ አይነቱ የጨዋታ ህግ የተሻሉ ሆነው ስለተገኙ መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም (ሻዕቢያ፣ ኦነግ፣ ደርግ፣ ኢህአፓ-እነጌታቸው ማሩንና ብርሃነመስቀል ረዳን፣ ህወሓት-እነስሁል፣ እነአረጋዊ፣ እነስዬ፣ ብአዴን-እነያሬድ ጥበቡንና ሙሉዓለም አበበን፣ ኢህአዴግ፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ቅንጅት፣ አንድነት… የመርህና የህግ ተገዥ የሆኑ አመራሮቻቸውን ደግመው ደጋግመው በሴራ ፖለቲካ በጓሮ በር ሸኝተዋል) የዚህ ፅሁፍ ዓላማ አውራው ኢህአዴግ፣ በተለይም ከድህረ ትጥቅ ትግሉ ወዲህ ባለተፃፈ ህጉ በመሪዎቹ ላይ የፈፀማቸውን የሴራ ፖለቲካ ለመቃኘት መሞከር ነው፡፡ እንደ ሚታወቀው ስርዓቱ ወደስልጣን ከመጣ በኋላ ተአማኒነትን ያላገኙ ግዙፍ የፖለቲካ እርምጃዎችን በጉምቱ መሪዎቹ ላይ በተደጋጋሚ ሲወስድ አይተናል (በተጠመደ ፈንጅ ህይወቱ ያለፈውን የብአዴን መሪ ሙሉዓለም አበበንና የጄኔራል የሎም ግድያን ሳንጨምር)

Sunday, 28 July 2013

ETHIOPIA: LEGALLY CORRUPT July 24, 2013 by Wondimu Mekonnen

Introduction

The simplest definition of state corruption is the self-enrichment of government officials through the use of the power bestowed on them and state mechanism. In Ethiopia, the TPLF is a mafia type gang that is running its own Mafiosi economic empire, not the country as a legitimate caring government.
The country itself is up for sale, as long as there are buyers out there. That is why people in Gambella were to evicted and their land sold to Indian and Arab, Turkish, Pakistani Billionaires. Recently, the Ethiopian Government refused to cooperate with the World Bank when it was asked to investigate whether the World Bank violated its own policies by funding, in which thousands of people were allegedly relocated to make way for agricultural investors. The British Government actually knowingly or unknowingly funded a programme that evicted the tribes of the Lower Omo Valley in south west Ethiopia – chief among them the Mursi, the Nyangatom, the Bodi and the Daasanach, who depend on a combination of flood retreat cultivation on the banks of the Omo

Thursday, 18 July 2013

! …. ትንሽ ስለ ዓረና ትግራይ ፓርቲ …….! Abraha Desta


ዓረና ትግራይ ፓርቲ ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ

ፓርቲው ለእሁድ ሓምሌ 14, 2005 ዓም በመቐለ ማዘጋጃቤት አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል። ፓርቲው ‘አሉ’ በሚላቸው የህዝብ ችግሮች (ኑሮ ውድነት፣ የወጣቶች ስደት፣ የግብር አከፋፈል ችግሮችና የሙስና ሁኔታ፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የመሳሰሉት የህዝብ ችግሮችና በዓረና ትግራይ የሚቀርቡ አማራጭ መፍትሔ ሓሳቦች ከመቐለና አከባቢው ህዝብ ነዋሪዎች መወያየት እንደሚፈልግ አስታውቋል። ሁላችን ተጋብዘናል፤ እንሳተፋለን።

ስንሳተፍ ግን ምን እንጠብቃለን? ዓረናዎች የህዝብ ችግሮችና የመፍትሔ አማራጫቸውን ሲነግሩን የህወሓት ደጋፊዎች (መሳተፋቸው አይቀርም ከሚል ነው) ደግሞ ‘ እናንተ ዓረናዎች እኮ ያው ናችሁ። ህወሓት ነበራቹ። ያኔ ለውጥ አላመጣችሁም።’ የሚል የተለመደ የፕሮፓጋንዳ ስትራተጂ መጠቀማቸው አይቀርም።

እኔም እላቸዋለሁ፡ አዎ! አብዛኛው የትግራይ ህዝብ የህወሓት ታጋይ ነበር፤ የህወሓት ፓርቲ አመራር አባል ግን አልነበረም። እነኚህ የዓረና አባላትም የትግራይ ህዝብ አባላት እስከሆኑ ድረስ የህወሓት ታጋዮች ነበሩ። የህወሓት ታጋይ መሆን በራሱ ስሕተት አይደለም። ህወሓት እንደ ትግልና እንደ ገዢ መደብ የተለያዩ ናቸው።

መንግስት ያደረሰበትን ሰቆቃ በፍኖተ ነፃነት ያጋለጠው ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ የገባበት ጠፍቷል



ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ የገባበት ጠፋ

ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት በመንግስት የደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በማዕከላዊና ዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ የደረሰበትን በደል ይፋ ቢያደርግ እንደሚገድሉት እንዳስጠነቀቁት ለፍኖተ ነፃነት አስረድቶ ነበር::

ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ ከአበበ ገላው


ውድ አትሌት ሃይሌ፣ ከነመላው ቤተሰብህ እንደምን ከርመሃል? ልጆቹ እንዴት ናቸው፣ አለምስ እንዴት ሰንብታለች?
ሰሞኑን የወዳጅ የዘመድ ምክር አላዳምጥ ብለህ እንደነ ጋሼ ግርማና ጋሼ ሃይለማርያም ደሳለኝ የህወሃቶች አሻንጉሊት መሆን
እንዳማረህ ስሰማ በጣም ተገረምኩ። በመላው አለም ዝና ያተረፍክበትን እሩጫ ትተህ “ቤተመንግስት” ወይንም “ፓርላማ” ቁጭ ብለህ
ዝንብ ማባረር ምን ይጠቅመኛል ብለህ ነው? አንተም እንደነጋሼ ግርማና ሀይለማሪያም በቁምህ ከመሞትህ በፊት ምክሬን ባትሰማ
እንኳን ለማንኛውም ይቺን አጠር ያለች ጦማር ልጽፍልህ ወሰንኩ።
እኔ ያቺን “ሪከርድ” የሰበርክባትን ቲሸርት
ነፍሳቸውን ይማርና ለዛ ህዝብ ላፈኑ፣ ላሰቃዩ፣
ለረገጡና ለጨረሱ፣ እንኳን በቁማቸው ሞተውም
ላስመረሩን የሂትለርና የሞሶሊኒ ግልባጭ
በአደባባይ ስትሸልም መካሪ ማጣትህን
ገምቻለሁ። ግለሰቡ መሸለም ሳይሆን ተይዘው
እንደ ናዚዎቹ ኑረንበርግ ለፍርድ መቅረብ
ይገባቸው እንደነበር ጠፍቶህ ነበር ማለት
አይቻለኝም። ግን ሃያሉ ፈጣሪ ፍርዱን እንደማያዘገይ አሳየን።