አቶ ስዬ አብርሃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አሰከባሪ ተቋም ውስጥ በወታደራዊ አማካሪነት በጥሩ ደመወዝ መቀጠራቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ከወንድሞቻቸው ጋር ለስድስት አመት ታስረው የተፈቱት ስዬ በተፈቱ ማግስት የአሜሪካን ድምፅ ራዲዬን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ « ፖለቲካ ከልጅነቴ ጥርሴን የነቀልኩበትና አብዛኛው እድሜዬን ያሳለፍኩበት በመሆኑ ከትግሉ መድረክ ልርቅ ጨርሶ አልችልም» በማለት አስረግጠው መናገራቸውን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ። « መድረክ » የሚል የፖለቲካ ስብስብ ከፈጠሩና የአንድነት አባል መሆናቸውን በይፋ ካወጁ በኋላ «ለትምህርት» በሚል ወደ አሜሪካ የመጡት ስዬ ከአንድነት ፓርቲ ሪፖርት እንዲያደርጉ የቀረበላቸውን ተደጋጋሚ ጥያቄና ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አመልክተዋል። በመጨረሻ « በቅርቡ አገር ቤት ተመልሼ ትግሌን እቀጥላለሁ » ማለታቸውን ያልሸሸጉት ምንጮቹ ስዬ ይህን በተናገሩ ሰሞን በሲያትል በተደረገ ስብሰባ ላይ « ለ21 አመት የተጀመረውን ልማትና ዲሞክራሲ እናስቀጥላለን» በማለት ብዙዎችን አንገት ያስደፋና ያሳዘነ ንግግር ማሰማታቸውን አስታውሰዋል። በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለፅ አደባባይ መውጣታቸው ብሎም « ያሰራቸውን ስርአት ዲሞክራሲያዊ » አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው አስገራሚ ነበር ብለዋል።
No comments:
Post a Comment