Thursday, 23 May 2013

አራት የኢአዴግ ባለስልጣኖች ከሀገር እንደወጡ አልተመለሱም

ለሁለት ሳምንት ስልጠና ወደ አሜሪካ አገር ከሄዱ 20 የመንግስት ባለስልጣናት መካከል በቅርቡ ከስራው የተነሳው እና በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠረጠረው የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ የነበረው ኦሞድ ኦቦንግ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል አስተዳዳሪ አብዱላዚዝ መሃመድ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጨምሮ አብዛጮቹ ባለስልጣናት ስልጠናቸውን ቢጨርሱም ወደ ሃገር ቤት ከሚመለሰው ቡድን ተለይተው መጥፋታቸው ታወቀ። በቅርቡ ከተጀመረው የሙስና እስር ጋር ተያይዞ በርካታ ሃገር ቤት ያሉ ባለስልጣናት እና ባለሃብቶችም ከነቤተሰቦቻቸው ከሃገር ለመውጣት እየተሯሯጡ እንደሆነ ተዘግቦአል።
ዝርዝሩን እንደደረሰን አናሳውቃለን

1 comment:

  1. አብረው ሲበሉ ቆይተው ሲነቃባቸው ወይም ሲኮራረፉ ተቃዋሚ ነኝ በማለት ወደ አሜሪካ ወይም ወደ አውሮፓ መፈርጠጥ በዛ::

    ReplyDelete