No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday, 29 March 2013

North Korea orders rockets on standby to hit US bases - state media

Pyongyang has ordered rocket units be put on standby to fire on US bases in the South Pacific. “The time has come to settle accounts with the US imperialists in view of the prevailing situation,” North Korean leader declared, according to state media.
It follows a US B-2 flyover of South Korea that saw dummy ammunition dropped as part of a joint military drill Thursday.
The North Korean leader and army marshal Kim Jong-un declared that “the revolutionary armed forces of the DPRK would react to the US nuclear blackmail with a merciless nuclear attack, and war of aggression with an all-out war of justice,” according to KCNA.
The decree placing the Strategic Rocket Force on standby was signed following an urgent meeting of the military command early Friday morning, according to North Korean media. The plan suggests

ESAT Yesamintu Engida Interview With Photo Journalist Benyam Mengesha Part


! …….. የትእምት ካፒታል ስንት ነው? ……………!

ዛሬ እሁድ መጋቢት 8 የኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶ ች ጉባኤያቸው እንደጀመሩ ኢቲቪ እየነገረን ነው።

በመቐለ ከተማ ‘ቀውጢ’ የተባለ የድጋፍ ሰልፍ ተጠርቶ እየተከናወነ ይገኛል። ሃይለኛ ዝግጅት ነው። በህወሓት ታሪክ ለድርጅታዊ ጉባኤ ስብሰባ ድጋፍ ለማሰባሰብ ህዝባዊ ሰልፍ ሲጠራ የኣሁኑ ለመጀመርያ ግዜ ነው። ደርግም ለሞት ሲቃረብ ሰልፍ መጥራት ኣብዝቶ ነበር ኣሉ።
...

ለፕሮግራሙ የወጣ ወጪ ስንት መሆኑ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ኣልተሳካም። ግን በጣም ብዙ መሆኑና ከትግራይ መንግስት ካዝና እንደሆነ ግን ኣውቄያለሁ። ፓርቲና መንግስት ኣንድ የሆነበት ሀገር፤ የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለፓርቲ ሰልፍ ዝግጅት ሲውል ኣይገርምም!!!?

ከሰልፉ በላ ይ ይበልጥ ቀልቤን የሳበው ግን የትእምት (ትካል እግሪ ምትካል ትግራይ) ወይ EFFORT (Endowment Fund For the Rehabilitation of Tigray) ተሽከርካሪዎች በመቐለ ከተማ ያደረጉት ትእይንት (ሰልፍ) ነው። በጣም ገርሞኛል። ብዛታቸው፣ ዓይነታቸው፣ ሁለመናቸው።

ትእምት በጣም ሃብታም መሆኑ ገባኝ። ‘ታድያ ይሄን ይዘን ለምን ኣላደግንም?’ የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። የሚገርም ነው።

ገርሞኝ ዝም ኣላልኩም። ኣንድ የትእምት ሰራተኛ የትእምት ኩባኒያዎች ካፒታል ስንት እንደሆነ ጠይቄው የሚከተለውን መረጃ ሰጥቶኛል። (ፅሑፉ የራሱ ነው)።

! …….. ወይ የመናገር ነፃነ …..ት! …….!

እንዲህም ተነስተዋል፣ “ኣብርሃ መቀሌ ዉስጥ ሁኖ የፈለገውን እየተናገረ፡ ‘ ኢትዮዽያ ዉስጥ የመናገር መብት የለም’ ይላል።”

ጥሩ የሚባል ኣስተያየት ነው። ነገር ግን የመናገር መብት ወይ ነፃነት በኣግባቡ ካለመገንዘብ የመነጨ ይመስለኛል።

(1) የመናገር መብት በፌስቡክ ብቻ መፃፍ መቻል ማለት ነው? ስለ መናገር መብት ስናገር፣ መናገር የምችልባቸው መድረኮች እንዲኖሩ እየጠየቅኩ ነው። ለምሳሌ እኔ በነፃ ሚድያ (የግል ቲቪ፣ ሬድዮ፣ ጋዜጣ፣ መፅሄት፣ ጦማርና የተለያዩ ዌብሳይቶች እንደፈለኩ መናገርና መፃፍ እችላለሁ??? እነዚህ ሁሉ የተዘጉ ኣይደሉምን??? በነፃነት እንዳንናገር ኣልታፈንም??? የግል ሚድያ ሲታፈን የመናገር መብትም ኣብሮ እየታፈነ ነው።

ስለዚ በፌስቡክ መፃፍ ስለቻልኩ የመናገር መብቴ ተከብሮልኛል ማለት ኣይቻልም። ፌስቡክ የኢትዮዽያ መንግስት የግል ስጦታ ኣይደለምና።

(2) እንበልና እኔ (በፌስቡክም በሌላም) የፈለኩትን ነገር እንድናገር ተፈቅዶልኛል። እኔ የመናገር መብት ኣለኝ ማለት ሁሉም የኔ ኣምሳያ የመናገር መብት ኣለው ማለት እንችላለን? ብዙ ዜጎች (እንኳን የመናገር መብታቸው ሊጠቀሙና) ለህይወታቸውም ፈርተው ይኖራሉ። ብዙ ጓደኞቼ ህወሓትን ባለመደገፋቸው ከስራ ተባረዋል። የፈለጉትን የተናገሩ ከገዢው ፓርቲ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል።

Wednesday, 27 March 2013

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?

የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡

ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡

“ዘጠኝ ቦላሌ…” ከይኸነው አንተሁነኝ ከይኸነው አንተሁነኝ

የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ሕወሃት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም። አውቃለሁ ብሎ ያቀዳቸው ተማከርኩ ብሎ ያወራቸው ሁሉም እንዳይሆን እንዳይሆን እየሆኑበት መሆኑ ይሰማል። ብዙ የተነገረለት ስንት የተባለለት ”የሕወሃቱ የእድገት ትራንስፎርሜሽን”ም ብዙም እንዳልጨበጠ የሚወራው ሳይሆን እየሆነ ያለው የምድሩ ላይ እውነት እያሳበቀበት ነው። ወትሮም ያልነበረው የሁለት አሃዝ ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ፉከራም ወደ ሗላ እየባረቀ ”ለነዚህ ያህል ዓመታት ሁለት አሃዝ ተከታታይ እድገት ለምን ድህነትንና ስደትን በመጠኑ እንኳ ሊቀርፍ አልቻለም?” የሚለውን የዓለም ማሕበረሰብ ጥያቄ ባልተሳከረ መልኩ ለመመለስ ለሕወሃት አስቸጋሪ ሆኖበታል። ምክንያቱም የኑሮ ውድነቱ፣ ርሃብ እና ችግር የሚያንገላታው የሕዝባችን ቁጥር፣ የተማረ የሰው ሃይል ስራ አጥነት እንደጉድ መጨመር፣ ሁሉን አቀፍ ስደት ለመናገር ከሚያስቸግር በላይ መሆን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከምንም ጊዜ በላይ ዋጋው ረክሶ የታየባቸው ዘመናት በሙሉ በሕወሃት የአገዛዝ ዘመን በተለይም ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አመጣሁ እያለ በሚለፍባቸው በነዚሁ ዓመታት ነበርና ነው። ለዚህም ይመስላል የዘንድሮው የሕወሃት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ለዓመታት የሙጥኝ ያላትን ያችን ጉደኛ አስራ አንድ ቁጥር ለቆ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወዳስቀመጡት የእድገት ትንበያ አሃዝ ለመድረስ ወደ ታች የተምዘገዘገው።

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡

በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡