No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday, 10 September 2012

Two Swedish Journalists released

By William Davison -
Sept. 10 (Bloomberg) — Two Swedish reporters jailed by Ethiopian authorities last year for supporting terrorism were among more than 1,900 prisoners pardoned today by the government, Justice Minister Berhan Hailu said.
The release of the prisoners on the eve of the Ethiopian New Year marks the end of a process started during the rule of former Prime Minister Meles Zenawi, Berhan told reporters in the capital, Addis Ababa, today.
“Regarding the Swedish journalists, they are among the ones who will be released soon,” he said. “The journalists submitted petitions accepting they committed the crime.”

እናንተ ወያኔዎች እንደ ቀትር እባብ መቅበዝበዛችሁን ትታችሁ እንደ ሰው አስቡ!

ከፍቅሬ ዘለቀው
የአንባገነኖች ቁንጮና የዘረኞች መሀንድስ መለሰ ዜናዊ ሞት ነሐሴ 14፣ 2004 ዓ ም ይፋ ከተደረገ ጀምሮ የመንግሰቱ አቀንቃኞች፣ ደጋፊዎች፣ ሆድ አደሮች፣ ካድሬዎችና ሹማምንቶች ድንጋጤ ከመጠን ያለፈ ሆኖ እንደታየ ለመታዘብ በቅተናል። እውን ይህ ሁሉ ድንጋጤና መርበትበት እነሱ እንደሚሉት አገሩን የሚወድ፣ አርቆ አሳቢ፣ የልማት መሀንድስ፣ የአፍሪካ አባት፣ ኢየሱስ፣ ወዘተ… የሆነውን ንጉሳቸውን በማጣታቸው ነውን? መልሱ ግን አይደለም ነው። በሕዝብ አገልጋይነት ስም፣ በጌታቸው አጋፋሪነት የሕዝብን ንብረትና ሀብት በመዝረፍ ያገኙት የነበረው ጥቅም ሲቀር እየታያቸው እንጂ።
በጣም የሚያሳዝነው ግን እነሱ ያዘኑትን ያህል፣ ይህን የተራበና በፍትህ እጦት የተሰቃየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእነሱ ተርታ በግዳጅና በጥቅም አሰልፈው እንዲያለቅስ ማድረጋቸው ሳያንስ አላዘናችሁም፣ የእዝን መዋጮ አላዋጣችሁም፣ የመለስን ካኒታራ አልገዛችሁምና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመፍጠር ማሰቃየታቸው፣ መደብደባቸውና ወደ ዘብጥያ ማጋዛቸው ነው። ከዚህም አልፎ በአቶ መለስ ሞት የተደሰቱትን በስሜታዊነት መግደላቸው፣ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች መዘገባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

TPLF to Install Three Deputy Prime Ministers

by Tsinat Haile

 
Coming under pressure from different corners and mainly from the international community, TPLF had no choice left but to cave in to their demands including to the ones that are coming from its surrogate groups and various sections of the society. There are rumors that a final deal has been reached to an arrangement in which HD would become the PM and there would be three Deputy Prime Ministers (DPM’s).

Accordingly, Girma Birru of OPDO is mentioned as the frontrunner for the DPM position in charge of economic affairs and all the ministries in this sector report to him.

Sunday, 9 September 2012

አሜሪካ የተደበቀው ወንጀለኛ


ከኢየሩሳሌም አርአያ
የህወሃት አባል ነው ። ከትጥቅ ትግሉ ዘመን አንስቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ስልጣን እስከተቆናጠጠበት ጊዜ ድረስ ያለው የጀርባ ታሪክ በንጹሃን ደም የተጨማለቀ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ ግለሰብ ተስፋዬ መረሳ ይባላል። ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ተራው ታጋይ ከሴት ጋር የፍቅርም ሆነ የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ እንደማይፈቀድለት አስገራሚው የፓርቲው ህግ ይደነግጋል። ይህ ህግ እስከ 1981 አ.ም የቆየ ሲሆን የበላይ አመራሩ ግን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው። ፆታዊ ግንኙነት ሲያደርጉ የተገኙ ተራ ታጋዮች ይፈፀምባቸው የነበረው ቅጣት በጥይት ተደብድቦ መገደል ነበር። በሺህ የሚቆጠሩ የፓርቲው ተራ አባላት የዚህ ቅጣት ሰለባ ሆነዋል። እነዚህ ታጋዮች እንዲረሸኑ ሲወሰን ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት እና በርካታው የፓርቲ አባላት ከሚያስታዉሷቸው ገዳዮች አንዱ እና ቀንደኛው ተስፋዬ መረሳ ሲሆን ፣ ከእርሱ በተጨማሪ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ ወ/ስላሴ ፣ሃይሉ (ሳንቲም) … በጭካኔ የግድያ ተግባራቸው ይጠቀሳሉ። ፊደል ያልቆጠሩት እነዚህ ወንጀለኞች የገዛ የትግል ጓዶቻቸውን ለመረሸን እጅ በማውጣት “እኔ… እኔ” እየተባባሉ ያሳዩ የነበረው ሰይጣናዊ ፉክክር እና ጥድፊያ ብዙ የፓርቲው አባላት አሁን ድረስ ያስታውሱታል።

ከመለስ በኋላስ?

ተመስገን ደሳለኝ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዕሁድ ዕለት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል፡፡ ለሁለት ሳምንት ያህልም ለእልፍ አእላፍት አንገብጋቢ ጉዳዮቻችን ግርዶሽ ሆኖብን የነበረው ብሔራዊ ሀዘንም አብሮ አብቅቷል፡፡ ለቤተሰቦቻቸው እና ለዘመዶቻቸው መፅናናትን ከልብ እመኛለሁ፡፡ ስለዚህም ከቀብር መልስ ባሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገር መጀመር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ (የአቶ መለስ ሞት በመንግስት በይፋ ከተነገረ በኋላ ጥቂት ባለስልጣናት እና አንድ ቱጃር ነጋዴም ህይወታቸው እንዳለፈ በማህበራዊ ድረ-ገፆች በስፋት ሲዘገብ ቢቆይም ‹‹ሟቾቹ›› በኢቲቪ እየቀረቡ በአቶ መለስ መሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው አለመሞታቸውንም በገደምዳሜ አሳይተውናል፡፡ ይህ አንድ እውነት ነው፡፡ አልፎ ተርፎም ሞቱ የተባሉት ቱጃር ነጋዴ ከጥቂት ቀናት በፊት ሰራተኞቻቸውን ሰብስበው ‹‹መለስን ከአንድ ወር ከአስራአምስት ቀን በፊት ብራስልስ ሄጄ ጠይቄዋለሁ፡፡ አልጋው ላይ ተኝቶ በላፕቶፑ ስራውን እየሰራ ነበር፡፡ ረመዳን ነው አልዋሽም፣ ሞተ በተባለበት ጊዜ የውሸት ነው አልሞተም ነበር›› ብለዋል፡፡ እንግዲህ ነጋዴው አቶ

Yenemeles gemena be Araya Woldu sigalet. Aug 02,2012. part 01


ESAT Ethiopian News Sept. 08, 2012