No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday, 17 January 2013

“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”ዘገባው የ15 አገራትን ዝርዝር አውጥቷል

የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡
እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡

« ፍቅረኛሞቹ» አዜብ መስፍንና ብርሃነ ኪዳነማርያም(ከኢየሩሳሌም አርአያ)


አዜብ መስፍንን ከሱዳን አምጥቶ ሕወሓትን እንዲቀላቀሉ ያደረገ ነው። የፍቅር ግንኙነትም ነበራቸው። ይህ ሰው ብርሃነ ኪዳነማርያም (በቅፅል ስሙ ብርሃነ-ማረት) ነው። አዜብና ብርሃነ ድርጅቱን ሲቀላቀሉ የተቀበሏቸው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ (አሁን የአረና አባል) ነበሩ። ጥቂት የበላይ አመራሮች በሁለቱ የፍቅር ግንኙነት ዙሪያ መከሩ። ከዛም የብርሃነና የአዜብ ግንኙነት እንዲቋረጥ በማድረግ ከለያዩዋቸው በኋላ ከመለስ ዜናዊ ጋር አዜብ እንዲጠቃለሉ ሆነ። (በነገራችን ላይ አንዳንድ ወገኖች አዜብና ሟቹ ክንፈ ገ/መድህን በጫካ ግንኙነት እንደነበራቸው ተደርጎ የሚነገረው ከእውነት የራቀ እንደሆነ የቅርብ ታማኝ ምንጮች ይገልፃሉ፤)
ወደ ዋናው ርዕሰ ጉዳይ እናምራ፥ በሕወሓት ውስጥ አድፍጠው መሰሪ ተግባር ከሚፈፅሙት አንዱ ነው ተብሎ በፓርቲው ወገኖች የሚፈረጀው ብርሃነ ኪ/ማርያም (ብርሃነ-ማረት) ማንነትና አደገኛ አካሄድ ምን እንደሚመስል ከላይ የተገለፀውን መንደርደሪያ ያስቀደሙ ታማኝ ምንጮች ተከታዩን ይላሉ።

Wednesday, 16 January 2013

ኢትዮጵያ፤ የመዳኛ ወቅትና፤ የዕረቀሰላም ጊዜ


ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
የረፖርተር ድሕረ ገፅ ሲዘግብ:በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት  ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል:: በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል፡፡ ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል፡፡ ይህም መሰረታዊ ችግሩና መንስኤው አስተዳደራዊ ድክመት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ ባለፈው በእለተ ዕረቡ ጃንዋሪ 2 2013 የተቀሰቀሰው ግጭትም በተለይ በሁለት ጎሳዎች በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መሃል

Tuesday, 15 January 2013

አዲስ አበባ ረክሳለች! ለጋ ህጻናትን ለባለስልጣናትና ባለሃብቶች ማቅረብ “ትርፋማ” ሆኗል


ትውልድ አምካኝ ቤቶችን፣ ትውልድ አምካኝ ደላሎችን፣ በህጻናት የወሲብ ንግድ ገንዘብ የሚሰበስቡትን፣ ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪዎቹ፣ ህግ አወጪዎቹና ዋናዎቹ “የአገሪቱ ህዳሴ ባለቤቶች” የሚባሉት በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደሙባቸዋል።
ሃኪሞች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ አገር የሚመሩት፣ ህግ የሚያስከብሩት፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ አውራ ባለስልጣናት፣ ህዝብ ፊት ቀርበው በልማት ስም የሚምሉት ሃብታም ተብዬዎች፣ የፖሊስ የበላይ አመራሮች፣ የስለላ አውራ ሰዎች፣ አጫፋሪዎች፣ የአቻ ፓርቲ አመራሮችና መካከል ጥቂት የማይባሉ ከዳር እስከዳር መመሸጊያቸው ዝግ ቤቶች ናቸው። አንዳንዴም ከዝግ ቤቶች ፍራሽ ላይ ሆነው የፖለቲካ መመሪያ የሚሰጥበት አጋጣሚ አለ። ይህን አስደንጋጭ እውነት “መርከስ” ነው። አዲስ አበባ ይፋ አደረገችው እንጂ በየክልሉ ከተሞች የሚደረገው ተመሳሳይ ነው።

Temesgen Desalegn ‹‹አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሁለት ወቅታዊ ጉዳዮች

1. ከመለስ ሞት በኋላ መረጋጋት የተሳነው ኢህአዴግ ከበርካታ ችግሮች ጋር ፊት ለፊት ተፋጧል፡፡ ከችግሮቹ በከፊልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡ …በረከት ስምኦን የነበራው ተደማጭነት እየተሸረሸረ ነው፣ የበረከት ባለቤት የበረከትን መፅሃፍ ለመሸጥ (ገዥ ፍለጋ) በየተቋማቱ እየተንከራተቱ ነው፤ አዲሱ ለገሰ የተደማጭነት መስመሩን ‹‹ኢህአዴግን ለማጠናከር›› በሚል ምክንያት ይበልጥ እያደረጀ ነው፤ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከቀን ወደ ቀን በህወሓት ውስጥ ተሰሚነቱ እየጨመረ ነው፣ በእርግጥም ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች የአስጊ ህመም ችግር የሌለባቸው ተብለው የሚመደቡት ...ደብረፅዮን፣ አባይ ፀሀዬና ቴውድሮስ አድሃኖም ናቸው፣ አቦይ ስብሃት ነጋ ‹‹መፈንቅለ ፓርቲ›› በህወሓት ውስጥ ለማድረግ ቀን ከለሌት እያሴሩ ነው፣ ከሁለት ወር በኋላ የሚደረገው የኢህአዴግ ጠቀላላ ጉባኤ አዲስ ነገር ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል፤ ኦህዴድ በሹም ሽር ሊናጥ ነው፣ አለማየሁ አቱምሳ በሩቅ ምስራቅ ለሚከታተለው ህክምና እስከአሁን ያለውንም ሆነ በቀጣይ የሚያስፈልገውን ወጪውን እየሸፈነ ያለው ሼክ መሀመድ አላሙዲ ነው፤ ለምን? አለማየሁ የመንግስት ባለስልጣን ነው፣ በተጨማሪም ሆን ተብሎ በተሰጠው መርዝ ነው ታማሚ የሆነው የሚባለውን ወሬ ይዘን፣ ከዚህ ጀርባ ማን ነው ያለው? የሚል ጥያቄ መቀርቡ አይቀርም (የሰማሁት መረጃ ጆሮ ያቃጥላል) ግን ለምን? ኩማ ደመቅሳ መልካም አስተዳደር ባለማስፈንና ሙስናን መቆጣጠር

ጥፋቱ የማን ነው? “ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን

ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም በውድ አገራቸው የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ ታወቀ። አቶ ስዬ አብርሃ፣ አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ያደረጉት አቶ በረከት “አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በሚኒስትር ማዕረግ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ይህንን የተናገሩት Eritrean Oppositions Arabic Paltalk በሚሰኝ የኤርትራ ተቃዋሚዎች የፓልቶክ መወያያ ክፍል እንግዳ ሆነው ባካሄዱት የጥያቄና መልስ ነው።

"Egypt has succeeded in stopping any funding to build Ethiopian Renaissance Dam" Egypt Minister of Water

Egypt State Information Service (Cairo)
Minister of Water Resources and Irrigation, Dr. Mohamed Baha'a El Din said in an interview with the official Chinese News Agency (Xinhua) on 12/1/2013 that Egypt will not sign the agreement of "Entebbe" signed by the Nile River upstream countries unless the conditions become suitable for downstream countries.
The Minister stressed that the agreement, without signing Cairo and Khartoum, is useless.